Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር የሚሻለውን ያውቃል

    ነሐሴ 14 ቀን 1892 ዓ.ም፡፡ ለበርካታ ወራት ስሰቃይበት የነበረው ሥቃይ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ለተጸለየው ጸሎት መልስ ሆኖ በአንድ ጊዜ ባለመወገዱ ተገረምኩ፡፡ ነገር ግን «ጸጋዬ ይበቃሃል” (2ኛ ቆሮ. 12፡ 9) የተባለው ተስፋ ተፈጸመልኝ፡፡ በእኔ በኩል ምንም ጥርጣሬ ሊኖር አይችልም፡፡ ሀዘኔን ወደ ማን መውሰድ እንዳለብኝ ስላወቅኩ የሕመም ሰዓቶቼ የጸሎት ሰዓቶች ነበሩ፡፡ ደካማ የሆነ ብርታቴን ገደብ የለሽ የሆነውን ኃይል የሙጥኝ ብዬ በመያዝ የማጠንከር ዕድል ነበረኝ፡፡ ቀንና ሌሊት በእግዚአብሔር ተስፋዎች ጽኑ አለት ላይ እቆማለሁ፡፡Amh2SM 240.2

    ልቤ በፍቅር መታመን ወደ ኢየሱስ ይሄዳል፡፡ ለእኔ የሚሻለኝ ምን እንደሆነ ያውቃል፡፡ «በመከራ ቀን ጥራኝ፣ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ” (መዝ. 50፡ 15) በሚለው ተስፋ የሙጥኝ ባልል ኖሮ ሌሊቶቼ የብቸኝነት ይሆኑብኝ ነበር፡፡ --Manuscript 19, 1892.Amh2SM 240.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents