Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእምነት ተራመድ

    እውቀታችን በፈቀደልን መጠን ከተጻፈው ቃል ጋር ከተስማማን ምንም ዓይነት የተለየ እርካታ ቢሰማንም ባይሰማንም በእምነት መሄድ አለብን፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ እንድናምን፣ ተስፋችንን በእርሱ ላይ እንድናሳርፍ እና ያለ አንዳች ጥያቄና ጥርጣሬ በቃሉ እንድንታመን አንድያ ልጁን ኢየሱስን እንዲሞትና መስዋዕት እንዲሆን አሳልፎ በመስጠት ይህን የመሰለ የታላቅ ፍቅሩ አስደናቂ ማረጋገጫ ሰጥቶን ሳለ እንደማንታመንበት ስናሳይ እግዚአብሔርን እናዋርደዋለን፡፡ Amh2SM 242.3

    የተገለጸ ስሜት ቢኖርህም ባይኖርህም በእምነት የጸጥታ ጸሎቶችን በማቅረብ፣ የእርሱን ብርታት አጥብቀህ በመያዝ ወደ ኢየሱስ መመልከትህን ቀጥልበት፡፡ እያንዳንዱ የተጸለየው ጸሎት በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ እንዳረፈና በፍጹም አልተውህም ብሎ ቃል በገባው መልስ እንደተሰጠበት በመቁጠር ወደ ፊት ቀጥል፡፡ ጫና እና የሀዘን ስሜት ተሰምቶህ አዝነህ ሳለ እንኳን በልብህ ለእግዚአብሔር እየዘመርክና ዜማ እያዜምክ ወደ ፊት ተጓዝ፡፡ ይህን ልምምድ እንደሚያውቅ ሰው እነግርሃለሁ፣ ብርሃን ይመጣል፣ ደስታ የእኛ ይሆናል፣ ጭጋግና ደመናው ይወገዳል፡፡ ከጥላና ከጨለማ ጨቋኝ ኃይል ወደ እርሱ መገኘት የጠራ የፀሐይ ብርሐን እንሻገራለን፡፡ Amh2SM 242.4

    የበለጠ የእምነታችንን መግለጫ ብንሰጥ፣ እንዳሉን በምናውቃቸው እንደ ምህረት፣ ትዕግሥት እና የእግዚአብሔር ፍቅር ባሉ በረከቶች የበለጠ ሐሴት ብናደርግ በየቀኑ የበለጠ ጥንካሬ ይኖረን ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ልዑል በሆነው በክርስቶስ የተነገሩ ክቡር ቃላት ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ስጦታን ለመስጠት ፈቃደኛ ከሚሆኑት የበለጠ የሰማዩ አባታችን መንፈስ ቅዱስን ለሚጠይቁት ለመስጠት ፈቃደኛ ለመሆኑ በእኛ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ማሳደር የሚችል ማረጋገጫና ኃይል አይደሉምን?Amh2SM 243.1

    በየቀኑ ራሳችንን ለእግዚአብሔር መቀደስ አለብን፣ መስዋዕታችንንም ከእምነታችን ጋር የሚመጣጠን ስሜት እንዳለንና እንደሌለን ሳይመረምር እንደሚቀበል ማመን አለብን፡፡ ስሜትና እምነት ምዕራብ ከምስራቅ የሚለየውን ያህል የተለያዩ ናቸው፡፡ እምነት በስሜት ላይ አይደገፍም፡፡ ቢሰማንም ባይሰማንም በእምነት ወደ እግዚአብሔር ከልባችን መጮህ አለብን፣ ከዚያም በጸለይነው እንኑር፡፡ መተማመኛችንና ማስረጃችን የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ከጠየቅን በኋላ ሳንጠራጠር ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ አወድስሃለሁ፣ አወድስሃለሁ፡፡ በቃልህ አፈጻጸም አላሳፈርከኝም፡፡ ራስህን ገልጠህልኛልና ፈቃድህን ለማድረግ የአንተ ነኝ፡፡ Amh2SM 243.2

    ቁራዎች ወይም ማንኛውም ዓይነት ሥጋ ተመጋቢ የሆኑ አእዋፎች በመስዋዕትህና በእግዚአብሔር ሥጦታ ላይ እንዳያርፉ አብርሃም እንዳደረገው በታማኝነት ነቅተህ ጠብቅ፡፡ የቀንን ብርሃን በቃል ብቻ እንዳያይ እያንዳንዱ የጥርጣሬ ሀሳብ እንዳይፈጠር መጠበቅ አለበት፡፡ የጨለማ ኃይሎችን ከሚያከብሩ ቃላቶች ብርሃን ይሸሻል፡፡ ከሙታን የተነሳው የጌታችን ሕይወት በየቀኑ በእኛ መታየት አለበት፡፡ Amh2SM 243.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents