Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለማያቋርጥ ጥረት የተሰጠ ሽልማት

    የባለቤቴን ጤንነት ለመመለስ በተደረገው ጥረት ለአሥራ ስምንት ወራት ከእግዚአብሔር ጋር የማያቋርጥ ትብብር ካደረግኩ በኋላ ወደ ቤት መልሼ ወሰድኩት፡፡ ወደ ወላጆቹ ወስጄ «አባት፣ እናት፣ ይኸውላችሁ ልጃችሁ» አልኳቸው፡፡Amh2SM 308.1

    እናቱ «ኤለን፣ ለዚህ አስደናቂ ለሆነ የጤና መመለስ ከእግዚአብሔርና ከአንቺ ሌላ ምሥጋና የሚገባው ማንም የለም፡፡ ጥረትሽ ውጤት አስገኝቷል» አለችኝ፡፡Amh2SM 308.2

    ጤንነቱ ከተመለሰ በኋላ በሕይወቱ ዘመን ከሰራቸው ሥራዎች ሁሉ የተሻለ ሥራ የሰራባቸውን በርካታ ዓመታት በሕይወት ኖረ፡፡ ለአሥራ ስምንት ወራት ልፋት ያለበትን እንክብካቤ ላደረግኩበት እነዚህ ጠቃሚ ሥራ የተሰራባቸው ዓመታት እጥፍ ድርብ አድርገው አልካሱምን?Amh2SM 308.3

    ይህንን አጭር የሕይወት ልምምድ ትረካ የሰጠኋችሁ የታመሙትን ሰዎች ወደ ጤንነት ለመመለስ ስለምንጠቀምባቸው የተፈጥሮ ዘዴዎች የሆነ የማውቀው ነገር እንዳለ ላሳያችሁ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ስንተባበር እርሱ ድርሻውን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አምነን ከሰራን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ተአምራቶችን ይሰራልናል፡፡ የወንድሞቼ ጥረቶች እጅግ የተሳኩ እንዲሆኑ ትርጉም ያለው መንገድ እንዲከተሉ ልመራቸው የምችለውን ነገር ሁሉ ለማድረግ እሻለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ቢሆን ኖሮ ወደ መቃብር የሄዱት ብዙዎች ዛሬ በሕይወት ሊኖሩ ይችሉ ነበር፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ማገናዘብ የምንችል ወንዶችና ሴቶች እንሁን፡፡ Manuscript 50, 1902.Amh2SM 308.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents