Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 5

    በዚህ በተበላሸ ዘመን ልጆች ደካማ የሆነ የሰውነት አቋም ይዘው ይወለዳሉ፡፡ ወላጆች በሕጻናትና በወጣቶች መካከል እየተከሰተ ያለውን ታላቅ የሟቾች ቁጥር በመመልከት እየተደነቁ «ድሮ እንዲህ አልነበረም» ይላሉ፡፡ ልጆች ዛሬ በሚሰጣቸው እንክብካቤ ባያድጉም ያኔ እጅግ ጤናማና ብርቱ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ዛሬ ብዙ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሳለ ደካማ ሆነው ያድጋሉ፣ ይጠወልጉና ይሞታሉ፡፡ ከወላጆች መጥፎ ልማዶች የተነሳ በሽታና የአእምሮ ደካማነት ወደ ልጆቻቸው ተላልፏል፡፡ {2SM 465.1}Amh2SM 465.1

    ከተወለዱ በኋላ ለተፈጥሮ ሕጎቻቸው ትኩረት ካለመስጠት የተነሳ ግድ የለሽ በመሆን ሁኔታቸው የበለጠውን የከፋ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ተገቢ የሆነ አያያዝ የአካል ጤንነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሽላል፡፡ ሕጻናት ልጆቻቸው ከእነርሱ የወረሱትን መጥፎ ውርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁኔታውን ለማሻሻል ትክክለኛውን መንገድ አይከተሉም፡፡ ልጆቻቸውን በተመለከተ የሚከተሉአቸው የስህተት መንገዶች ለሕይወት ያላቸውን አያያዝ በመቀነስ ያለ ዕድሜ እንዲሞቱ ያዘጋጃቸዋል፡፡ እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የፍቅር እጦት የላቸውም፣ ነገር ግን ፍቅራቸው በተሳሳተ ሁኔታ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ እናት በልጇ አያያዝ ላይ የምትፈጽመው አንድ ትልቅ ስህተት ልጁን ጠንካራ እንዲሆን የሚያደርገውን ንጹህ አየር መንፈግ ነው፡፡ አራስ ልጆች በሚተኙበት ጊዜ ራሳቸውን መሸፈን ብዙ እናቶች የሚያደርጉት ነገር ነው፡፡ ይህ የሚደረገው ደግሞ ሞቃታማ በሆነ እና እንደሚገባው በቂ የአየር ዝውውር በሌለበት ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ይህ ብቻውን የልብንና የሳንባዎችን ተግባር ለማድከም እና መላውን ሰውነት ለመጉዳት በቂ ነው፡፡ አራስ ሕጻንን ከንፋስ ሽውታ ወይም ከማንኛውም ድንገተኛና ከመጠን በላይ ከሆነ ለውጥ መከላከል ተገቢ ቢሆንም ልጁ ንጹህና ብርታት የሚሰጥ አየርን መተንፈስ እንዲችል የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለሕጻን እንክብካቤ በሚደረግበት ቦታ ወይም በልጁ ዙሪያ ምንም ዓይነት ደስ የማይል ሽታ መኖር የለበትም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ካደጉ ልጆች ይልቅ ደካማ ለሆነ አራስ ልጅ የበለጠ አደገኛ ናቸው፡፡ {2SM 465.2}Amh2SM 465.2

    እናቶች ልጆቻቸውን ሲያለብሱ ጤናን ከግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ ፋሽንን ባገናዘበ መልኩ የማድረግ ልምድ ሲከተሉ ነበር፡፡ የህጻኑ ውጫዊ ልብስ ሲዘጋጅ በአጠቃላይ ትኩረት የተሰጠው ከምቾት ይልቅ ለቁንጅና ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የባከነው የትንሹን እንግዳ ልብስ ቆንጆ ለማድረግ ሲባል አስፈላጊ ባልሆነ ጌጠኛ የጥልፍ ሥራ ላይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እናት ይህን ሥራ የምትሰራው የራሷንና የልጇን ጤና አደጋ ላይ በመጣል ነው፡፡ አስደሳች የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ በሚገባት ሰዓት ዓይኖቿንና ነርቮቿን ክፉኛ የሚይዛቸውን ሥራ ጎብጣ ትሰራላች፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እናት ለራሷና ለልጇ ጥቅም ሲባል የራሷን ብርታት እንድትንከባከብ ስላለባት ግዴታ እንድታውቅ ማነሳሳት ከባድ ነው፡፡ {2SM 465.3}Amh2SM 465.3

    ታይታና ፋሽን ብዙ የአሜሪካ ሴቶች ልጆቻቸውን እየሰውበት ያሉበት የአጋንንት መሰዊያ ነው፡፡ ጤና ዋጋ የሚሰጠው ከሆነ እናት ለመስራት ሳምንታትን የፈጀችባቸውን ፋሽንን የተከተሉ ግን ሙሉ በሙሉ የማይጠቅሙ ልብሶችን በትንሽ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ታለብሳለች፡፡ ልብሶቹ ከሚገባ በላይ ረዥም ስለሆኑ በሕጻኑ ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ አካሉ ወይም ወገቡ የልብን እና የሳንባዎችን ነጻ ተግባር በሚከለክል ጥብቅ ጥምጥም ይታጠቃል፡፡ ከልብሳቸው ርዝመት የተነሳ ሕጻናቱ ደግሞ አስፈላጊ ያልሆነ ክብደትን ለመሸከም ተገደዋል፡፡ እንደዚህ ለብሰው ጡንቻዎቻቸውን እና እጅና እግሮቻቸውን እንደልብ አይጠቀሙም፡፡ {2SM 466.1}Amh2SM 466.1

    እናቶች ልጆቻቸው በጥብቅ መታጠቂያ ካልታጠቁ እንዳይሰባበሩ ወይም እንዳይጎብጡ የፈሩ ይመስል ትንንሽ ልጆቻቸው ቅርጻቸውን እንዲጠብቁ በማለት አካላቸውን ማጥበቅ አስፈላጊ እንደሆነ አስበዋል፡፡ ተፈጥሮ ሥራዋን እንድትሰራ ነጻነት ስለተሰጣት ፍጥረተ-እንስሳት ቅርጸ-ቢስ ይሆናሉን? ትንንሽ ጠቦቶች ቅርጽ እንዲኖራቸው ዙሪያቸው በመቀነት ስላልተጠመጠመ ቅርጸ-ቢስ ይሆናሉን? ግሩምና ድንቅ ሆነው ተሰርተዋል፡፡ የሰው ሕጻናት ከፈጣሪ ሥራ ሁሉ እጅግ ፍጹም ሆነው ግን እጅግ ራሳቸውን መርዳት የማይችሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ እናቶቻቸው በአካል፣ በአእምሮና በግብረገብ ጤናማ አድርገው እንዲያሳድጓቸው ስለ አካል ሕጎች ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እናቶች ሆይ፣ ምንም ዓይነት ጥምጥም ወይም መቀነት ሊያስተካክል የማይችለውን ቅርጽ ለልጆቻችሁ ተፈጥሮ ሰጥታቸዋለች፡፡ እግዚአብሔር ሕጻናቱን እናንተ እንድትጠነቀቁላቸው ከመስጠቱ በፊት ሰውነታቸውን መሸከም እንዲችሉና በውስጥ ያለውን የተፈጥሮ ደቃቅ ፋብሪካ እንዲጠብቁ አጥንቶችንና ጡንቻዎችን ሰጥቷቸዋል፡፡ {2SM 466.2}Amh2SM 466.2

    የህጻን ልብስ መሰፋት ያለበት ጠግቦ ከበላ በኋላ እንኳን ሰውነቱን በፍጹም እንዳያጠብቅ ተደርጎ ነው፡፡ እንግዶች እንዲያደንቋቸው በማለት ሕጻናትን ፋሽንን ተከትሎ ማልበስ ጎጂ ነው፡፡ ልብሳቸው የተሰራው ለልጅ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ምቾት እንደማይሰጥ ሆኖ ሲሆን የበለጠውን ምቾት እንዳይኖረው የሚያደርገው ደግሞ በሁሉም እየታሸ ከአንዱ ወደ አንዱ መተላለፉ ነው፡፡ እስከ አሁን ከተጠቀሱት ሁሉ የሚበልጥ ሌላ ክፉ ነገር አለ፡፡ ሕጻኑ ከብዙ ትንፋሾች የተነሳ ለተበላሸ አየር ተጋልጧል፤ አንዳንዶቹ ትንፋሾች በእድሜ ለበሰሉ ሰዎች ጠንካራ ሳንባዎች እንኳን በጣም የሚያስጠሉና ጎጂ ናቸው፡፡ የህጻኑ ሳንባ በትምባሆ ተጠቃሚዎች ትንፋሽ በተበከለ ክፍል ውስጥ ያለውን የተመረዘ አየር በመተንፈስ ይሰቃያል፣ ይታመማልም፡፡ ብዙ ሕጻናት ትምባሆ አጫሽ ከሆኑ አባቶቻቸው ጋር በአልጋዎች ውስጥ በመተኛት መዳን እስከማይችሉ ድረስ ተመርዘዋል፡፡ ከሳንባ በሚወጣና በቆዳ ቀዳዳዎች አማካይነት የሚወጣውን መርዘኛ የሆነ የትምባሆ ጭስ በመተንፈስ የሕጻኑ ሰውነት በመርዝ ተሞልቷል፡፡ በአንዳንዶች ላይ እንደማይፈጥን መርዝ ሆኖ አእምሮን፣ ልብን፣ ጉበትን፣ እና ሳንባዎችን በመጉዳቱ እነዚህ የአካል ክፍሎች መንምነው በቀስታ ሲጠፉ በሌሎች ላይ ደግሞ ቀጥተኛ የሆነ ውጤት በማሳየት የጡንቻ መኮማተርን፣ የሚጥል በሽታን፣ የአካል መስለልን፣ የእጅ መንዘፍዘፍ በሽታንና ድንገተኛ ሞትን ያስከትላል፡፡ የእነዚህ ልጆች ሞት የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆንም ሀዘን የደረሰባቸው ወላጆች የሚወዱአቸውን ልጆቻቸውን በማጣታቸው እንዲህ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ መከራ ባመጣባቸው ምስጢራዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይደነቃሉ፡፡ ቆሻሻ ለሆነ የትምባሆ ፍላጎት የሰማዕትነትን ሞት ሞተዋል፡፡ ወላጆቻቸው ካለማወቃቸው የተነሳ ልጆቻቸውን በሚያስጠላ መርዝ ይገድሏቸዋል፡፡ የትምባሆ ባርያ የሆነ ሰው ከሳንባዎቹ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እያንዳንዱ ትንፋሽ በዙሪያው ያለውን አየር ይመርዛል፡፡ ሕጻናት የነርቭ ሥርዓትን የሚረብሽ ተጽእኖ ካለው ከማንኛውም ነገር ነጻ ሆነው መጠበቅ አለባቸው፡፡ ሲራመዱም ሆነ ሲተኙ፣ ቀንም ሆነ ማታ ከእያንዳንዱ የመርዝ ብክለት ነጻ የሆነ ንጹህ፣ ጽዱ፣ እና ጤናማ አየር መተንፈስ አለባቸው፡፡ {2SM 466.3}Amh2SM 466.3

    በሕጻናትና በወጣቶች መካከል ሌላኛው ሞትን የሚያስከትል ትልቅ ነገር ክንዶቻቸውንና ትካሻቸውን እራቁት የማድረግ ባሕል ነው፡፡ ይህ ፋሽን ከመጠን በላይ ሊኮነን አይችልም፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ዋጋ አስከፍሏል፡፡ እጆችንና እግሮችን ሲታጠቡ አየር በብብቶች አከባቢ በመዘዋወር ዋና ለሆኑ የአካል ክፍሎች ቅርብ የሆኑትን እነዚህን በቀላሉ የሚሰማቸውን ክፍሎች በማቀዝቀዝ ጤናማ የሆነ የደም ዝውውርን ይገድባል፣ በተለይ የሳንባዎችን እና የአእምሮ በሽታን ያመጣል፡፡ ከማይጠቅም የእንግዶች ሙገሳና አድናቆት ይልቅ ለልጆቻቸው ጤንነት የበለጠ ዋጋ የሚሰጡ ሰዎች ለጋ የሆኑ ሕጻናትን ትከሻዎችና ክንዶች ያለብሳሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የእናት ትኩረት ቡናማ ወደሆኑ የልጇ ክንዶችና እጆት እንድትመለከት ተደርጎ ነበር፡፡ ይህን ጤንነትንና ሕይወትን ስለሚያጠፋ ልምምድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ የምትመልሰው መልስ «ሁልጊዜ ልጆቼን የማለብሰው እንዲህ ነው፡፡ ይለምዱታል፡፡ የህጻነት ክንዶች ተሸፍነው ማየት አልችልም፡፡ ጊዜው ያለፈበት ፋሽን ይመስላል” የሚል ነበር፡፡ እነዚህ እናቶች ለራሳቸው ለመልበስ የማይደፍሩትን ዓይነት አለባበስ በቀላሉ ሊጎዱ ለሚችሉ ሕጻናት ያለብሳሉ፡፡ የራሳቸው ክንዶች ካልተሸፈኑ ከቅዝቃዜ የተነሳ እንደሚንቀጠቀጡ ያውቃሉ፡፡ እነዚህ በለጋ እድሜ ያሉ ሕጻናት ጉዳት ሳይደርስባቸው ይህን የመጠንከር ሂደት መሸከም ይችላሉን? አንዳንድ ልጆች ከመወለዳቸው ጀምሮ ጠንካራ አቋም ስላላቸው የህይወት ዋጋ ሳያስከፍላቸው እንደዚህ ዓይነቱን አግባብነት የሌለውን አያያዝ ይቋቋማሉ፡፡ ነገር ግን ከሕይወት መቀመጫ በርቀት ላይ ከመቀመጣቸው የተነሳ ከደረትና ከሳንባዎች የበለጠ ልብስ የሚያስፈልጋቸው ክንዶች እራቁታቸውን ሆነው ሳለ አካልን በብዙ ልብስ ከመጠን በላይ በመጠቅለል በሺሆች የሚቆጠሩ ተሰውተዋል፣ በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ደግሞ አጭር እና የማይጠቅም ኑሮ እንዲኖሩ መሠረት ተጥሏል፡፡ እናቶች በዚህ መልክ ልጆቻቸውን እየያዙ ሰላማዊና ጤናማ ሕጻናት እንዲኖሩአቸው ይጠብቃሉን? {2SM 467.1}Amh2SM 467.1

    እጆችና እግሮች በሚቀዘቅዙበት ጊዜ ደም ከእነዚህ ክፍሎች ወደ ልብና ወደ አንጎል ይደርሳል፡፡ የደም ዝውውር ስለሚታገድ ተግባሩን በጥሩ ሁኔታ የሚያከናውን የተፈጥሮ ፋብሪካ ተጣጥሞ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ የህጻኑ አካል በመረበሽ ተገቢ ባልሆነ መልክ በመያዙ እየደረሰበት ላለው ሥቃይ መጮህና ማዘን ይጀምራል፡፡ ምግብ የህጻኑን ሥቃይ ብቻ የሚጨምር ቢሆንም እናት የተራበ መስሏት ትመግበዋለች፡፡ ጠባብ ልብስና ጫና የበዛበት ጨጓራ አይስማሙም፡፡ ለመተንፈስ ቦታ የለም፡፡ ለመተንፈስ ሊያለቅስ፣ ሊታገልና ሊያለከልክ ይችላል፣ እናት ይህ እንዲሆን ያደረገውን ነገር ምን እንደሆነ ማመን አለባት፡፡ የጉዳዩን ባሕርይ ካስተዋለች፣ ቢያንስ ጥብቅ የሆነውን ጥምጥም በማስወገድ፣ እየተሰቃየ ያለውን ሕጻን ወዲያውኑ ከሥቃዩ ማሳረፍ ትችላለች፡፡ በቆይታ ትባንንና ልጇ እውነትም እንደታመመ በማሰብ ሐኪም ትጠራለች፡፡ ሐኪሙ ሕጻኑን ለጥቂት ደቂቃዎች በሀዘኔታ ይመለከተውና መርዘኛ የሆኑ መድሃኒቶችን፣ ወይም ሕመምን የሚያስታግስ አነቃቂ ተብሎ የሚጠራውን ነገር ያዛል፡፡ ለተሰጧት መመሪያዎች ታማኝ የሆነችው እናት እነዚህን መድሃኒቶች በደል በደረሰበት ሕጻን ጎሮሮ ውስጥ ታንቆረቁራለች፡፡ በእርግጥ አስቀድሞ ካልታመመ ከዚህ ሂደት በኋላ ግን ይታመማል፡፡ አሁን ከበሽታዎች ሁሉ በላይ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ እና መድሃኒት በሚያስከትለው የማይድን በሽታ ይሰቃያል፡፡ ቢያገግም እንኳን ይብዛም ይነስም መርዘኛ መድሃኒት ያስከተላቸውን ውጤቶች መሸከም አለበት፡፡ ከዚህ የተነሳ ለጡንቻዎች መኮማተር፣ ለልብ በሽታ፣ በአእምሮ ውስጥ ውኃ መቋጠር ወይም ለሳንባ ነቀርሳ ይጋለጣል፡፡ አንዳንድ ሕጻናት መርዘኛ የሆኑ መድሃኒቶችን በአነስተኛ መጠን እንኳን ለመሸከም የሚችል ጥንካሬ የላቸውም፡፡ ተፈጥሮ በውስጧ ጣልቃ የገባውን ነገር ለመጋፈጥ ስታገግም፣ የለጋ ሕጻን ንቁ ኃይሎች እጅግ ሥራ ይበዛባቸውና ሞት ክስተቱን ወደ ፍጻሜ ያመጣዋል፡፡ {2SM 468.1}Amh2SM 468.1

    በዚህ ዘመን እናት ለመሞት እያጣጣረ ያለውን ደካማ ልጇን ጩኸት እየሰማች፣ ልቧ በሀዘን ተጎድቶ፣ በመሰቃየት ላይ ባለው የሕጻን አልጋ ዙሪያ ወዲያና ወዲህ ስትል ማየት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ምንም ክፋት የሌለበትን ልጇን እግዚአብሔር ማሰቃየቱ ለእሷ ምስጢራዊ ነገር ይመስላል፡፡ ያንን አሳዛኝ ክስተት ያመጣው የራሷ የተሳሳተ እርምጃ እንደሆነ አታስብም፡፡ የሕጻኗን ጤና የጎዳችው መርዝ እንደሰጠች ነው፡፡ በሽታ ያለ መንስኤ በፍጹም አይመጣም፡፡ መጀመሪያ መንገድ ይዘጋጅና የጤና ሕጎችን ችላ በማለት በሽታ ይጋበዛል፡፡ እግዚአብሔር በትንንሽ ልጆች ሥቃይና ሞት አይደሰትም፡፡ እግዚአብሔር ለወላጆች ልጆችን የሰጠው በአካል፣ በአእምሮ እና በግብረገብ እንዲያስተምሯቸውና ለዚህ ምድርና በመጨረሻም ለሰማይ ጠቃሚነት እንዲያሰለጥኗቸው ነው፡፡ {2SM 468.2}Amh2SM 468.2

    እናት የልጇን አካላዊ ፍላጎት የማታውቅ ከሆነ እና ከዚህ የተነሳ ልጇ ከታመመባት እሷ እንዲታመም ያደረገችውን ለመገልበጥ እግዚአብሔር ተኣምር ይሰራል ብላ መጠበቅ የለባትም፡፡ መኖር ይችሉ የነበሩ በሺሆች የሚቆጠሩ ሕጻናት ሞተዋል፡፡ እነዚህ ልጆች የሚመገቡት ምግብ፣ የሚለብሱት ልብስ እና የሚተነፍሱት አየር ጤንነትንና ሕይወትን ከማቆየት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወላጆች ካለማወቃቸው የተነሳ የሰማዕትነት ሞት እየሞቱ ናቸው፡፡ ባለፉት ዘመናት የነበሩት እናቶች የልጆቻቸው ሐኪም መሆን ነበረባቸው፡፡ የልጇን ውጫዊ ልብስ ለማስዋብ መስዋዕት ያደረገችውን ሰዓት ለከበረ ዓለማ ማዋል ትችል ነበር፡፡ ያውም ስለ ራሷና ስለ ልጇ አካላዊ ፍላጎት አእምሮዋን ማስተማር ነበር፡፡ እሷ ከምትከተለው መንገድ የተነሳ ትውልዶች ይጎዱ ይሆን ወይስ ይጠቀሙ ይሆን? የሚለውን አመለካከት ይዛ ስለ ልጆቿ አስተዳደግ መከተል የምትችለውን የተሻለ መንገድ በተመለከተ በአእምሮዋ ውስጥ ጠቃሚ እውቀትን ማካበት ነበረባት፡፡ {2SM 469.1}Amh2SM 469.1

    አስቸጋሪ እና የሚጨነቁ ሕጻናት ያሏቸው እናቶች ምቾት እንዲያጡ ያደረጋቸው ነገር ምን እንደሆነ ማጥናት አለባቸው፡፡ ይህን በማድረጋቸው በአያያዛቸው ላይ የሆነ ስህተት እንዳለ ያያሉ፡፡ ልጇ እግሮቹንና እጆቹን መጠቀም እንዲችል የሚያጠብቁ ልብሶችን በማውለቅና በሚገባ ሁኔታ ልል እና አጠር ያሉ ልብሶችን እንዲለብስ በማድረግ ሕመሙ ሊድን ሲችል ብዙ ጊዜ እናት በልጇ ላይ በሚታዩ የህመም ምልክቶች ትደናገጥና በችኮላ ሐኪም ትጠራለች፡፡ እናቶች መንስኤንና ውጤቱን ማጥናት አለባቸው፡፡ ልጁ ቅዝቃዜ አግኝቶት ከሆነ ይህ የሆነበት ምክንያት በአጠቃላይ ከእናት የተሳሳተ አያያዝ ነው፡፡ በሚተኛበት ጊዜ ራሱንና አካሉን ብትሸፍን ንጹህና አስፈላጊ የሆነ አየር ከማጣቱ የተነሳ ለመተንፈስ በሚያደርገው ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልበዋል፡፡ ከአንሶላ ስታወጣው ቅዝቃዜ እንደሚያገኘው እሙን ነው፡፡ የክንዶቹ እራቁት መሆን ሕጻኑን ለማያቋርጥ ቅዝቃዜ እና ለሳንባዎችና ለአእምሮ መጨናነቅ ያጋልጡታል፡፡ እነዚህ መጋለጦች ሕጻኑ ታማሚና እድገቱ የተገታ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ {2SM 469.2}Amh2SM 469.2

    ወላጆች ለልጆቻቸው አካላዊ ጤንነት በከፍተኛ ደረጃ ሀላፊነት አለባቸው፡፡ በአራስ ቤት እያሉ ይደርስባቸው ከነበረው ተገቢ ያልሆነ አያያዝ የተረፉት ሕጻናት በልጅነት ዕድሜያቸው ከአደጋ ነጻ አይደሉም፡፡ እነርሱን በተመለከተ አሁንም ወላጆቻቸው የተሳሳተ መንገድ ይከተላሉ፡፡ እጆቻቸውና እግሮቻቸው እራቁት ይተዋሉ፡፡ ከጤንነት ይልቅ ለፋሽን ዋጋ የሚሰጡ ሰዎች በልጆቻቸው ላይ ቀለበቶች ያስቀምጣሉ፡፡ ቀለበቶች ምቹ ያልሆኑ፣ መጠናቸውን ያልጠበቁና ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ናቸው፡፡ ልብስ ወደ ሰውነት እንዳይቀርብ ይከለክላሉ፡፡ ያኔ እናቶች የእግራቸውን የላይኛውን ክፍል ወደ ጉልበት አከባቢ በሚደርስ ከቀጭን የጥጥ ጨርቅ በተሰራ ሻሽ መሰል የውስጥ- ልብስ ይሸፍኑ ነበር፡፡ የእግሮቻቸው የታችኛው ክፍል ሙቀት በሚሰጥ ለስላለሳ ጨርቅ ወይም በጥጥ የተሸፈነ ሲሆን እግሮቻቸው ስስ ሶል ባላቸው ገምባሌ ቦቲዎች ይሸፈኑ ነበር፡፡ ልብሶቻቸው ከገላ ጋር እንዳይገናኙ በቀለበቶች ስለተያዙ ከልብሶቻቸው በቂ ሙቀት ማግኘት ስለማይችሉ እግሮቻቸው ያለማቋረጥ በቀዝቃዛ አየር ይታጠባሉ፡፡ ጫፍ ላይ ያሉ የአካል ክፍሎች ይቀዘቅዛሉ፣ ልብ ወደ እነዚህ ወደ ቀዘቀዙና ጫፍ ላይ ወዳሉ ክፍሎች ደም ለመግፋት እጥፍ ሥራ ተጥሎበታል፡፡ ደም በሰውነት ውስጥ ዑደቱን ጨርሶ ወደ ልብ ሲመለስ ከልብ ሲወጣ የነበረው ብርታት ያለበት ሞቃት የሆነ ፍሰት አይኖረውም፡፡ በእግሮች ውስጥ ሲያልፍ ሳለ በመንገድ ላይ ቀዝቅዟል፡፡ ልብ ከመጠን በላይ በሆነ ሥራ እና ደካማ በሆነ የደም ዝውውር ደክሞ ሳለ ከመጀመሪያ የሚበልጥ ጉልበት የሚጠይቅ ሥራ፣ እንደ ሌሎቹ የአካል ክፍሎች ጤናማ በሆነ ሁኔታ በፍጹም ሞቀው ወደማያውቁ በሰውነት ጫፍ ላይ ወዳሉ የአካል ክፍሎች የመርጨት ሥራ ለመስራት ተገዷል፡፡ ልብ ጥረቱ ሳይሳካለት ይቀርና እግሮች እንደተለመደው ይቀዘቅዛሉ፤ በእነዚህ ጫፍ ላይ ባሉ የአካል ክፍሎች ውስጥ ቀዝቅዞ ያለው ደም ወደ ሳንባዎችና ወደ አእምሮ ተመልሶ ስለሚላክ የሳንባዎችና የአእምሮ መጨናነቅ እና መመረዝ ይከሰታል፡፡ {2SM 469.3}Amh2SM 469.3

    ልጆቻቸው ለመሰቃየት ለተገደዱባቸው በሽታዎች እግዚአብሔር እናቶችን ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡ እናቶች በፋሽን መስገጃ ቦታ እየሰገዱ የልጆቻቸውን ጤንነትና ሕይወት መስዋዕት ያደርጋሉ፡፡ ብዙ እናቶች በዚህ መልክ ልጆቻቸውን ማልበስ ለሚያስከትለው ውጤት እውቀት የላቸውም፡፡ ነገር ግን ብዙዎች አደጋ ውስጥ ያሉት ይህን ያህል እውቀቱ ስለሌላቸው ነው ወይ? የማገናዘብ ኃይል ላላችሁ ለእናንተ አለማወቅ በቂ ምክንያት ነው ወይ? ፈቃደኛ ከሆናችሁ ራሳችሁን ማሳወቅና ልጆቻችሁን ጤናማ በሆነ ሁኔታ ማልበስ ትችላላችሁ፡፡ {2SM 470.1}Amh2SM 470.1

    ወላጆች ልጆቻቸውን ካባ እና የፀጉር ልብስ እያለበሱአቸውና ያን ያህል አስፈላጊ ባልሆነበት ቦታ እነዚህን ልብሶች እየጫኑ ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገባቸውን እጆችንና እግሮችን ባዶአቸውን በመተው እራቁት እያደረጉ ልጆቻቸው ጤናማ እንዲሆኑ መጠበቅን መተው አለባቸው፡፡ ወደ ሕይወት ምንጭ ተጠግተው ያሉ የሰውነት ክፍሎች ዋና ከሆኑ የአካል ክፍሎች ርቀው ካሉ እጆችና እግሮች ይልቅ አነስተኛ ልብስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተለምዶ በትካሻ፣ በሳንባዎች እና በልብ ላይ የሚደረጉ ትርፍ ልብሶችን እጆችና እግሮች ቢለብሱና ጤናማ የሆነ የደም ዝውውር ርቀው ላሉት የአካል ክፍሎች እንዲደርስ ቢደረግ ኖሮ ዋና የሆኑ የአካል ክፍሎች ድርሻቸው በሆነ ልብስ ብቻ የራሳቸውን የስራ ድርሻ ጤናማ በሆነ ሁኔታ ባከናወኑ ነበር፡፡ {2SM 470.2}Amh2SM 470.2

    እናቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁ ጠውልገውና እድገታቸው ተገትቶ፣ በጉንፋን፣ በእንፍሉዌንዛ፣ በመታፈን፣ በፊትና በአንገት ላይ በሚወጡ የዕጢ ነቀርሳ እባጮች፣ በሰውነት መጉረብረብ እና በሳንባና በአእምሮ መጨናነቅ ሲሰቃዩ ድንጋጤና የልብ ሀዘን ይሰማችኋልን? መንስኤዎችንና ውጤታቸውን አጥንታችኋልን? ቅባትና ቅመማ ቅመም የሌለባቸውን ቀላልና ተመጣጣኝ ምግብ ሰጥታችኋቸዋልን? ልጆቻችሁን ስታለብሱ በፋሽን አትመሩምን? እጆችን በቂ ልብስ ሳይለብሱ መተው የብዙ በሽታዎች እና ያለ ጊዜ መሞት ምክንያት ነው፡፡ የልጃገረዶቻችሁ እጆችና እግሮች እንደ ወንዶች ልጆቻችሁ ሁሉ በሁሉም መንገድ ሙቀት በሚያገኙበት ሁኔታ የማይለብሱበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ወንዶች ከቤት ውጭ እንቅስቃሴ የማድረግ ልምድ ስላላቸው ለቅዝቃዜ መጋለጥን ይለማመዱታል፣ ለወንዶች የውጭ አየር ተፈጥሮአዊ ባሕርይ ስለሚሆን ስስ ልብስ ሲለብሱ ለብርድ የሚጋለጡት ከሴቶች ይልቅ ባነሰ መጠን ነው፡፡ በቤት ውስጥ በሞቀ አከባቢ መኖር የለመዱና አደጋ የማይችሉ ልጃገረዶች እጆቻቸውና እግሮቻቸው እቤት በነበሩበት ጊዜ እንደነበረው ሁሉ ምንም መከላከያ ሳይደረግላቸው ወደ ውጭ ይወጣሉ፡፡ አየሩ ብዙም ሳይቆይ እጃቸውንና እግራቸውን በማቀዝቀዝ ለበሽታ መንገድ ይከፍታል፡፡ {2SM 471.1}Amh2SM 471.1

    ልጃገረዶቻችሁ የሚለብሱት ቀሚስ ወገቡ ልል መሆን አለበት፡፡ የልብሳቸው አይነት ምቹና ጨዋነትን የተከተለ መሆን አለበት፡፡ በቀዝቃዛ የአየር ንብረት በረዥም የእግር ሹራብ ውስጥ ሊደረግ የሚችል ሙቀት የሚሰጥ ለስላሳ ጨርቅ ወይም ከጥጥ የተሰሩ ልብሶችን መልበስ አለባቸው፡፡ በእነዚህ ላይ ሙቀት የሚሰጡና ማሰሪያ ኖሮአቸው በቁርጭምጭምት ዙሪያ በደንብ የተቆለፉ፣ ወይም በታችኛው ጫፍ ላይ ከጫማ ጋር ለመገናኘት ጠበብ ያሉ ሙሉ ሱሪዎች መልበስ አለባቸው፡፡ ቀሚሳቸው ከጉልበት በታች መድረስ አለበት፡፡ በዚህ የአለባበስ ዘዴ የሚያስፈልገው አንድ ቀለል ያለ ቀሚስ ወይም ቢበዛ ሁለት ሲሆን እነዚህ በወገብ ላይ መቆለፍ አለባቸው፡፡ ጫማዎቻቸው ወፍራም ሶል ያላቸው እና በደንብ ምቾት የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህን አለባበስ ከተከተሉ ልጃገረዶቻችሁ ከወንድ ልጆቻችሁ የበለጠ ለንፋስ በመጋለጥ ሰውነታቸው ለአደጋ አይጋለጥም፡፡ በክረምት ወራት እንኳን ቢሆን በምድጃ በሚሞቅ በተዘጋ ክፍል ውስጥ ከመወሰን ይልቅ ውጭ የሚኖሩ ቢሆን እንኳን ጤንነታቸው እጅግ የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ {2SM 471.2}Amh2SM 471.2

    ወላጆች አሁን እያደረጉ እንዳሉት ልጆቻቸውን ማልበስ በሰማይ እይታ ኃጢአት ነው፡፡ እነርሱ እንደ ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት ብቸኛው ምክንያታቸው ፋሽን ነው የሚለው ነው፡፡ በአንዲት ጥብቅ ያለች መጠምጠሚያ ሸፍነው የልጆቻቸውን እጆችና እግሮች ለቅዝቃዜ ማጋለጣቸውን እንደ ጨዋነት አድርገው ምክንያት ማቅረብ አይችሉም፡፡ ለጤና ተስማሚ ነው፣ ወይም ውብ ነው ብለው መሟገት አይችሉም፡፡ ሌሎችም ይህን ጤንነትን እና ሕይወትን የሚጎዳ ልምምድ ስለሚከተሉ ራሳቸውን የተሃድሶ አራማጆች ነን ለሚሉት ነገር ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ በዙሪያችሁ ያለው ሰው ሁሉ ለጤና ጎጂ የሆነውን ፋሽን ስለሚከተል ኃጢአታችሁን አነስተኛ አያደርገውም፣ ወይም ለልጆቻችሁ ጤንነትና ሕይወትም ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ --How to Live, No. 5, pp. 66-74. Amh2SM 471.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents