Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአዲሱ የጤና ማሰልጠኛ ተቋም ሥራ መሪ የተሰጠ ምክር

    ተቋሙ በውስጥና በውጭ የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፡፡ በግቢህ ውስጥ ያሉ ነገሮች እጅግ በጣም ጥሩ በሆነ ሥርዓት መቀመጣቸውን እርግጠኛ ሁን፡፡ በሕመምተኞች አእምሮ ደስ የማይል ሀሳብ የሚፈጥር ምንም ነገር አይኑር፡፡Amh2SM 298.1

    ሕመምተኞች ጤናማ አኗኗር እንዲኖሩና በቂ የአካል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ አደፋፍሯቸው፡፡ እንደዚህ ማድረግ ጤንነታቸው እንዲመለስላቸው ብዙ ይረዳቸዋል፡፡ በሽተኞች ብዙ ጊዜ ከቤት ውጭ እንዲያሳልፉ ለማደፋፈር ወንበሮች በዛፎች ጥላ ሥር ይቀመጡ፡፡ የአየር ንብረቱ ቀዝቃዛ በሚሆንበት ወቅት በሽተኞች ንፋስ ሳያገኛቸው በፀሐይ ውስጥ መቀመጥ እንዲችሉ በሸራ ወይም በመስታወት የተከለለ ቦታ ይዘጋጅ፡፡Amh2SM 298.2

    ንጹህ አየርና የፀሐይ ብርሐን፣ በተቋሙ ውስጥ እና ውጭ አስደሳች ሁኔታ መኖር፣ ጥሩ ቃላትና የርኅራኄ ተግባራት ለሕመምተኞች አስፈላጊ የሆኑ ፈውሶች ናቸው፡፡ ወደ ጤና ተቋሙ ለሚመጡ ሕመምተኞች እነዚህን ፈውሶች ለመስጠት የምታደርጋቸውን ጥረቶች እግዚአብሔር በስኬት ያጎናጽፋቸዋል፡፡ ደስተኛ ስትሆን እና ለሌሎች ርኅራኄንና ተስፋን ስትገልጽ የራስህ ነፍስ በብርሐንና በሰላም ይሞላል፡፡ ከእግዚአብሔር የሚገኘው የበረከት ፀሐይ ብርሐን ከሁሉም ነገር እንደሚበልጥብን በፍጹም አትርሳ፡፡Amh2SM 298.3

    እግዚአብሔር ነጻ ስለሰጣቸው ጤንነትን መላሽ ስለሆኑ ነገሮች ዋጋ እና በቀላሉ ስለምናገኛቸው ቀላል ነገሮች ጠቃሚነት ለነርሶችና ለበሽተኞች አስተምር፡፡Amh2SM 298.4

    ስለ ከሰል ፈዋሽነት ስላለኝ ልምምድ ትንሽ እነግርሃለሁ፡፡ ለአንዳንድ የምግብ መፈጨት ችግሮች ከመድሃኒቶች የበለጠ ውጤታማ መፍትሄ ነው፡፡ ጥቂት የከሰል ዱቄት ተቀላቅሎ የተማሰለበት የወይራ ዘይት ማንጻትና መፈወስ ይችላል፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ የሰውነት መጉረብረብ ሲከሰት የባሕር ዛፍን የደቀቀ ከሰል በነጻነት ተጠቅመናል፡፡…Amh2SM 298.5

    የእነዚህን ቀላል ፈውሶች ጥቅም ሁልጊዜ እያጠናህ አስተምር፡፡ ተራው ሕዝብ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን እነዚህን ዘዴዎች ስንጠቀም ልዩ የሆኑ የጌታ በረከቶች እንደሚከተሏቸው መጠበቅ እንችላለን፡፡ Letter 100, 1903.Amh2SM 298.6

    የከሰል አጠቃቀምን በተመለከተ ፈጣን ፈውስ የታየባቸው ሌሎች ልምምዶች፡፡ አንድ ወንድም ሆዱ ተጉረብርቦ ደም እያስቀመጠው ተወስዶ ነበር፡፡ ሰውዬው ጥንቁቅ የጤና ተሃድሶ አራማጅ አልነበረም፣ ነገር ግን ዝም ብሎ ፍላጎቱን የሚፈጽም ሰው ነበር፡፡ ለበርካታ ወራት ስንሰራ የነበርንበትን ቴክሳስን ለቀን ለመሄድ እየተዘጋጀን ነበርን፡፡ ከወባ በሽታ ትኩሳት የተነሳ እየተሰቃዩ ያሉትን ይህን ወንድምና ቤተሰቡን እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሰዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናቸው ሰረገላዎች ነበሩን፡፡ እኔና ባለቤቴ የበርካታ ቤተሰቦች አባወራዎች ሞተው ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ያለ እንክብካቤ ከሚቀሩ ወጪውን እኛ እንሸከማለን ብለን አሰብን፡፡Amh2SM 298.7

    ሁለቱ ወይም ሶስቱ በሽቦ ፍራሾች ላይ ተኝተው በሰረገላ ተጭነው ተወሰዱ፡፡ ነገር ግን ከሆድ መጉረብረብ ሕመም የተነሳ ይሰቃይ የነበረው ሰው እኔ ወደ እርሱ እንድመጣ መልእክተኛ ላከብኝ፡፡ እኔና ባለቤቴ እሱን ማንቀሳቀስ እንደማይጠቅም ወሰንን፡፡ ቁስሉ መበስበስ ጀምሯል የሚል ወሬ መናፈስ ጀምሯል፡፡ ይህ በሽተኛ በደቀቀ ከሰል ላይ ውኃ ተጨምሮ እንዲጠጣው እና በሆዱ እና በጨጓራው ላይ የከሰል ፋሻ እንዲደረግለት የሚል ሀሳብ ከእግዚአብሔር እንደተላከ ሆኖ መጣልኝ፡፡ ከዴኒሰን ከተማ አንድ ማይል በሚሆን ርቀት ላይ ነበርን፤ ነገር ግን የበሽተኛው ሰው ልጅ ወደ ቀጥቃጭ ቤት ሄደና ከሰል ወስዶ ካደቀቀው በኋላ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ተጠቀመው፡፡ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ለውጥ አሳየ፡፡ ቤተሰቡን ትተን ብቻችንን ልንቀጥል ነበር፣ ነገር ግን በቀጣዩ ቀን የእሱ ሰረገላ እኛን እየቀደመ ስናይ አስደናቂ ነበር፡፡ የታመመው ሰው በሰረገላው ውስጥ በአልጋ ላይ ተኝቶ ነበር፡፡ በተጠቀመው ቀላል ነገር የእግዚአብሔር በረከት ሥራውን ሰርቶ ነበር፡፡ Letter 182, 1899 (To a worker in an overseas field. See page 287).Amh2SM 298.8

    ከሰልና የተልባ ዘር፡፡ ሆስፒታልን በጣም እንፈልጋለን፡፡ በሕመም እየተሰቃየ ለነበረው የአሥራ ስምንት ወር ዕድሜ ለነበረው የወንድም ቢ ትንሽ ሕፃን ማድረግ የምትችለው ነገር ካለ ለማየት እህት ሣራ ማክእንተርፈር ሐሙስ ቀን ተጠርታ ነበር፡፡ በሆነ መርዘኛ ነፍሳት ከመነከሱ የተነሳ በጉልበቱ ላይ በጣም የሚያም እብጠት ለሳምንታት ነበረበት፡፡ በእብጠቱ ላይ የደቀቀ ከሰል ከተልባ ጋር ተቀላቅሎ ተደረገለትና ወዲያውኑ ፈውስ ሰጠው፡፡ ሕፃኑ ሌሊቱን በሙሉ ከሕመም የተነሣ ሲያለቅስ ያደረ ሲሆን ይህ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ተኛ፡፡ ዛሬ ሕፃኑን ሁለት ጊዜ ማየት ነበረባት፡፡ እብጠቱን ለሁለት ከፈለችውና ብዛት ያለው ብጫ ነገርና ደም ወጣ፡፡ ሕጻኑ ከነበረበት ሕመም ፋታ አገኘ፡፡ ሕመምን ለማስታገስና የሚያስከትለውን መዘዝ ለማስወገድ ልናገኛቸው የምንችላቸውን ቀላል ነገሮች ለመጠቀም ብልህ መሆን ስለምንችል እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ Manuscript 68, 1899 (General Manuscript).Amh2SM 298.9

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents