Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በቀደምት ጊዜያቶች የነበረው ራስን የመካድ መንፈስ አሁን ያስፈልጋል

    መጀመሪያ ሥራውን በጀመርን ጊዜ፣ በጣት የምንቆጠር ጥቂት ሰዎች በነበርን ጊዜ፣ ራስን መካድና ራስን መስዋዕት ማድረግ ምን ማለት እንደሆነ ባወቅን ጊዜ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች መሄድ ያለባቸውን ጥቂት ወረቀቶችን፣ ጥቂት በራሪ ጽሁፎችን ለማሰራጨት በሞከርን ጊዜ የነበረው ያህል ራስን መካድ አሁንም ያስፈልጋል፡፡ ያኔ ከእኛ ጋር ከነበሩት መካክል ዛሬ ከሥራው ጋር ግንኙነት ያላቸው ጥቂቶች አሉ፡፡ ተራ የሆነ ምግብና ልብስ ለመግዛት ከሚበቃ ገቢ በስተቀር ለዓመታት ደሞዝ አልተቀበልንም፡፡ ያገለገሉ (ሰልባጅ) ልብሶችን በመልበሳችን ደስተኞች ነበርን፣ አንዳንድ ጊዜ ብርታታችንን ለማቆየት የሚበቃ ምግብ እንኳን አልነበረንም፡፡ ያለው ነገር ሁሉ በሥራ ላይ ውሎ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ባለቤቴ በሳምንት ስድስት ዶላር ማግኘት ስለጀመረ በዚያ ገቢ እንተዳደር የነበረ ሲሆን እኔ ሥራውን ከእርሱ ጋር አብሬ እሰራ ነበር፡፡ ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ይሰሩ ነበር፡፡. . . .Amh2SM 188.4

    ሥራው ስኬታማ ከሆነ በኋላ ወደ ሥራው የገቡ ሰዎች በጣም በትህትና መራመድ አለባቸው፡፡ ራስን መስዋዕት የማድረግን መንፈስ ማሳየት አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር እያለ ያለው በዚህ ቦታ ያሉት ተቋማት ወደ ፊት መቀጠል የሚችሉት ልክ መሰረቱ ሲጣል በነበረ ጊዜ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ራስን መስዋዕት በማድረግ ነው፡፡--General Conference Bulletin, March 20, 1891, p. 184.Amh2SM 189.1

    ይህ ሥራ መሰራት በሚገባው ሁኔታ ሲሰራ፣ ወደ እውነት የሚለወጡትን ለመጨመር በመለኮታዊ ቅናት ስንሰራ፣ የእውነትን መልእክት ኃይል እየተከተለው እንደሆነ ዓለም ይመለከታል፡፡ የአማኞች አንድነት የተለያየ ባሕርይ ያላቸውን ሰዎች ፍላጎታቸውን አንድ በማድረግ ወደ ፍጹም መጣጣም ማምጣት ለሚችለው የእውነት ኃይል ምስክር ይሆናል፡፡ Amh2SM 189.2

    የአማኞች ጸሎትና ስጦታዎች ልባዊ ከሆነ ራስን መስዋዕት ከማድረግ መንፈስ ጋር ተቀላቅለው ለዓለም፣ ለመላእክትና ለሰዎችም የሚታዩ አስደናቂ ነገሮች ሆነዋል፡፡ አንድ ጊዜ ከፍተኛ ደሞዝ ለማግኘት ይስገበገብ የነበረው እጅ አሁን የእግዚአብሔር ረዳት እጅ ሆኗል፡፡ አማኞችን አንድ ፍላጎት አንድ አድርጓቸዋል፣ ያውም እግዚአብሔር ከፍ ከፍ የሚደረግባቸውን ማዕከሎች የማዘጋጀት ፍላጎት ነው፡፡ ክርስቶስ በተቀደሰ አንድነትና የፍቅር ቁርኝነት ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናል፣ ይህ ቁርኝት መቋቋም የማይቻል ኃይል ያለው ቁርኝት ነው፡፡ Amh2SM 189.3

    ኢየሱስ በፍርድ ፊት ከመቅረቡ በፊት፣ ከመስቀል አንድ እርምጃ ብቻ ራቅ ብሎ ቆሞ የጸለየው ለዚህ አንድነት ነበር፡፡ እንዲህ ነበር ያለው፣ «ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ አንተ እንደላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ አንተ፣ አባት ሆይ፣ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፣ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ» (ዮሐ. 17፡ 21)፡፡ --Letter 32, 1903.Amh2SM 189.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents