Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 44—ሰዎችን በሰመመን ውስጥ የመክተት አደጋዎች

    ሰዎችን በሰመመን ውስጥ የማስገባት ዘዴዎችን ለሚጠቀሙ ሀኪሞች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

    ወንድምና እህት ኤን ሆይ፣ የአእምሮ ፈውስ ሳይንስን በተመለከተ ያሉአችሁ አመለካከቶች ካልተለወጡ እና አእምሮአችሁን በተመለከተ በማያሻማ ሁኔታ የመቀየርና የመለወጥ አስፈላጊነት እንዳለ ካልተረዳችሁ በስተቀር የመሰናከያ አለቶች፣ በመላእክትና በሰዎች የምትታዩ አሳዛኝ እይታዎች እንደምትሆኑ እንድታስታውሱ በጌታ ስም እጠይቃችኋለሁ፡፡Amh2SM 349.1

    እውነት በእናንተ ላይ ያለው ተጽዕኖ ጥቂት ነው፡፡ አንድ ሰው ምንም ያህል ጥሩ ሰው ቢሆን፣ የሌላ ሰው አእምሮ በእሱ አእምሮ ቁጥጥር ሥር እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ከሆነ ለማንም ቢሆን አደገኛ ነው፡፡ የአእምሮ ፈውስ ሳይንስ ሰይጣናዊ ሳይንስ እንደሆነ ልንገራችሁ፡፡ የወደፊት ልምምዳችሁን በአስከፊ ሁኔታ እስከሚጎዳ ድረስ ርቃችሁ ሄዳችሁበታል፡፡ ወደ አእምሮአችሁ ከገባበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከዚህ ጊዜ ድረስ እጅግ ጎጂ የሆነ እድገት እያሳየ ነው፡፡ ይህን ሳይንስ የቀየሰው አቀናባሪ ሰይጣን መሆኑን ማየት ካልቻላችሁ በቀር እናንተ እንደምታስቡት ከእሱ ሥርና ቅርንጫፍ ለመለየት ይህን ያህል ቀላል አይሆንም፡፡ የዚህ ሳይንስ አጠቃላይ ፍልስፍና የሰይጣናዊ ማታለያ ድንቅ የፈጠራ ሥራ ነው፡፡ ስለ ነፍሳችሁ ብላችሁ ይህንን ከሚመስል ከእያንዳንዱ ነገር ራሳችሁን አላቅቁ፡፡ ይህን ሳይንስ በተመለከተ አእምሮውን ለመቆጣጠር እንድትችሉ በሌላ ሰው አእምሮ ውስጥ ሀሳቦችን በጨመራችሁ ቁጥር ከሰይጣን ጋር በቆራጥነት እየተባበራችሁ ናችሁ፡፡ ለነፍሳችሁ ብላችሁ ከዚህ የጠላት ወጥመድ ራሳችሁን አላቅቁ፡፡Amh2SM 349.2

    ማናችሁም ብትሆኑ ፍላጎት ያደረባችሁን ሳይንስ ማጥናት የለባችሁም፡፡ ይህን ሳይንስ ማጥናት ማለት ክፉንና መልካምን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ መቅጠፍ ማለት ነው፡፡ እናንተም ሆናችሁ ማንኛውም ሟች የሆነ ሰው እንደዚህ ዓይነቱን ሳይንስ እንዳይማር ወይም እንዳያስተምር እግዚአብሔር ይከለክላል፡፡ ወንድም ኤን ሆይ፣ ከዚህ ሳይንስ ጋር ጉዳይ ያለህ የመሆኑ ሁኔታ ብቻውን በጤና ተቋሙ ውስጥ መሪ ሐኪም መሆንህ ተገቢ አለመሆኑን ለማሳየት በቂ ነው፡፡…..Amh2SM 350.1

    የአእምሮ ፈውስ ሳይንስ በማስተማራችሁ እግዚአብሔር እንዳትነኩት ከከለከላችሁ ክፉንና ደጉን ከምታስታውቅ ዛፍ እየተመገባችሁ ነበር፡፡ አሁን ኢየሱስን ማየት የምትጀምሩበትና የእርሱን ባሕርይ በመመልከት በመለኮት አምሳያ የምትለወጡበት ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡Amh2SM 350.2

    የሰይጣን ኃይሎች የሚሰሩበትን የሰመመን ሽታ ያለበትን ነገር ሁሉ ከራሳችሁ ቆርጣችሁ ጣሉት፡፡ Letter 20, 1902.Amh2SM 350.3