Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በቃል ኪዳን ግንኙነት

    ክርስቶስን እንደ አዳኛችን አድርገን በተቀበልን ጊዜ ከእርሱ ጋር አብረን ሠራተኞች የመሆንን ሁኔታም ተቀብለናል፡፡ እንደ ክርስቶስ ፀጋ ታማኝ መጋቢዎች በዚህ ዓለም ውስጥ የእርሱን መንግሥት ለመገንባት እንድንሰራ ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ለመሆን ቃል ኪዳን ገብተናል፡፡ ለነፍሳችን የመበዠት ዋጋ ለከፈለው ለእርሱ የአእምሮ፣ የነፍስና የአካል ኃይሎችን ሁሉ ቀድሶ ለመስጠት እያንዳንዱ የክርስቶስ ተከታይ ቃለ-መሃላ ፈጽሟል፡፡ የድነታችንን መሪ በመከተል ወታደሮች ለመሆን፣ ተግተን ለመስራት፣ ፈተናን፣ ውርደትንና ስድብን ለመታገስ፣ የእምነትን ገድል ለመጋደል ቃል ገብተናል፡፡ {2SM 124.1}Amh2SM 124.1

    ከዓለማዊ ማህበራት ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል ኪዳን እየጠበቅህ ነህ ወይ? እነዚህ ግንኙነቶች የአንተንም ሆነ የሌሎችን አእምሮ ወደ እግዚአብሔር ይመራሉ ወይስ ፍላጎትንና ትኩረትን ወደ ሌላ አቅጣጫ እየቀየሩ ናቸው? ከመለኮታዊ ኃይሎች ጋር ያለህን ግንኙነት ያጠነክራሉ ወይስ አእምሮህን ከመለኮታዊ ነገር ወደ ሰብዓዊ ነገር ይመልሳሉ? {2SM 124.2}Amh2SM 124.2

    እግዚአብሔርን እያገለገልክ፣ እያከበርክና ከፍ ከፍ እያደረግክ ነህ ወይስ ኃጢአት እየሰራህ እያዋረድከው ነህ? ከኢየሱስ ጋር እየሰበሰብክ ነህ ወይስ እየበተንክ ነህ? ለእነዚህ ድርጅቶች አልፈው የሚሰጡ ሀሳብ፣ እቅድና ልባዊ ትጋት ሁሉ በከበረው በክርስቶስ ደም የተገዙ ናቸው፤ ነገር ግን ከከሃዲዎችና ከአረመኔዎች ጋር፣ የእግዚአብሔርን ስም ከሚያረክሱ ጋር፣ ከመጠጥ ሱሰኞች፣ ከሰካራሞችና ከትንባሆ አፍቃሪዎች ጋር አንድነት ስትፈጥሩ እርሱን እያገለገላችሁ ነው ወይ? {2SM 124.3}Amh2SM 124.3

    በእነዚህ ማህበራት ውስጥ ጥሩ የሚመስል ነገር ቢኖርም ከዚህ ጥሩ ነገር ጋር ውጤት አልባ እንዲሆን የሚያደርግና እነዚህን ሕብረቶች ለነፍስ ፍላጎቶች ጎጂ የሚያደርጉ እጅግ ብዙ ነገሮች ተቀላቅለዋል፡፡ ሥጋዊ ምግብ በመመገብ ከምንኖረው ውጭ ሌላ ሕይወት አለን፡፡ «ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” አለው (ማቴ. 4፡4)፡፡ «እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ. 6፡53)፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ «ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ” (ዮሐ. 6፡34)፡፡ ሰውነታችን የተሰራው ከምንበላውና ከምንጠጣው ነገር ነው፡፡ በተፈጥሮአዊው እንደሆነው ሁሉ በመንፈሳዊውም እንዲሁ ነው፤ መንፈሳዊ ተፈጥሮአችንን የሚመግበው አእምሮዎቻችን የሚያስቡት ነገር ነው፡፡ አዳኛችን እንዲህ ብሏል፣ «ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው» (ዮሐ. 6፡63)፡፡ መንፈሳዊ ሕይወት መቆየት ያለበት በቃሉ አማካይነት ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ነው፡፡ አእምሮ ቃሉን ማሰብ አለበት፣ ልብ በእሱ መሞላት አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በልብ ውስጥ በቅድስና ከተቀመጠና ከታዘዙት በክርስቶስ ፀጋ ኃይል ሰውን ትክክለኛ ያደርገዋል፣ ትክክለኛ ሆኖ እንዲኖርም ያደርገዋል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰብዓዊ ተጽዕኖ፣ እያንዳንዱ ምድራዊ ፈጠራ፣ ለሰው ብርታትና ጥበብ የመስጠት ኃይል የለውም፡፡ ኃይለኛ ስሜትን መግታት አይችልም፣ ወይም የባሕርይ መጣመምን ሊያስተካክል አይችልም፡፡ የእግዚአብሔር እውነት ልብን ካልተቆጣጠረ በስተቀር ህሊና ይጣመማል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ዓለማዊ ሕብረቶች አእምሮ ከእግዚአብሔር ቃል እንዲርቅ ይደረጋል፡፡ ሰዎች ቃሉን የሕይወታቸው ጥናትና መመሪያ እንዲያደርጉ አይመሩም፡፡ {2SM 124.4}Amh2SM 124.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents