Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «በፍሬያቸው” የተፈተኑ

    በእነዚህ ክፉ ቀናት ሰዎች እውነት ነው ብለው የሚያመጡትን ነገር ሁሉ መቀበል የለብንም፡፡ ከእግዚአብሔር እንደተላኩ መምህራን ከእግዚአብሔር መልእክት እንዳላቸው እየተናገሩ በሚመጡበት ጊዜ ይህ እውነት መሆኑን እንዴት እናውቃለን? ብሎ በጥንቃቄ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ኢየሱስ «ሀሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፣ ብዙዎችንም ያስታሉ» ብሎ ነግሮናል (ማቴ 24፡11)፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ምን እንደሆነ የምናውቅበትን መፈተኛ ስለሚሰጠን መታለል የለብንም፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፣ «ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ፣ እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ በውስጣቸው ብርሃን ስለሌላቸው ነው» (ኢሳ. 8፡ 20)፡፡ {2SM 99.1}Amh2SM 99.1

    ከዚህ አረፍተ ነገር ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር ሕግና ምስክር እንደሚለው ያለውን ነገር ማወቅ እንድንችል ትጉህ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች መሆን እንዳለብን ነው፡፡ በሌላ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ከአደጋ ነጻ አይደለንም፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፣ «የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፡፡ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፡፡ ከእሾህ ወይን፣ ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያደርጋል፣ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል፡፡ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፣ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም፡፡ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል፡፡ ስለዚህ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ» (ማቴ. 7፡ 15-19)፡፡ --The Review and Herald, Feb. 23, 1892. {2SM 99.2}Amh2SM 99.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents