Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሶስቱ መላእክት መልእክቶች በትልቁ አቀማመጣቸው

    የመጀመሪያው፣ የሁለተኛውና የሶስተኛው መላእክት መልእክቶች እወጃ በእግዚአብሔር ምሪት በተጻፈ ቃል ውስጥ ተመልክቶ ነበር፡፡ ከዚያ ውስጥ አንዲት ችካል ወይም የወረቀት መርፌ መወገድ የለበትም፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊ ሥልጣን አዲስ ኪዳንን በብሉይ ኪዳን የመተካት መብት እንደሌለው ሁሉ የእነዚህን መልእክቶች ቦታ የመቀየር መብትም የለውም፡፡ ብሉይ ኪዳን ወንጌል በምሳሌና በምልክቶች ነው፡፡ አዲስ ኪዳን ዋናው ነገር ነው፡፡ አንዱ የሌላውን ያህል አስፈላጊ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን ከክርስቶስ ከናፍር የተነገሩ ቃላትን ስለሚያቀርብ እነዚህ ትምህርቶች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ኃይላቸውን አላጡም፡፡{2SM 104.2}Amh2SM 104.2

    የመጀመሪያውና የሁለተኛው መላእክት መልእክቶች በ1843 እና በ1844 ዓ.ም ተሰጥተዋል፣ አሁን በሶስተኛው መልአክ መልእክት እወጃ ሥር ነን፤ ነገር ግን ሶስቱም መልእክቶች አሁንም መታወጅ አለባቸው፡፡ እውነትን እየፈለጉ ላሉት ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ አሁንም መደገማቸው አስፈላጊ ነው፡፡ ቅደም ተከተላቸውንና ወደ ሶስተኛው መልአክ መልእክት የሚያመጡ ትንቢቶችን አጠቃቀም በማሳየት በቃልና በጽሁፍ አዋጁን ማሰማት አለብን፡፡ ያለ መጀመሪያውና ሁለተኛው ሶስተኛው ሊኖር አይችልም፡፡ በሕትመት ውጤቶችና በንግግር በትንቢታዊ ታሪክ መስመር ላይ የነበሩትንና ወደ ፊት የሚመጡትን ነገሮች በማሳየት እነዚህን መልእክቶች ለዓለም ልንሰጥ ነው፡፡ {2SM 104.3}Amh2SM 104.3

    የታተመው መጽሐፍ የራዕይ መጽሐፍ ሳይሆን ከዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ ከመጨረሻ ዘመን ጋር የተገናኘው ክፍል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ «ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፣ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፣ እውቀትም ይበዛል» (ዳን. 12፡ 4)፡፡ መጽሐፉ በተከፈተ ጊዜ «ወደ ፊት አይዘገይም» ተብሎ ታውጇል (ራዕይ 10፡6ን ይመልከቱ)፡፡ አሁን የዳንኤል መጽሐፍ ማህተሙ ስለተፈታ ክርስቶስ ለዮሐንስ ያሳየው ራዕይ ለምድር ኗሪዎች ሁሉ መምጣት አለበት፡፡ እውቀት ከመብዛቱ የተነሳ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን ለመቆም ሊዘጋጅ ነው፡፡ {2SM 105.1}Amh2SM 105.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents