Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወደ ስህተት የተመራ ልጅ ራዕዮች

    [በምዕራፍ 7 ላይ ስለተጠቀሰው ሚስተር ጋርማየር የተሰጡት ወይም ከእሱ ጋር የተፈጸሙ ግንኙነቶች የተለየ ብርሃን አለን ከሚሉ ሰዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት ሊረዱ የሚችሉ ምክሮች እና መረጃ ናቸው፡፡… አሰባሳቢዎች] Amh2SM 72.3

    በሚስተር [ጄ. ኤም] ጋርማየር ወይንም በሥራዎቹ ላይ ትንሽ እምነት እንኳን እንደሌለኝ እንድናገር ተገድጃለሁ፡፡ ባለፈው የመከር ወቅት በጃክሰን በነበረን ስብሰባ ጊዜ የወጣው መጽሔት የህዝባችን አነስተኛ ፈቃድ እንኳን አልነበረውም፡፡ የሪቪውና ሄራልድ ዝርዝርን በመስረቅ የተሰራጨ ነው፡፡ {2SM 72.3}Amh2SM 72.4

    የሚስተር ጋርማየር ሴት ልጅ ራዕይ እንዳላት ትናገራለች፣ ወይም ራዕይ እንዳላት እሱ ይናገርላታል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ማህተም ያላረፈባቸው ናቸው፡፡ በልምምዳችን ውስጥ ካጋጠሙን በርካታ የዚህ ዓይነት ነገሮች ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ አለው--የሰይጣን ማታለያ ነው፡፡ {2SM 73.1}Amh2SM 73.1

    በጃክሰን በነበረን ስብሰባ ላይ እነዚህ ጥራዝነጠቅ ቡድኖች የነፍሳት ጠላትን ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን በግልጽ ተናግሬያለሁ፤ በጨለማ ውስጥ ነበሩ፡፡ የምህረት በር በጥቅምት 1884 ዓ.ም እንደሚዘጋ የሚገልጽ ታላቅ ብርሃን እንዳላቸው ተናገሩ፡፡ {2SM 73.2}Amh2SM 73.2

    በእግዚአብሔር በተሰጠ መልእክት ውስጥ ከ1844 ጀምሮ የተወሰነ ጊዜ እንደማይኖር ሊያሳየኝ ጌታ እንደወደደ እዚያ በሕዝብ ፊት ተናግሬያለሁ፤ እነዚህ አራት ወይም አምስት ሰዎች በታላቅ ጉጉት ተቀባይነት እንዲያገኝ ሀሳብ እያቀረቡ ያሉት ነገር መናፍቅነት ነው፡፡ የዚህች ምስኪን ልጅ ራዕዮች ከእግዚአብሔር አልነበሩም፡፡ ይህ ብርሃን ከሰማይ አልመጣም፡፡ ጊዜው አጭር ነበር፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነበር፡፡ ሰዎች በእግዚአብሔር ማህተም እንዲታተሙ ለማዘጋጀት ታላቅ ሥራ ሊሰራ ነበር፡፡ -An Exposure of Fanaticism and Wickedness (Pamphlet), pp. 9, 10 (1885). {2SM 73.3}Amh2SM 73.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents