Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአዳዲስ ንድፈ-ሀሳቦች ማራኪነት

    የአክራሪነትና የስህተት ንድፈ-ሀሳቦች እያንዳንዱ ምዕራፍ እንደ እውነት እንዲወሰድ በመፈለግ በእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ መካከል ይመጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች ከወቅቱ እውነት ጋር ምንም ድርሻ የሌላቸውን የስህተት አስተያየቶች በአእምሮ ውስጥ ይሞላሉ፡፡ በራስ በተቀየሱ ውሳኔዎች ጥንካሬ፣ የአእምሮ ምሁርነትን ከሳይንስ ወይም እውቀት ተብሎ ከሚወሰድ ነገር ጋር በማስተባበር፣ ዓለምን የሚያሸንፍ ሥራን መጀመር እችላለሁ ብሎ የሚያስብ ማንኛውም ሰው ራሱን የሚያገኘው በራሱ ግምቶች ፍርስራሽ ውስጥ ተኝቶ ነው፤ በኋላ ለምን እዚያ እንደሆነ በግልጽ ያስተውላል፡፡… {2SM 14.2}Amh2SM 14.2

    ስህተትን የሚናገሩ ሰዎች እንደሚነሱ እግዚአብሔር ብርሃን ሰጥቶኛል፡፡ ቅዱስ እውነትን ወደ ተራ ነገሮች ደረጃ በማምጣት እግዚአብሔር በፍጹም ያልገለጸውን ነገር ሲሰሩና ሲናገሩ ነበር፡፡ ከእውነት ሳይሆን ሰዎች በትዕቢት ከፈጠሩአቸው የተሳሳቱ ሀሳቦች ውስጥ አከራካሪ ጉዳዮች ሲነሱ ነበር፣ ወደፊትም ይነሳሉ፡፡ እውነተኛው መፈተኛ እንዲጎላ በሚደረግባት ወቅት ምንም ዋጋ ከሌላቸው ሰው ሰራሽ መፈተኛዎች ጋር በእኩል እንዲታይ ለማድረግ የሰዎች አእምሮ ፈጠራዎች በፍጹም መፈተኛ ያልሆኑትን መፈተኛዎች ይፈለስፋሉ፡፡ ሁሉም ነገር እየመጣ ከትክክለኛ አስተምህሮ ጋር እንደሚቀላቀል እንጠብቃለን፣ ነገር ግን ግልጽ በሆነ መንፈሳዊ መረዳት እና በሰማያዊ ቅባት አማካይነት እምነትንና ትክክለኛ የሆነ ውሳኔን ግራ ለማጋባትና የወቅቱን ታላቅ፣ የተከበረ፣ የመፈተኛ እውነትን ዋጋ ለማሳጣት እየመጣ ያለውን ተራ ነገር ከቅዱስ ነገር ለይተን ማወቅ አለብን፡፡ . . . . {2SM 14.3}Amh2SM 14.3

    ሰዎች ለእውነት ትክክለኛ ያልሆነ ገጽታ ከመስጠታቸው፣ ከማቅለላቸው፣ በተሳሳቱ የሰዎች ክርክሮች በመመርኮዝ ዋጋ ከማሳጣታቸው የተነሳ ከዚህ ከመጨረሻ ዘመን የበለጠ እውነት የተሰቃየበት ጊዜ በፍጹም የለም፡፡ ሰዎች ለሕዝብ የጥበብ ምንጭ ናቸው ብለው ያመኑባቸውን የተለያዩ ዓይነት መናፍቅነቶች ከራሳቸው ጋር ይዘው መጥተዋል፡፡ ሕዝቦች በአንዳንድ እንግዳ በሆኑ አዳዲስ ነገሮች ስለተማረኩ ሰዎች ትክክል እንደሆነ አድርገው የሀሰት ማስረጃ የሰጧቸውን ሀሳቦች ባሕርይ ለመለየት በልምምድ የበሰሉ አይደሉም፡፡ ነገር ግን ይህን ሀሳብ ትልቅ ውጤት እንዳለው ነገር በመቁጠር የእግዚአብሔር ጥበብ ከሚገኝበት ነገር ጋር ማቆራኘት እውነት አያደርገውም፡፡ እነሆ፣ ይህ በቤተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚታየውን ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን ቅድስና እንዴት ይዘልፈው ይሆን፡፡ {2SM 15.1}Amh2SM 15.1

    ራሳቸው የፈለሰፉትን አዲስ ነገር ለማቅረብ የሚፈልጉ ሰዎች አዲስና እንግዳ የሆኑ ነገሮችን በሀሳባቸው ውስጥ ይፈጥራሉ፣ በደንብ ሳያስቡበት እንደ ከበረ ንድፈ ሀሳብ የሸመኑአቸውን እነዚህን ተለዋዋጭ ንድፈ ሀሳቦች ይዘው ብቅ በማለት እንደ የሞት ሽረት ጥያቄ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ --Letter 136a, 1898. {2SM 15.2}Amh2SM 15.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents