Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለአንዲት ራዕዮች አሉኝ ለምትል ሴት የተሰጠ መልእክት
    [ግንቦት 24 ቀን 1905 ዓ.ም ከዋሽንግተን ዲ ሲ የተጻፈ]

    በጀርመን አገር ስላለች እና ራዕዮች እንዳሏት ስለምትናገር እህት ሥራ በተመለከተ ልንይዝ ስለሚገባን አመለካከት ጥያቄ መጥቶልኝ ነበር፡፡ {2SM 97.1}Amh2SM 97.1

    ያለፈው ሌሊት በጌታ የተሰጠኝ ቃል ከዚህች እህት ምክር እንዲፈልጉ እግዚአብሔር ሕዝቡን አይመራም የሚል ነው፡፡ ይህቺ እህት እንድትሰራ ተጠርቻለሁ ብላ በምታስበው ሥራና በምታስተላልፈው መልእክት ብናደፋፍራት ብዙ ምስቅልቅል ይፈጠራል፡፡ ይህ ወይም ያ ሰው ማድረግ ያለበትን ነገር የመንገር ሥራ ጌታ አልሰጣትም፡፡ ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፣ «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ኣሳርፋችኋለሁ፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴ. 11፡ 28-30)፡፡ «ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፣ ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በንፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና፡፡ ያ ሰው ከእግዚአብሔር አንዳች የሚያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡ 5-7)፡፡ {2SM 97.2}Amh2SM 97.2

    ሰዎች ምሪትን ለማግኘት በግላቸው እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ፣ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዲያጠኑ፣ በትህትና፣ በጸሎትና በሕያው እምነት አብረው እንዲመክሩ አስተምሯቸው፡፡ ነገር ግን ይህቺ እህት ለሕዝብ እንድታስተላልፍ እግዚአብሔር መልእክት እንደሰጣት እንድታስብ አታደፋፍሯት፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የተሰጠኝ ብርሃን ይህቺ እህት ለሌሎች የሚሆን መልእክት እንደተሰጣት እንድታስብ ከተደፋፈረች ውጤቱ አጥፊ ይሆንና የራሷን ነፍስ የማጣት አደጋ ውስጥ ትሆናለች፡፡ {2SM 97.3}Amh2SM 97.3

    ለዚህች እህት የእኔ መልእክት ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ሂጂ፣ ለራስሽ ወደ እርሱ ተመልከቺ፡፡ ጌታ የሌሎችን ተግባር የማመልከት ሥራ አልሰጠሽም፤ ነገር ግን መለኮታዊ መገለጦች አሉኝ የምትይና ሌሎችን ለማበረታታት የምትፈልጊ እውነተኛ ክርስቲያን ከሆንሽ ረዳት መሆን ትችያለሽ፡፡ --Manuscript 64, 1905. {2SM 98.1}Amh2SM 98.1