Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቅንነት አስፈላጊ ነው

    በዚህ ዘመን፣ ክርስቶስ በሰማይ ደመና ከመምጣቱ ቀደም ብሎ፣ ጌታ ቅን የሆኑና ሰዎችን በታላቁ የጌታ ቀን እንዲቆሙ የሚያዘጋጁ ሰዎችን ይጠራል፡፡ መጻሕፍትን በማጥናት ረዥም ጊዜ የወሰዱ ሰዎች በሕይወታቸው ለዚህ የመጨረሻ ጊዜ አስፈላጊ የሆነ ቅን አገልግሎት እያሳዩ አይደሉም፡፡ ቀላልና ግልጽ ምስክርነት አያስተላልፉም፡፡ በአገልጋዮችና በተማሪዎች መካከል በእግዚአብሔር መንፈስ የመሞላት አስፈላጊነት አለ፡፡ በሙሉ ነፍሱ ከሚቀርብ መልእክተኛ ልብ የሚወጡ በጸሎትና በቅንነት የሚቀርቡ ተማጽኖዎች ጽኑ እምነትን ይፈጥራሉ፡፡ የተማሩ ሰዎች እግዚአብሔርንና እርሱ የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቃቸው ከመደገፍ ይልቅ ከመጻሕፍት በተማሩት እውቀት ስለሚደገፉ ይህን ለማድረግ የተማሩ ሰዎች አያስፈልጉም፡፡ ብቸኛውን እውነተኛና ሕያው እግዚአብሔርን የሚያውቁ ሁሉ የእግዚአብሔርን አንድያ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቃሉ፣ የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይሰብካሉ፡፡ . . . {2SM 152.3}Amh2SM 152.3

    ማንም ቢሆን እግዚአብሔር ለሚገስጻቸው ሰዎች የማስጠንቀቂያ መልእክት አይመጠላቸውም ብሎ ይገምታልን? ተግሳጽ የተሰጣቸው ሰዎች በቁጣ ተነስተው የእግዚአብሔርን መልእክተኛ ለመጫን ሕግ ለማምጣት ይሻሉ፣ ነገር ግን ይህን በማድረጋቸው በመልእክተኛው ላይ ሕግ እያመጡ ሳይሆን ተግሳጹንና ማስጠንቀቂያውን በሰጠው በክርስቶስ ላይ እያመጡ ናቸው፡፡ ሰዎች ከሚፈጽሙት የስህተት ድርጊት የተነሳ የእግዚአብሔርን ሥራ ለአደጋ በሚያጋልጡበት ጊዜ ምንም ዓይነት የተግሳጽ ድምጽ አይሰሙምን? ጉዳዩ ጥፋተኛውን ብቻ የሚመለከት ቢሆንና ሥራው ከእርሱ የማያልፍ ቢሆን ኖሮ የማስጠንቀቂያ ቃላቱ ለእርሱ ብቻ ይሰጡ ነበር፤ ነገር ግን የእርሱ ተግባር በእውነት ጉዳይ ላይ አዎንታዊ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ እና ነፍሳት ለአደጋ ከተጋለጡ የማስጠንቀቂያው ስፋት ከተፈጸመው ጉዳት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ምስክርነቶች አይከለከሉም፡፡ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚሉ ግልጽ የተግሳጽና የማስጠንቀቂያ ቃላቶች እግዚአብሔር ከሾማቸው ወኪሎች ይመጣሉ፤ ቃላቱ የሚመነጩት ከሰብዓዊ መሳሪያዎች ሳይሆን እነርሱን ለሥራው ከሾማቸው ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በምድራዊ ፍርድ ቤቶች ክስ ቢመሰረት እና ለፍርድ እንዲቀርቡ እግዚአብሔር ዝም ካለ ይህን የሚያደርገው ስሙ እንዲከበር ነው፡፡ ይህን ሥራ ለመስራት ራሱን ለሚሰጥ ሰው ወዮለት፡፡ ምንም ቢሆን እግዚአብሔር የሚያነበው አንድን ነገር ለማድረግ ያነሳሳውን ውስጣዊ ምክንያት ነው፡፡ ወንድሞቻችን ግልጽ እንዲሆኑና በጉዳዩ ላይ እንዳይደራደሩ እግዚአብሔር እንዲያስተምራቸው እጸልያለሁ፡፡ ከዚህ ጋር ግንኙነት ከሚፈጥሩና እንደዚህ ካሉ ሰዎች የተነሳ የእግዚአብሔር ሥራ መቀጥቀጥና መቁሰል ደርሶበታል፣ ቶሎ ከእርሱ ቢለዩ የተሻለ ነው፡፡. . . {2SM 152.4}Amh2SM 152.4

    እግዚአብሔር ጽኑ የሆነ ታማኝነት ያላቸውን ሰዎች ይጠራል፡፡ ሁለት ገጽ ያላቸውን ሰዎች በችግር ጊዜ ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡ ትክክል ባልሆነ ሥራ ላይ እጃቸውን ጭነው «ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም” የሚሉ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ --Letter 19 1/2, 1897. {2SM 153.1}Amh2SM 153.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents