Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እስከ ፍጻሜ ድረስ

    በዚህ ሰዓት የምንሰራው ሥራ በልብ፣ በአእምሮና በነፍስ ላይ አሻራውን በጥልቀት እንዲያሳርፍ ከልብ እጸልያለሁ፡፡ መደናገር እየጨመረ ሊሄድ ይችላል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አማኞች እንደመሆናችን መጠን እርስ በርሳችን እንበረታታ፡፡ ባንዲራውን ዝቅ አናድርግ፣ ነገር ግን የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ ወደሆነው እየተመለከትን ከፍ አድርገን እንያዝ፡፡ በሌሊት ወቅት እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ ልቤን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር አነሳለሁ፣ እርሱም ያበረታኝና በአገር ውስጥም ሆነ በሩቅ አገሮች ባሉ የሥራ መስኮች ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ጋር አብሮአቸው እንዳለ ማረጋገጫ ይሰጠኛል፡፡ የእሥራኤል አምላክ አሁንም ሕዝቡን እየመራ መሆኑን እስከ ፍጻሜም ድረስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን በመገንዘቤ ተበረታትቻለሁ ተባርኬያለሁም፡፡Amh2SM 406.3

    ለአገልጋይ ወንድሞቻችን ከከናፍሮቻችሁ የሚወጡ ቃላት በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይል የተቀመሙ ይሁኑ እንድላቸው ታዝዣለሁ፡፡ ልዩ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሪትን ፈልገን የምናውቅበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ሥር-ነቀል የሆነ ራስን የመቀደስ ሥራ ያስፈልገናል፡፡ በሕይወታችንና በአገልግሎታችን የእግዚአብሔርን ኃይል መግለጫ ለማሳየት ጊዜው ሙሉ በሙሉ አሁን ነው፡፡ Amh2SM 406.4

    ጌታ የሶስተኛውን መልአክ መልእክት የማወጅ ሥራ እየጨመረ በሚሄድ ብቃት ወደ ፊት ሲቀጥል ለማየት ይመኛል፡፡ ለሕዝቡ ድልን ለመስጠት በየዘመናቱ እንደሰራ ሁሉ በዚህ ዘመንም ለቤተ ክርሰቲያኑ ያለውን ዓላማ በድል ወደ ታጀበ ፍጻሜ ለማምጣት ይናፍቃል፡፡ በእርሱ የሚያምኑ ቅዱሳን ከብርታት ወደ በለጠ ብርታት፣ በእርሱ ሥራ እውነትና ጽድቅም ከእምነት ወደበለጠ እርግጠኝነትና መታመን በመሻገር በአንድነት ወደ ፊት እንዲቀጥሉ ያዛቸዋል፡፡Amh2SM 407.1

    እያንዳንዱን አዲስ ልምምድ መጋፈጥ እንድንችል ብርታት ሊሰጠን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን በማስታወስ ለእሱ ቃል መርሆዎች እንደ አለት ጸንተን መቆም አለብን፡፡ በጌታ ስም ከብርታት ወደ ብርታት መሄድ እንድንችል በሕይወታችን ሁልጊዜ የጽድቅን መርሆዎች እንጠብቅ፡፡ ከቀደምት ልምምዳችን አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በእግዚአብሔር መንፈስ መመሪያና ማረጋገጫ የተደገፈውን እምነት እጅግ ቅዱስ እንደሆነ አድርገን መያዝ አለብን፡፡ እግዚአብሔር ሕጉን በሚጠብቅ ሕዝብ አማካይነት እያንቀሳቀሰ ያለውን እና ጊዜ ወደ ፊት በገፋ ቁጥር በእርሱ የፀጋ ኃይል አማካይነት እየጠነከረና ብቃቱ እየጨመረ የሚሄደውን ሥራ እጅግ የከበረ አድርገን መንከባከብ አለብን፡፡ ጠላት የእግዚአብሔርን ሕዝብ መረዳት ለመጋረድ እና ብቃታቸውን ለማዳከም እየፈለገ ነው፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በሚያመለክታቸው ሁኔታ ከሰሩ የቀድሞዎቹን የፈረሱ ቦታዎች ለመገንባት የአጋጣሚ በሮችን ይከፍትላቸዋል፡፡ ጌታ በታማኞቹ ላይ የመጨረሻ ድልን ማህተም ለማሳረፍ ከሰማይ በኃይልና በታላቅ ግርማ እስኪወርድ ድረስ ልምምዳቸው የማያቋርጥ እድገት የሚያሳይ ይሆናል፡፡Amh2SM 407.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents