Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የሌላኛው መልአክ መልእክት

    የሁለተኛው መልአክ መልእክት ፍሬ ነገር ከክብሩ የተነሳ ምድርን በሚያበራው በሌላኛው መልአክ እንደገና ተሰጥቷል፡፡ እነዚህ መልእክቶች ሁሉ በዚህ የምድር ታሪክ መዝጊያ ላይ በሕዝብ ፊት ለመቅረብ በአንድ ላይ ይቀላቀላሉ፡፡ ዓለም በሙሉ ይፈተናል፣ የአራተኛውን ትዕዛዝ ሰንበት በተመለከተ በስህተት ጨለማ ውስጥ የነበሩ ሁሉ ለሰዎች ሊሰጥ ያለውን የመጨረሻውን የምህረት መልእክት ያስተውላሉ፡፡ {2SM 116.2}Amh2SM 116.2

    ሥራችን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ማወጅ ነው፡፡ «አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ» (አሞጽ 4፡12) የሚለው መልእክት ለዓለም መሰጠት ያለበት ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ለእኛ በግላችን የተሰጠን ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ሸክምን ሁሉና በቀላሉ የሚወርረንን ኃጢአት ለመጣል ተጠርተናል፡፡ ወንድሜ ሆይ፣ ከክርስቶስ ጋር ለመጠመድ መስራት ያለብህ ሥራ አለ፡፡ እየገነባህ ያለኸው ሕንጻ በአለት ላይ ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን፡፡ ዘላለምን ይሆን ይሆናል በሚል በእድል ጉዳይ ለአደጋ አታጋልጥ፡፡ አሁን እየገባንባቸው ባሉት አደገኛ በሆኑ እይታዎች ውስጥ ለመሳተፍ ላትኖር ትችላለህ፡፡ በእያንዳንዷ ጊዜ መንቃት የለብህምን? ራስህን በቅርበት መመርመርና ዘላለም ለእኔ ምን ሊሆንልኝ ይችላል ብለህ መጠየቅ የለብህምን?{2SM 116.3}Amh2SM 116.3

    የእያንዳንዱ ነፍስ ትልቅ ሸክም መሆን ያለባቸው ጥያቄዎች ልቤ ታድሷል ወይ? ነፍሴ ተለውጣለች ወይ? በክርስቶስ በማመን ኃጢአቶቼ ይቅር ተብለውልኛል ወይ? ዳግመኛ ተወልጃለሁ ወይ? «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ» (ማቴ. 11፡28) ከሚለው ግብዣ ጋር እየተስማመሁ ነኝ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡…ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ትልቅነት ሁሉንም ነገር እንደ ጉዳት ትቆጥሩታላችሁ? ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን እያንዳንዱን ቃል ማመን ሀላፊነታችሁ እንደሆነ ይሰማችኋልን? --Manuscript 32, 1896. {2SM 117.1}Amh2SM 117.1