Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሌሎች ግልጽ የሚያደርጉ መግለጫዎች

    ክፉ ተጽእኖ አሳድረው ያልፉ ይሆን? ክፉ ተጽእኖ ትቶ የሚያልፍ ምንም ነገር ቢሆን በሰብአዊ አካል ውስጥ መጨመር የለበትም፡፡ Medical Ministry, p. 228 (Manuscript 162, “how to conduct Sanitariums,” 1897).Amh2SM 280.4

    ቀለል ያሉ ፈዋሽ መድሃኒቶች ተፈጥሮን ከማገዛቸው ባሻገር ከተጠቀሙአቸው በኋላ ክፉ ውጤትን ትተው አያልፉም፡፡ Letter 82, 1897 (To Dr. J. H. Kellogg).Amh2SM 280.5

    ደምን የሚመርዙ ነገሮች፡- በጤና ማዕከሎቻችን ውስጥ ቀለል ያሉ ፈውሶችን መጠቀምን እንደግፋለን፡፡ ጠንካራ መድኃኒቶች የደምን ፍሰት ስለሚመርዙ እንዳይጠቀሙባቸው እናስተምራለን፡፡ ጤና እንዲጠበቅ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ እንዴት መብላት፣ እንዴት መጠጣት፣ እንዴት መልበስና እንዴት መኖር እንዳለባቸው ትርጉም ያለው ትምህርት መሰጠት አለበት፡፡ Counsels on Diet and Foods, p. 303 (Sermon at Lodi, California, May 9, 1908).Amh2SM 280.6

    በተፈጠሩ ችግሮች ላይ መርዘኛ የሆኑ መድሃኒቶችን በመጨመር ችግሮችን ለመፍታት አትሞክሩ፡፡ Ministry of Healing, p. 235 (1905).Amh2SM 280.7

    እያንዳንዱ ጠንቀኛ መድሃኒት፡- በሐኪሞች ትዕዛዝም ሆነ በግለሰቡ ምርጫ በጨጓራ ላይ የሚደረግ እያንዳንዱ ጠንቀኛ መድሃኒት በሰብአዊ ፍጡር ላይ ጥቃት በማድረስ መላውን አካል ይጎዳል፡፡ Manuscript 3, 1897 (General manuscript).Amh2SM 280.8

    አስፈላጊ የሆኑ ኃይሎችን መስበር፡- መድሃኒቶች ሁልጊዜ አስፈላጊ የሆኑ ኃይሎችን የመስበርና የማጥፋት ዝንባሌ አላቸው፡፡ Medical Ministry, p. 223 (General manuscript entitled “ sanitarium,” 1887).Amh2SM 281.1

    ጎጂ ውጤቶችን የሚያስከትሉ መርዘኛ ዝግጅቶች፡- ጊዜያዊ ስቃይን የሚያስታግሱ እንኳን ቢሆን ጎጂ የሆኑ ውጤቶችን ትተው የሚያልፉ መድሃኒቶችን የእግዚአብሔር ባሪያዎች ለሕሙማን መስጠት የለባቸውም፡፡ ከአትክልትም ሆነ ከማዕድናት የሚዘጋጀውን እያንዳንዱን መርዘኛ ዝግጅት ወደ ሰውነታችን ማስገባት ጉበትንና ሳንባዎችን በመጉዳትና በአጠቃላይ አካልን በማናወጥ አስከፊ ተጽእኖ ትቶ ያልፋል፡፡ Spiritual Gifts, Vol. 4, p. 140 (1864).Amh2SM 281.2

    የመርዘኛ መድሃኒቶች አስከፊ ውጤቶች፡- ከተፈጥሮ የሚገኙ ቀላል ፈውሶች መርዘኛ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከተጠቀሙ በኋላ የሚሰማቸውን ዓይነት አስከፊ ውጤቶች ሳያስከትሉ ጤንነትን ለመመለስ ይረዳሉ፡፡ መርዘኛ መድሃኒቶች ሕመምተኛው ራሱን የሚረዳበትን ኃይል ያጠፋሉ፡፡ ሕመምተኞች ቀላልና ጤናማ ምግቦችን በመመገብ፣ በአንድ የምግብ ሰዓት ላይ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን በመመገብ ጨጓራን ማጨናነቅን በመተው ይህን ኃይል እንዲለማመዱ መማር አለባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለሕመምተኛው በሚሰጥ ትምህርት ውስጥ መካተት አለባቸው፡፡ ጤናን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል፣ ከሕመም እንዴት መራቅ እንደሚቻል፣ እረፍት በሚያስፈልግበት ጊዜ እንዴት ማረፍ እንደሚቻል ንግግር መደረግ አለበት፡፡ Letter 82, 1908 (To Physicians and Managers at Loma Linda).Amh2SM 281.3