Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ተቋማትን ለመገንባት የገጠር ቦታዎችን መምረጥ

    አሁንም እየተሰጠ ያለው መመሪያ «ከትልልቅ ከተማዎች ውጡ፡፡ የጤና ተቋሞቻችሁን፣ ትምህርት ቤቶቻችሁን እና ቢሮዎቻችሁን ሕዝብ በብዛት ካለባቸው ማዕከሎች አርቃችሁ አቋቁሙ» የሚል ነው፡፡ አሁን ብዙዎች በከተማዎች ውስጥ ለመቅረት ይማጸናሉ፣ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ክፉን ማየትንና መስማትን የሚጠሉ ሰዎች ሁሉ መኖሪያቸውን ወደ ገጠር የሚያንቀሳቅሱበት ጊዜ ይመጣል፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የከተማዎች ከባቢ አየር እንዳለ የተበከለ እስኪመስል ድረስ ክፋትና ሙስና ስለሚጨምር ነው፡፡ Letter 26, 1907.Amh2SM 357.1

    ትምህርት ቤቶቻችን፣ የማተሚያ ቤቶቻችን እና የጤና ተቋሞቻችን ወጣቶች እውነት ምን እንደሆነ መማር በሚችሉባቸው ከከተማ ወጣ ባሉ ቦታዎች እንዲቋቋሙ እግዚአብሔር ተከታታይ ማስጠንቀቂያዎችን ልኳል፡፡ ማንም ቢሆን ትላልቅ የንግድ ፍላጎቶችን በከተማዎች ለማቋቋም ድጋፍ እንዲሆኑለት ምስክሮችን ለመጠቀም አይሞክር፡፡ በዚህ ርዕስ ላይ የተሰጠውን ብርሃን ውጤት አልባ አታድርጉ፡፡Amh2SM 357.2

    አገልጋዮቹ እንዲሰሩ ጌታ እየመራ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቃወም ሰዎች ስህተት የሆኑ ነገሮችን እየተናገሩ ይነሳሉ፡፡ ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች መንስኤውንና ውጤቱን አገናዝበው መልስ የሚሰጡበት ጊዜ ነው፡፡ ታላላቅ የንግድ ተቋሞችን በከተሞች ውስጥ ለማቋቋም ጊዜው እጅግ ረፍዷል፤ ወጣት ወንዶችንና ሴቶችን ከገጠር ወደ ከተማ ለመጥራት ጊዜው በጣም አልፏል፡፡ ከእኛ እምነት ለሆኑ ሰዎች በከተሞች ውስጥ መቆየትን እጅግ ከባድ የሚያደርጉ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ የንግድ ተቋማትን በከተሞች ለማቋቋም ገንዘብን ወጪ ማድረግ ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡ Maniscript 76, 1905.Amh2SM 357.3