Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ የመለኮት መገኘት

    ክርስቶስ በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ፡- ሐኪም አሳሳቢ የሆነ ቀዶ ጥገና ከማድረጉ በፊት የታላቁን ሐኪም እርዳታ ይጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር ከመከራ ውስጥ በሰላም እንደሚያሳልፈው፣ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ጊዜ ሁሉ ለሚታመኑት እውነተኛ መጠጊያ እንደሆነ እየተሰቃየ ላለው ሕመምተኛ ያረጋግጥለት፡፡ Ministry of Healing, p. 118 (1905).Amh2SM 284.2

    አዳኙ በሕመምተኛው ክፍል፣ በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ አለ፤ ለስሙ ክብር ኃይሉ ታላቅ ነገርን ያደርጋል፡፡ Manuscript 159, 1899 (Manuscript, “The Privileges and Duties of Christian Physician”).Amh2SM 284.3

    ቀዶ ጥገና ማድረግ እምነትን መካድ አይደለም፡- ከእምነታችን ጋር በተገናኘ ሁኔታ እግዚአብሔር ያስቀመጠውን እያንዳንዱን ዘዴ የመጠቀም፣ ተስፋውን እንዲሰጠን ከለመንን በኋላ በእግዚአብሔር መታመን መብታችን ነው፡፡ ቀዶ ጥገና አስፈላጊ ከሆነና ሐኪሙም ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ቀዶ ጥገና ማድረግ እምነትን መካድ አይደለም፡፡ ሕመምተኛው ፈቃዱን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ከሰጠ በኋላ ወደ ታላቁ ሐኪምና ብርቱ ፈዋሽ በመቅረብ፣ በሙሉ መታመን ራሱን በመካድ በእግዚአብሔር ይታመን፡፡ ጌታ ለስሙ ክብር እንደሚሆን በመመልከት የሕመምተኛውን እምነት ያከብርለታል፡፡ «በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ፡፡ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ” (ኢሳ. 26፡ 3፣ 4)፡፡ Manuscript 67, 1899 (General Manuscript).Amh2SM 285.1

    አሳሳቢ የሆነ ቀዶ ጥገና እያደረግክ ሳለህ ወደ እግዚአብሔር ስትመለከት ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በአጠገብህ ቆመው ነበር፣ እጆችህ ተመልካቾችን ባስደነቀ ትክክለኛነት ሥራውን እየሰሩ ሳለ የመላእክቶች እጆች ታይተው ነበር፡፡ Letter 73, 1899 (To the physician addressed in the preceding item).Amh2SM 285.2

    መለኮታዊ ተመልካች በሐኪሙ አጠገብ፡- እስካሁን ከኖሩት የሕክምና ሚስዮናውያን መካከል ክርስቶስ ትልቁ የህክምና ሚስዮናዊ ነው፡፡ አንድም ሕመምተኛ ሞቶበት አያውቅም፡፡ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ላሉት ሐኪሞች እንዴት ብርታትና ምሪት እንደሚሰጥ ያውቃል፡፡ ከባድ የሆኑ ቀዶ ጥገናዎችን ሲያደርጉ በአጠገባቸው ይቆማል፡፡ ይህ እንዲህ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ቢለዋው የፀጉር ስፋትን ያህል ዝንፍ ቢል ኖሮ ሊጠፉ የሚችሉ ሕይወቶችን አድኗል፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ክርስቶስ ሕወቱን የሰጠላቸውን ሰዎች ያለማቋረጥ እያገለገሉ ናቸው፡፡Amh2SM 285.3

    በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሐኪሞች እሱን እያገለገሉት ስለሆነ እግዚአብሔር ችሎታንና ብቃትን ይሰጣቸዋል፡፡ ችሎታቸው የራሳቸው ሳይሆን ከላይ የሚመጣ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ሥራቸውን በብልህነት ማከናወን እንዲችሉ ለሐኪሞች ጥበብን የሚሰጥ መለኮታዊ ተመልካች በአጠገባቸው እንዳለ ይገነዘባሉ፡፡ Manuscript 28, 1901 (Words addressed to workers at the St. Helena Sanitarium).Amh2SM 285.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents