Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ልጆቻችንን እንደገና እናያቸዋለን

    ልጇ ለሞተባት እናት የተሰጠ ማጽናኛ

    በልጅሽ ሞት የደረሰብሽን ልምምድ ስትናገሪ፣ ፈቃድሽን ለሰማያዊ አባትሽ በማስገዛት፣ ጉዳዩን ለእርሱ በመተው እንዴት በጸሎት ዝቅ እንዳልሽ ስትናገሪ የእናትነት ልቤ ተነክቷል፡፡ እኔም አንቺ ባለፍሽው ዓይነት ልምምድ ውስጥ አልፌያለሁ፡፡ Amh2SM 258.1

    የመጀመሪው ልጃችን በአሥራ ስድስት ዓመቱ በሕመም ተቀሰፈ፡፡ የጤንነቱ ሁኔታ አሳሳቢ በሆነበት ጊዜ ታሞ ወደ ተኛበት አልጋ ጠራንና እንዲህ አለ፣ “አባቴና እናቴ ሆይ፣ ከበኩር ልጃችሁ መለየት ከባድ ሊሆንባችሁ ይችላል፡፡ የእኔን ሕይወት ማትረፍ ለእግዚአብሔር መልካም መስሎ ከታየው፣ ስለ እናንተ ስል ብድን ደስ ይለኛል፡፡ ሕይወቴ አሁን ወደ ፍጻሜ መምጣት ለእኔ ጥቅምና ለእርሱ ስም ክብር የሚሆን ከሆነ ነፍሴ ደህና ናት እላለሁ፡፡ አባቴም ለብቻህ ሂደህ ጸልይ፣ እናቴም ለብቻሽ ሂደሽ ጸልዪ፤ ጸልዩ፡፡ ከዚያ በኋላ እናንተም እኔም እንደምንወደው እንደ አዳኜ ፈቃድ መልስ ታገኛላችሁ፡፡” አብረን የምንጸልይ ከሆነ ሀዘኔታችን ይበረታና እግዚአብሔር እንዲሰጠን መልካም ያልሆነውን ነገር እንጠይቃለን ብሎ ፈርቶ ነበር፡፡ Amh2SM 258.2

    እሱ እንደጠየቀን አደረግን፣ ጸሎታችን በሁሉም መልኩ አንቺ ከጸለይሽው ጸሎት ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ ልጃችን እንደሚፈወስ ምንም ማረጋገጫ አልተሰጠንም ነበር፡፡ አዳኛችን በሆነው በኢየሱስ ሙሉ እምነቱን በማድረግ ሞተ፡፡ የእርሱ ሞት ለእኛ ታላቅ ምት ነበር፣ ነገር ግን ሕይወቱ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮ ስለነበር በሞት ውስጥ እንኳን ድል ነበር፡፡ Amh2SM 258.3

    ከበኩር ልጄ ሞት በፊት ሕፃን ልጄ እስከ ሞት ታሞ ነበር፡፡ ጸሎት አደረግንና እግዚአብሔር ልጃችንን ያድንልናል ብለን አሰብን፤ ነገር ግን በሞት ዓይኑን ጨፍነን ሕይወት ሰጭ የሆነው የራሱን የተወደዱ ክቡራን ልጆች ሞት ወደሌለበት ዘላለማዊነት እስከሚያነቃቸው ቀን ድረስ በኢየሱስ እንዲያርፍ ቀበርነው፡፡Amh2SM 258.4

    ከዚያ በኋላ ለሰላሳ ስድስት አመት ከጎኔ የቆመው የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ ባለቤቴ ተወሰደብኝና ሥራ ለመስራት ብቻዬን ቀረሁ፡፡ እሱ በጌታ አንቀላፍቷል፡፡ በእሱ መቃብር ላይ የማፈሰው እንባ የለኝም፡፡ ነገር ግን አጠገቤ አለመኖሩ ምንኛ ይሰማኛል! የምክርና የጥበብ ቃላቶቹ ምንኛ ይናፍቁኛል! ለብርሃንና ለምሪት፣ ሥራውን እንዴት ማቀድና መንደፍ እንደሚያስፈልግ ጥበብ ለማግኘት የእሱ ጸሎቶች ከእኔ ጸሎቶች ጋር ሲዋሃዱ ለመስማት ምንኛ እናፍቃለሁ! Amh2SM 259.1

    ነገር ግን ጌታ መካሪዬ ነበር፣ ለአንቺም ሀዘንሽን እንድትሸከሚ ፀጋን ይሰጥሻል፡፡ Amh2SM 259.2

    ስለ ትንንሽ ልጆችሽ መዳን ትጠይቂያለሽ፡፡ የክርስቶስ ቃሎች መልስሽ ናቸው፡- “ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው፣ አትከልክሏቸውም፡- የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና” (ሉቃስ 18፡ 16)፡፡ Amh2SM 259.3

    እንዲህ የሚለውን ትንቢት አስታውሺ፣ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናትን እምቢ አለች፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ድምፅሽን ከልቅሶ ዓይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ ዋጋ ይሆናልና፣ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ፡፡ ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ ይላል እግዚአብሔር፣ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ” (ኤር. 31፡ 15-17)፡፡ Amh2SM 259.4

    ይህ ተስፋ የአንቺ ነው፡፡ ልትጽናኝና በእግዚአብሔር ልትታመኚ ትችያለሽ፡፡ ከመከራ ጊዜ በፊት ብዙ ትንንሽ ሕጻናት እንደሚቀነሱ ጌታ መመሪያ ሰጥቶኛል፡፡ ልጆቻችንን እንደገና እናያቸዋለን፡፡ በሰማይ አደባባዮች እንገናኛለን እናውቃቸውማለን፡፡ በእግዚአብሔር ታመኚ፣ አትፍሪም፡፡ --Letter 196, 1899.Amh2SM 259.5