Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 45—በገጠር ስለመኖር የቀረበ ጥሪ

    ዛሬ ጧት ሁለት ሰዓት እስኪያልፍ ድረስ እንቅልፍ ማግኘት አልቻልኩም ነበር፡፡ ሌሊቱን ኮሚቴ ላይ ነበርኩ፡፡ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሀብት ራሳቸውን እንዲረዱና ልጆቻቸውን ለማዳን ከከተማዎች እንዲወጡ አንዳንድ ቤተሰቦችን እየተማጸንኩ ነበር፡፡ አንዳንዶች ቆራጥ ጥረቶችን ሳያደርጉ እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡Amh2SM 354.1

    የምህረት መላእክት የሎጥን፣ የሚስቱንና የልጆቹን እጆች በመያዝ አስቸኮሉአቸው፡፡ ቶሎ እንዲወጡ እግዚአብሔር እንደፈለገባቸው ሎጥ ፈጥኖ ቢሆን ኖሮ ሚስቱ የጨው አምድ አትሆንም ነበር፡፡ ሎጥ ያለመጠን የመዘግየት መንፈስ ነበረበት፡፡ እንደ እርሱ አንሁን፡፡ ሎጥ ሶዶምን ለቆ እንዲወጣ ያስጠነቀቀው ያው ድምጽ እኛንም «ከመካከላቸው ውጡ፣ የተለያችሁ ሁኑ፣... እርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ» ይለናል (2ኛ ቆሮ. 6፡ 17)፡፡ ይህንን ማስጠንቀቂያ ሰምተው የሚታዘዙት መጠጊያ ያገኛሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በደንብ ይንቃና ቤተሰቡን ለማዳን ይሞክር፡፡ ለሥራው ወገቡን ይታጠቅ፡፡ ቀጥሎ መደረግ ያለበት ነገር ምን እንደሆነ እግዚአብሔር ነጥብ በነጥብ ይገልጣል፡፡Amh2SM 354.2

    በሐዋርያው ጳውሎስ አማካይነት የእግዚአብሔርን ድምጽ አድምጡ፡- «በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” (ፊልጵ. 2፡ 12፣ 13)፡፡ ሎጥ ሜዳውን የተጓዘው ፈቃደኛነት በሌለባቸውና አዝጋሚ እርምጃዎች ነበር፡፡ ለረዥም ጊዜ ከክፉ ሰራተኞች ጋር ሕብረት ስለፈጠረ በሜዳው ላይ ሚስቱ ለዘላለም የጨው አምድ ሆና እስክትቀር ድረስ የነበረበትን አደጋ ማየት አልቻለም ነበር፡፡ The Review and Herald, Dec. 11, 1900.Amh2SM 354.3

    ልጆች ለጥፋት ዝግጁ ለሆኑ የከተማ ፈተናዎች አይጋለጡ፡፡ ከተማዎችን ለቀን እንድንወጣ ጌታ ማስጠንቀቂያና ምክር ልኮልናል፡፡ አባቶችና እናቶች ሆይ፣ የልጆቻችሁን ነፍሶች የምትመለከቱትእንዴት ነው? በቤተሰቦቻችሁ ውስጥ ያሉትን አባላት ወደ ሰማያዊ አደባባዮች እንዲነጠቁ እያዘጋጃችኋቸው ነው ወይ? የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት እንዲሆኑ እያዘጋጃችኋቸው ነው ወይ? የሰማያዊው ንጉሥ ልጆች እንዲሆኑ እያዘጋጃችሁ ናችሁን? «ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?” (ማር. 8፡ 36)፡፡ ምቾት፣ ደስታና ተስማሚ ሁኔታ ከልጆቻችሁ ነፍሶች ዋጋ ጋር የሚነጻጸረው እንዴት ነው? Manuscript 76, 1905.Amh2SM 355.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents