Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አመጽና ክህደት

    አመጽና ክህደት በምንተነፍሰው አየር ውስጥ ናቸው፡፡ ረዳተ-ቢስ ነፍሶቻችንን በእምነት በክርስቶስ ላይ ካላንጠለጠልን በስተቀር በእነርሱ መነካታችን አይቀርም፡፡ ሰዎች አሁን እንኳን በቀላሉ ወደ ስህተት የሚመሩ ከሆነ ሰይጣን በክርስቶስ ተመስሎ ተአምራቶችን ሲሰራ እንዴት መቆም ይችላሉ? ሰይጣን የክርስቶስን መልክ በመልበስ ክርስቶስ የሰራቸውን ሥራዎች እየሰራ እኔ ክርስቶስ ነኝ ሲል በዚህ የተሳሳተ ውክልናው የማይናወጥ ማነው? የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሀሰተኛ ክርስቶሶች ታማኝነታቸውን እንዳይገልጹ የሚያግዳቸው ምንድን ነው? «አትከተሉአቸው” (ሉቃስ 17፡23)፡፡Amh2SM 394.4

    አስተምህሮዎች በግልጽ መስተዋል አለባቸው፡፡ እውነትን እንዲሰብኩ ተቀባይነት ያገኙ ሰዎች በጽኑ መመስረት አለባቸው፤ ያኔ መህልቃቸው አጥብቆ ስለሚይዝ ጀልባቸው ማዕበሉንና ወጀቡን መቋቋም ትችላለች፡፡ ማታለያዎች እየጨመሩ ስለሚሄዱ አመጽን በትክከለኛው ስሙ መጥራት ይኖርብናል፡፡ ሙሉ የጦር ዕቃን ለብሰን መቆም አለብን፡፡ በዚህ ጦርነት ውስጥ የምንገጥመው ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ኃጢአትንና ሥልጣናትንም ጭምር ነው፡፡ መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ ኤፌሶን 6፡ 10-18 በጥንቃቄና በሚመስጥ መልኩ ይነበብ፡፡Amh2SM 395.1

    እምነታቸውን የሚክዱ ሰዎች የዘንዶውን ቃላት እያስተጋቡ ናቸው፡፡ ከቅዱሳን ጋር ጦርነት ለማድረግ የሄዱትን የሰይጣን ወኪሎች መግጠም አለብን፡፡ «ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ» (ራዕይ 12፡17)፡፡ እምነታቸውን የሚክዱ ሰዎች እውነተኛና ታማኝ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ በመተው ባርናባስን ከሚወክሉት ጋር ይወዳጃሉ፡፡ «ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ» (ማቴ. 7፡20)፡፡Amh2SM 395.2

    ይህን የምጽፍበት ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ብዙ ሰዎች እንዳይ የተደረግኩት በሚራመዱ ዛፎች ተመስለው ነው፡፡ እነዚህ ዛፎች በአታላዩ መረብ ውስጥ ለማስገባት የተዘጋጀውን ወጥመድ ለይተው ከማወቃቸው በፊት ሌላ ጥልቅ ልምምድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አሁን እስከ ግማሽ መንገድ ድረስ የተሰራ ሥራ መኖር የለበትም፡፡ ክፍተት ባለበት ቦታ ላይ እንዲቆሙና አጥር እንዲሰሩ ጌታ የሚጠራቸው ሰዎች ራሳቸውን የሚገዙ፣ ቆራጥ አቋም ያላቸው እና በፍጹም ነፍሳቸው የሚሰሩ ናቸው፡፡ (ኢሳ. 58፡ 12-14 ላይ የተወሰደ)፡፡Amh2SM 395.3

    በሁሉም ቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ በሁሉም አገልጋዮቻችን አማካይነት መተላለፍ ያለበት የማያሻማ ምስክርነት አለ፡፡ እግዚአብሔር ክህደት እንዲመጣ የፈቀደበት ምክንያት ሰው ምን ያህል ሊታመኑበት የማይችል እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ ሁልጊዜ መመልከት ያለብን ወደ እግዚአብሔር ነው፤ ቃሉ አዎን ወይም አይደለም ሳይሆን አዎን እና አሜን ነው፡፡ Undated manuscript 148.Amh2SM 395.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents