Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ተመልከቱ

    እያንዳንዱ ሰው በጥንቃቄ ለማሰብ ጊዜ ይውሰድ፤ በክርስቶስ ምሳሌ ውስጥ ቤት ለመገንባት ጀምሮ መጨረስ እንዳቃተው ሰው አትሁኑ፡፡ እንቅስቃሴው ምን እንደሚያስከትል በጥንቃቄ ሳይታይ፣ እያንዳንዱ ነገር ተመዝኖ ሳይታይ፣ እርምጃ መወሰድ የለበትም፡፡…ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ልዩ ልዩ ችሎታው ሥራ ተሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ በማመንታት አይንቀሳቀስ፣ ነገር ግን በጽናት ሆኖ በትህትናና እግዚአብሔርን በመታመን ይንቀሳቀስ፡፡Amh2SM 362.1

    አንድ ነገር ለማድረግ የሚጣደፉና ምንም ነገር ወደማያውቁት ሥራ ለመግባት የሚጣደፉ አንዳንድ ግለሰቦች ይኖራሉ፡፡ እግዚአብሔር ይህን አይፈልግም፡፡ በቅንነት፣ በጸሎት፣ ቃሉን በጥንቃቄና በጸሎት በማጥናት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት በነቃ አእምሮና ልብ አስቡ፡፡…የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት ትልቅ ነገር ነው፡፡…Amh2SM 362.2

    በባትል ክሪክ ያለችው ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ምክር እንድትሄድ ቃላቶችን እልካለሁ፡፡ ለብዙዎቻችሁ ከባትል ክሪክ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡ ደግሞም ከባትል ክሪክ ስትወጡ ምን እንደምታደርጉ በደንብ የተገለጸ እቅድ የመኖር አስፈላጊነትም አለ፡፡ ከባትል ክሪክ ስትወጡ በጥድፊያ አትውጡ፡፡ ለምን እየወጣችሁ እንደሆነ ሳታውቁ በችኮላ አትሂዱ፡፡ እነሆ ጠቢብና አሳቢ ጄኔራሎች፣ ሚዛናዊ የሆኑ ሰዎች፣ ችግር የማያስከትሉ መካሪዎች፣ ስለ ሰብአዊ ተፈጥሮ መረዳት ያላቸው ሰዎች፣ በፈሪሃ-እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመሩና እንደሚመክሩ የሚያውቁ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡Amh2SM 362.3