Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መጋቢት 20 ቀን 1891 ዓ.ም ከቀረበው ተማጽኖ የተወሰዱ ምንባቦች

    ጌታ ኢየሱስ ወደ ዓለማችን የመጣው ከሁሉም ብሔረሰቦች ወንዶችንና ሴቶችን ለማዳን ነው፡፡ ለነጮች እንደሞተ ሁሉ ለጥቁሮችም ሞቷል፡፡ ክርስቶስ ብርሃን ለመስጠት የመጣው ለመላው ዓለም ነው፡፡ በአገልግሎቱ ጅምር ላይ ተልእኮውን ተናግሯል፡- «ለድሆች የምስራች እሰብክ ዘንድ ስለ ቀባኝ የእግዚአብሔር መንፈስ በላዬ ነው፤ ልባቸው የተሰበረባቸውን እፈውስ ዘንድ፣ በግዞት ላሉት ነጻ መውጣትን እሰብክ ዘንድ፣ እና የእውራንን ዓይን እገልጥ ዘንድ፣ የተቀጠቀጡትን ነጻ አወጣ ዘንድ፣ የጌታን ተቀባይነት ያለው ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል፡፡». . .Amh2SM 487.3

    ጳውሎስ «ማን ነው የሚለያየን?” ይላል፡፡ የነጭ አምላክ የጥቁርም አምላክ ስለሆነ ከሁሉ ላነሱት ልጆቹ ያለው ፍቅር እናት ለምትወደው ልጇ ካላት ፍቅር እንደሚበልጥ ጌታ ይናገራል፡፡. . . .Amh2SM 487.4

    የእግዚአብሔር ዓይኖች በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ናቸው፤ ሌሎችን ለመርዳት የበለጠ ከባድ ሸክም ለመሸከም ለተጠሩት ካለው ገርነት ካለበት ርኅራኄ በስተቀር ሁላቸውንም ይወዳል፣ በነጭና በጥቁር መካከልም ምንም ዓይነት ልዩነት አያደርግም፡፡ እግዚአብሔርን የሚወዱና ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው አድርገው የሚያምኑ፣ በመንገዳቸው ላይ የተቀመጡትን ፈተናዎችና ችግሮች እየተጋፈጡ ሳሉ፣ በላይ ያለው እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንደሚመለከታቸው በመቁጠር እና ዓለም ለመስጠት ችላ ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እሱ በተሻለ ሁኔታ እንደሚክሳቸው በመቁጠር ደስ ባለው መንፈስ ሕይወታቸውን እንዳለ መቀበል አለባቸው፡፡. . . .Amh2SM 487.5

    ኃጢአተኛ ሲለወጥ እና መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል ይህ ድርጊቱ የእግዚአብሔር ልጅ ያደርገውና የዳኑት መላእክት ሰራዊት ማሕበርተኛ ያደርገዋል፡፡ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ ይሆናል፡፡ ከሰብአዊ ቤተሰብ ማናቸውም ቢሆኑ ራሳቸውን ለክርስቶስ ቢሰጡ፣ እውነትን ቢሰሙና ቢታዘዙት፣ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ይሆናሉ፡፡ ክርስቶስ ላልተማሩት ሆነ ለጠቢባን፣ ለሃብታሞችና ለደሃዎች፣ ለአህዛብና ለባርያ፣ ለነጭና ለጥቁር፣ የነፍሳቸውን የመቤዠት ዋጋ ከፍሏል፡፡ በእርሱ ሲያምኑ የሚያነጻው ደም በለያቸው ይደረግላቸዋል፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የጥቁር ሰው ስም በነጭ ሰው ስም አጠገብ ተጽፏል፡፡ ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው፡፡ ልደት፣ የኑሮ ደረጃ፣ ዜግነት ወይም ቀለም ሰዎችን ከፍ ወይም ዝቅ አያደርግም፡፡ የሰውን ማንነት የሚወስነው ባሕርይ ነው፡፡ ቀይ ሰው፣ ቻይናዊ ወይም አፍሪካዊ በመታዘዝና በእምነት ልቡን ለእግዚአብሔር ከሰጠ እግዚአብሔር በቆዳ ቀለሙ ምክንያት ምንም ልዩነት ሳያደርግበት ይወደዋል፡፡ ውድ ወንድሜ ብሎ ይጠራዋል፡፡ . . . .Amh2SM 488.1

    ሰዎች በውርስ ያገኟቸውም ሆነ እራሳቸው ያጎለበቷቸው ምክንያት የለሽ ጥላቻዎች አሏቸው፣ ነገር ግን የኢየሱስ ፍቅር ልብን ሲሞላ እና በክርስቶስ አንድ ሲሆኑ እርሱ የነበረው መንፈስ እነርሱም ይኖራቸዋል፡፡ ጥቁር ወንድም በአጠገባቸው ቢቀመጥ አይከፋቸውም ወይም አይንቁትም፡፡ እየተጓዙ ያሉት ወደ አንድ ሰማይ ስለሆነ በእግዚአብሔር መንግሥት እንጄራን ለመብላት በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ይቀመጣሉ፡፡ ኢየሱስ በልባችን ቢኖር ኖሮ ያው አዳኝ በልቡ እየኖረበት ያለውን ጥቁር ሰው መናቅ አንችልም ነበር፡፡ --Manuscript 6, 1891. Published in The Southern Work, 1966 ed., pp. 9-14Amh2SM 488.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents