Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእግዚአብሔር ምሪት የተሰጠን መልእክት አሳማኝ መረጃ ያጅበዋል

    ጌታ ለሰው መልእክት ሲሰጥ መልእክቱ የሚሰጠው ከእሱ መሆኑን ሕዝቡ ከሚያውቁበት ከሆነ ነገር ጋር አብሮ ነው፡፡ ሕዝቡ መልእክት ይዞ ወደ እነሱ የሚመጣውን ሁሉ እንዲያምኑ እግዚአብሔር አይፈልግም፡፡ {2SM 71.2}Amh2SM 71.2

    እግዚአብሔር ለሕዝቡ ማስጠንቀቂያዎችን የሚልከው ሊያጠፋቸው ሳይሆን ስህተታቸውን ለማረም ነው፡፡... {2SM 71.3}Amh2SM 71.3

    አደገኛ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንኖራለን፡፡ ካለኝ ብርሃን በመነሳት ሰዎች ሊፈጽሙት ያለ አስደናቂ ሥራ እንዳላቸው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነገር ለማምጣት ሰይጣን እየሞከረ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው መልእክት ሲሰጥ፣ ያ ሰው፣ በሚያሳየው የዋህነትና ትህትና፣ እግዚአብሔር በእሱ አማካይነት እየሰራ ለመሆኑ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይኖራል ይነግሳልም፣ በፊቱ ራስን ዝቅ በማድረግ እንድንሄድ ይፈልግብናል፡፡ ይህ ኤን የተባለ ሰው በጉባኤ ፊት ራሱን በግድ እንዲያቀርብ አይፈልግም፡፡ ... {2SM 71.4}Amh2SM 71.4

    የሚያስተላልፉት መልእክት እንዳላቸው በሚናገሩ ሰዎች ምክንያት በየጊዜው ስብሰባዎቻችን መደናቀፍ የለባቸውም፡፡ ባልተፈለገ ቦታ ራሱን በግድ የሚያስገባ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እየሰራ አይደለም፡፡ በጦር ሰራዊት ውስጥ እንዳሉ ወታደሮች መሥራት አለብን፡፡ ከምድባችን ወጥተን በራሳችን መሥራት የለብንም፡፡ --Manuscript 30, 1901. {2SM 71.5}Amh2SM 71.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents