Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከዓለማዊ የንግድ ድርጅቶችና እርስበርሳቸው ከሚጋጩ ተግባራት ነጻ መሆን

    በጥብቅ መርህን የምንከተል ከሆንን መስተካከል ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አገልጋዮቻችንን በተመለከተ የተለየ መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ ሀብታሞች ለመሆን እንዲሹ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ በዓለማዊ የንግድ ድርጅቶች ውስጥ መሳተፍ ያሉአቸውን ኃይሎች ለመንፈሳዊ ነገሮች መስጠት እንዳይችሉ ስለሚያደርግ በዓለማዊ የንግድ ድርጅቶች ውስጥ መሳተፍ የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መደገፍ የሚችል በቂ ደሞዝ ማግኘት አለባቸው፡፡ በራሳቸው ቤት ላለው ቤተ ክርስቲያን ተገቢ የሆነ ትኩረት መስጠት እንዳይችሉ የሚያደርጉ እጅግ ብዙ የሆኑ ሸክሞች ሊጫኑባቸው አይገባም፡፡ አብርሃም እንዳደረገው ሁሉ ልጆቻቸው የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ እና ፍትህና ፍርድ እንዲያደርጉ ማስተማር ተግባራቸው ነው፡፡. . . .Amh2SM 187.3

    አገልጋዮችና መምህራን ችሎታቸው በሚፈቅደው መጠን ሀላፊነታቸውን እንዲወጡና ወደ ሥራቸው ያሏቸውን ከሁሉ የተሻሉ ኃይሎች እንዲያመጡ እንደሚፈልግና ባያደርጉ ደግሞ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ያስታውሱ፡፡ እግዚአብሔር ከሰጣቸው ሥራ ጋር የሚጋጩ ተግባራትን መሥራት የለባቸውም፡፡ አገልጋዮችና መምህራን ሁልጊዜ በገንዘብ ሀላፊነት ጫና ሥር ሲሆኑ፣ ወደ መድረክ ወይም ወደ መማሪያ ክፍል ደክሟቸው ወይም አእምሮአቸው ተጨንቆ እና ነርቮቻቸው ሥራ በዝቶባቸው ሲገቡ እግዚአብሔር ያቀጣጠለው ቅዱስ እሳት ሳይሆን ተራ እሳት ከማቅረብ በቀር ሌላ ምን ሊጠበቅ ይችላል? በሥራ የደከመና የተበጣጠሰ ጥረት ተናጋሪውን ከመጉዳቱም ባሻገር አድማጮችንም ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ እግዚአብሔርንና የመንፈስ ቅዱስን ቅባት ለመሻት ጊዜ አልነበረውም፡፡ ይህን የአሰራር መንገድ መቀየር የለብንምን?--Manuscript 101, 1902.Amh2SM 188.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents