Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የራዕይ አስር መልአክ

    የፍርዱ ሰዓት መድረሱን የሚያውጀው የራዕይ 14 መልእክት በመጨረሻ ዘመን ይሰጣል፤ በራዕይ አስር ላይ አንድ እግሩ በምድር ላይ ሆኖ ሌላኛው እግሩ ደግሞ በባሕር ላይ እንዳለ ሆኖ የተወከለው መልአክ የሚያሳየው መልእክቱ ወደ ሩቅ አገሮች እንደሚወሰድ፣ ውቅያኖስን እንደሚሻገር፣ እና በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶችም ለዓለም የሚሰጠውን የመጨረሻውን የማስጠንቀቂያ መልእክት እንደሚሰሙ ነው፡፡ {2SM 107.3}Amh2SM 107.3

    «በባሕርና በምድር ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፣ ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፣ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፣ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ፡- ወደ ፊት አይዘገይም» አለ (ራዕይ 10፡ 5፣ 6)፡፡ ይህ መልእከት ትንቢታዊ ወቅት ማለቁን ያስታውቃል፡፡ በ1844 ዓ.ም ጌታችንን ለማየት የጠበቁት የደረሰባቸው ተስፋ መቁረጥ የእርሱን መምጣት በታላቅ ጉጉት ለጠበቁት በርግጥም መራራ ነበር፡፡ ይህ ተስፋ መቁረጥ እንዲመጣና የሰዎች ልቦች እንዲገለጡ በጌታ ተራ ተይዞለት ነበር፡፡ {2SM 108.1}Amh2SM 108.1

    እግዚአብሔር ያላዘጋጀው አንድ ደመና እንኳን በቤተ ክርስቲያን ላይ አልወደቀም፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያላየው አንድም ኃይል የእግዚአብሔርን ሥራ ለመቃወም አልተነሳም፡፡ ሁሉም የተፈጸመው እርሱ በነቢያቱ አማካይነት እንደተነበየው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን በጨለማ ውስጥ አልተዋትም አልጣላትምም፣ ነገር ግን ሊሆን ያለውን ነገር በትንቢታዊ መግለጫዎች ገልፆአል፤ በእርሱ ፈቃድ፣ በዓለም ታሪክ ውስጥ በተመደበለት ቦታ ተግባሩን በማድረግ፣ ነቢያት አስቀድመው እንዲናገሩ መንፈስ ቅዱስ የገለጠውን ነገር አምጥቷል፡፡ ዓላማዎቹ በሙሉ ይፈጸማሉ ይጸናሉም፡፡ ሕጉ ከዙፋኑ ጋር ስለተገናኘ ሰይጣናዊ ወኪሎች ከሰብዓዊ ወኪሎች ጋር በመጣመር ሊያጠፉት አይችሉም፡፡ እውነት የሚሰጠውና የሚመራው በእግዚአብሔር ነው፤ አንዳንዴ ጥላ ያጠላበት ቢመስልም ይኖራል፣ ይከናወናልም፡፡ የክርስቶስ ወንጌል የሚታወቀው ሕግ በባሕርይ ሲገለጽ ነው፡፡ እርሱን በመቃወም የተፈጸሙት ማታለያዎች፣ ውሸትን ለመደገፍ ጥቅም ላይ የዋለው እያንዳንዱ መሳሪያ፣ በሰይጣን ወኪሎች የተዘጋጀ እያንዳንዱ ውሸት፣ በመጨረሻ ለዘላለም ይሰበሩና የእውነት አሸናፊነት በእኩለ ቀን እንደሚወጣ ፀሐይ ይሆናል፡፡ የጽድቅ ፀሐይ ፈውስ በክንፎቹ ሆኖ ያበራል፣ ምድር በሞላ በእርሱ ክብር ትሞላለች፡፡ {2SM 108.2}Amh2SM 108.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents