Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የጸሎትና የምስጋና ጊዜ

    ችግሮችና ፈተናዎች ሲከቡን ወደ እግዚአብሔር መሸሽና ለማዳን ሃያልና ነጻ ለማውጣት ብርቱ በሆነው በመተማመን እርዳታ መጠበቅ አለብን፡፡ መቀበል ከፈለግን የእግዚአብሔርን በረከቶች መጠየቅ አለብን፡፡ ጸሎት መደረግ ያለበት እና አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው፤ ነገር ግን ምስጋናን ችላ አንልምን? በረከቶችን ሁሉ ለሚሰጠን አዘውትረን ምሥጋና ማቅረብ የለብንምን? አመስጋኝነትን ማጎልበት አለብን፡፡ በሀዘንና በመከራ ውስጥ እንኳን እያለፍን ቢሆን የእግዚአብሔርን ምህረቶች አዘውትረን ማሰብና ማሰላሰል፣ ቅዱስ ስሙንም ከፍ ከፍ ማድረግና ማክበር አለብን፡፡. . . .Amh2SM 268.2

    የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት በእኛ ላይ በዝቷል፡፡ በእርሱ የሚታመኑትን አይተዋቸውም አይጥላቸውምም፡፡ ስለ ራሳችን ፈተናዎች ጥቂት በመናገር ስለ እግዚአብሔር ምህረትና በጎነት ብዙ ብንናገር ኖሮ ራሳችንን የምናገኘው ከራሳችን ሀዘንና ግራ መጋባት በላይ ከፍ ብለን ነበር፡፡ ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ፣ በጨለማ መንገድ ውስጥ እየገባችሁ እንደሆነ ተሰምቷችሁ እንደ ባቢሎን ምርኮኞች በገናዎቻችሁን በአኻያ ዛፎች ላይ መስቀል እንዳለባችሁ እየተሰማችሁ ያላችሁ፣ ፈተናን አስደሳች ዝማሬ እናድርግ፡፡ ከፊቴ ጨለማ የሆነ ሁኔታ እየጠበቀኝ ሳለ፣ ነፍሴን የሀዘን ሸክም ተጭኗት እያለ እንዴት አድርጌ ልዘምር? ትሉ ይሆናል፡፡ ምድራዊ ሀዘን ኃይል ሁሉ ያለውን ወዳጃችሁን ኢየሱስን ቀምቶባችኋልን? ውድ ልጁን የሰጠው የእግዚአብሔር አስደናቂ ፍቅር የማያቋርጥ የምሥጋና መሪ ሀሳብ መሆን የለበትምን? ወደ ጸጋው ዙፋን ልመናችንን ስናመጣ፣ የምስጋና ዝማሬዎችን ማቅረብንም አንርሳ፡፡ «ምስጋናን የሚሰዋ ያከብረኛል» (መዝ. 50፡ 23)፡፡ አዳኛችን እስካለ ድረስ የማያቋርጥ ምስጋና እና ውዳሴ እንድናቀርብ የሚያደርግ ምክንያት አለ፡፡--The Review and Herald, Nov. 1, 1881.Amh2SM 268.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents