Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመጨረሻ ድል ቃል ኪዳን

    ከፊታችን የሚጠብቀን ሥራ የሰብአዊ ፍጡርን እያንዳንዱን ኃይል የሚያዳክም ነው፡፡ ጠንካራ እምነትንና ሁልጊዜ ነቅቶ መጠበቅን የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚያጋጥሙን ችግሮች ተስፋ የሚያስቆርጡ ናቸው፡፡ የሥራው ትልቅነት በራሱ ያስደነግጠናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር እርዳታ ባሪያዎቹ በመጨረሻ ድልን ይቀዳጃሉ፡፡ ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፣ ከፊታችሁ ከሚጠብቁአችሁ ፈታኝ ልምምዶች የተነሣ «እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ» (ኤፌ. 3፡ 13)፡፡ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መንገዱን እያዘጋጀላችሁ ከፊታችሁ ይሄዳል፤ በእያንዳንዱ አንገብጋቢ እርዳታ በሚሻ ሁኔታ ውስጥ ረዳታችሁ ይሆናል፡፡ Amh2SM 407.3

    «ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሰረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፣ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፣ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ፡፡Amh2SM 408.1

    «እንግዲህ በእኛ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን” (ኤፌ. 3፡ 14-21)፡፡ General Conference Bulletin, May 27, 1913, pp. 164, 165.Amh2SM 408.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents