Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በቃለ መጠይቅ ውስጥ የተመለሱ ጥያቄዎች

    ደብሊዩ ሲ ኋይት፡- የንግድ ጥያቄዎችን እና ስለ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በተመለከተ እንዲሁም ለጥያቄው ጌታ «አዎን ወይም «አይደለም» ብሎ እንዲመልስለት የሚጠይቀውን ግለሰብ ውሳኔዎች በተመለከተ ምን ታስባለህ? ቃላቱን በካርዱ በአንድ ወገን ላይ ጽፎ ወደ መሬት በመጣል ካርዱ የወደቀበት ሁኔታ አንድን ነገር እንዲያደርግ ወይም እንዳያደርግ እግዚአብሔር የሚያመለክትበት መንገድ እንደሆነ በማመን እንደ መልስ አድርጎ ይቀበልን?Amh2SM 327.1

    ኢ ጂ ኋይት እንዲህ ትላለች፡- (ይህ እግዚአብሔር የማያረጋግጠው የዘፈቀደ ዘዴ ነው፡፡ የዚህን ዓይነት የመፈተኛ ሀሳብ ለሰጡ ሰዎች «አይሆንም፣ አይሆንም ብየአቸዋለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚመለከቱ ቅዱስ ነገሮች እነዚህን በመሰሉ ዘዴዎች መደረግ የለባቸውም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ባለ መንገድ ፈቃዱን እንድንማር አያስተምረንም፡፡Amh2SM 327.2

    ካርድ ወይም ሳንቲም በመጣል እና እንዴት እንደወደቀ በመመልከት የእሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ መወሰን እግዚአብሔርን የሚያስከብሩ ልምምዶችን ይሰጠናልን? በፍጹም አይሰጠንም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ መፈተኛዎች ተቀብሎ ሥራ ላይ የሚያውላቸውን ሰው ኃይማኖታዊ ልምምድ ያበላሻሉ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበት መመሪያ ለማግኘት እነዚህን በመሳሰሉ ነገሮች ላይ የሚደገፍ እያንዳንዱ ሰው እንደገና መለወጥ ያስፈልገዋል፡፡)Amh2SM 327.3

    የአድቬንቲስት ሕዝብ በ1844 ዓ.ም ከደረሰባቸው ታላቁ ተስፋ መቁረጥ በኋለ በተደጋጋሚ መቋቋም የነበረብን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ ያኔ ታምሜ ከታኘሁበት ተቀስቅሼ ለዚህ አክራሪነት የተግሳጽ መልእክት እንድሰጥ ተልኬ ነበር፡፡ የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመው ነበር፡፡ ምልክት ይመርጡና ምልክቱ ያሳያቸውን መንገድ ይከተሉ ነበር፡፡Amh2SM 327.4

    ምልክት ከተጠቀሙባቸው አጋጣሚዎች በአንዱ የሞተው ልጅ ከሙታን እንደሚነሳ ስለተረዱ ሬሳውን አልቀበሩም ነበር፡፡Amh2SM 327.5

    እንደምልክት እየተጠቀሙ ስለነበሯቸው ስለ እነዚህ ነገሮች ስህተትነት ምስክርነት እንድሰጥ ተልኬ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንደ ሰጠኝ ብርሃን ከሆነ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ከሚለው ውጭ ምንም ደህንነት የለም፡፡Amh2SM 327.6

    ደብልዩ ሲ ኋይት፡- የንግድ ልውውጥን የሚመለከት ጉዳይ ነው እንበል፡፡ ለእኔ ጥሩ የሚመስለኝን ንብረት እመለከትና እንድገዛው ወይም እንዳልገዛው እግዚአብሔር እንዲነግረኝ ጠየቅኩት፡፡ ከዚያም ሳንቲምን ወደ ላይ የመወርወር ዘዴን ተጠቅሜ አንዱ ገጽ ወደ ላይ ከተገለበጠ ዕቃውን እገዛዋለሁ፤ ሌላኛው ገጽ ወደ ላይ ከተገለበጠ አልገዛውም አልኩ እንበል፡፡Amh2SM 327.7

    ኢ ጂ ኋይት፡- የዚህ ዓይነት ነገር ወደ እርሱ ሥራ መምጣት እንደሌለበት እግዚአብሔር መልእክት ሰጥቶኛል፡፡ ይህ ድርጊት ዝቅ አድርጎ አቧራ ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ለእኔ ቀርቦልኝ የነበረው እንዲህ ነበር፡፡ እነዚህ ነገሮች አእምሮን ከእግዚአብሔር፣ ከኃይሉና ከጸጋው ወደ ተራ ነገሮች ስለሚመልሱ ጠላት እነዚህን ተራ ነገሮች ሰው የሰራቸውን መፈተኛዎች ከመከተል የተነሳ የመጣ አስደናቂ ነገር አድርጎ ለማሳየት ይጠቀማል፡፡ Amh2SM 328.1

    ደብሊዩ ሲ ኋይት፡- ትንሽ ልዩነት እንኳን አያመጣም፡፡ ከዚህ በፊት ስለ እነርሱ የተናገርኳቸው በሜይን ግዛት ውስጥ ያሉ አክራሪዎች በእነዚህ አስፈሪ ልምምዶች ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ ሁሉ ይጸልዩ የለምን? Amh2SM 328.2

    ይህ ዕቅድ ሰው ሊያደርግ በሚችል ነገር ላይ ወደ መታመን ይመራል፡፡ እኛ የምንፈልገው የእግዚአብሔርን ኃይል በአነስተኛ መጠን ሳይሆን በከፍተኛ መጠን ነው፡፡ ከሰማይ አምላክ ብቻ የሚመጣውን ክብር እንፈልጋለን፡፡ ያኔ እርሱ በሚሰጣቸው መለኮታዊ ትምህርቶች መሰረት እንሰራለን፡፡Amh2SM 328.3

    ሕዝባችን በእምነት ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡና በእርሱ አገልግሎቶች አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያውቁ እንዲያስተምራቸው መንፈስ ቅዱስ በነጻ እንደሚሰጣቸው እና እንደሚመራቸው እንዲያምኑ ለማደፋፈር ባለን ኃይል ሁሉ እየሰራን ነበር፡፡ Ibid., pp. 16-20.Amh2SM 328.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents