Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በተስፋ መሞላትና ጀግንነት

    የጄኔራል ኮንፍራንስ ስብሰባን በመከታተል ላይ ያሉ ተወካዮቻችን በተስፋ የመሞላትንና የጀግንነትን መንፈስ የመንከባከብ ልዩ ክብር አላቸው፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ አዳኙ በብዙ መንገዶች ራሱን ገልጦላችኋል፤ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ስትሰሩ ሳለ ልባችሁን በእርሱ መገኘት የፀሐይ ብርሃን ሞልቶታል፤ በሚታዩና በማይታዩ አደጋዎች ውስጥ ጠብቆአችኋል፤ አሁንም እንደገና ከወንድሞች ጋር በጉባኤ ስትገናኙ ሳለ በጌታ ደስ ልትሰኙ እና የእርሱን በሕይወት የሚኖር ፀጋ በማወቃችሁ ሃሴት የማድረግ ልዩ ክብር አላችሁ፡፡ የእርሱ ፍቅር አእምሮንና ልብን እንዲቆጣጠር ፍቀዱለት፡፡ ያለ መጠን ከመድከም፣ ብዙ ከመጨነቅ የተነሳ ደስታችሁን ከመነጠቅ እና ከማዘን ተጠበቁ፡፡ የሚያነቃ ምስክርነት አስተላልፉ፡፡ ጨለማ ከሆነና ተስፋ ከሚያስቆርጥ ነገር ዓይናችሁን ዘወር በማድረግ ሕይወታችንን እና ያለንን ነገር ሁሉ እየሰጠንለት ያለውን የወቅቱን እውነት ሥራ በንቃት እየተከታተለ ወዳለው ወደ ታላቁ መሪ ወደ ኢየሱስ ተመልከቱ፤ ይህ የወቅቱ እውነት በግርማ ተሞልቶ ድል ያደርጋል፡፡Amh2SM 399.2

    ተወካይ ወንድሞቻችን በስብሰባው ወቅት የሚኖራቸው አመለካከት በመላው የሥራ መስክም ሆነ በተወካዮቹ በራሳቸው ላይ የሚታይ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ ውድ ወንድሞቼ ሆይ፣ ኢየሱስ በልባችሁ እያደረ፣ በሕይወት እየኖራችሁ፣ እያበረታችሁና እያጽናናችሁ እንደሆነ ይታይ፡፡ በየቀኑ የእርሱን ቅዱስ መንፈስ በሙላት የመቀበል እና ለዓለም እያወጅን ስላለው መልእክት ጠቀሜታ እና ስለሚያካትታቸው ነገሮች ሰፋ ያለ አመለካከቶችን የማግኘት ልዩ ዕድል አላችሁ፡፡ ጌታ ከሕጉ ውስጥ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን ሊገልጥላችሁ ፈቃደኛ ነው፡፡ በፊቱ ትሁት በሆነ ልብ ጠብቁ፡፡ እየኖርንበት ያለውን ዘመን ማስተዋል እንድትችሉ፣ ስለ አርሱ ዓላማ ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ፣ እና ነፍሳትን በማዳን ሥራ ውስጥ ብቃታችሁ እንዲጨምር ከልባችሁ ጸልዩ፡፡ Amh2SM 399.3

    ብዙ ጊዜ በሌሊት ወቅት በኃላፊነት ላይ ያሉ ወንድሞቻችን ጌታን በሙላት ለማወቅ ልባዊ ጥረት ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ እንዳደፋፍራቸው ታዝዣለሁ፡፡ ሠራተኞቻችን እየኖርንበት ያለንበትን ዘመን ማወቅ የሚገባቸውን ያህል ቢያውቁ ኖሮ በጌታ ወገን ለመሆን ቆራጥ ዓላማ ይኖርና በእውነት ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሠራተኞች ይሆኑ ነበር፡፡ ልባቸውንና ነፍሳቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሲቀድሱ በሁሉም ኃጢአት ላይ ድልን ለመቀዳጀት እስከ አሁን ካላቸው ልምምድ የበለጠ ጥልቅ ልምምድ እንደሚያስፈልጋቸው ይረዳሉ፡፡ Amh2SM 400.1

    በምድር ላይ በቅርቡ ሊመጣ ያለው ነገር ለእኛ ምን እንደሆነ ማሰብ መልካም ነው፡፡ ጊዜው የመቀለድና በራስ ወዳድነት የመኖር ጊዜ አይደለም፡፡ እየኖርንበት ያለው ዘመን በአእምሮአችን ውስጥ በደንብ ተጽእኖ ማሳደር እያቃተው ከሆነ እኛ ጋ ምን ሊደርስ ይችላል? ቅዱሳን መጻሕፍት እስካሁን ካየነው የበለጠ ንጹህና ቅዱስ ሥራ እንዲሰራ አይጠይቁምን?Amh2SM 400.2