Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በካንሰር እየሞተ ያለን ሰው ለማገልገል የተጻፉ ቃላት

    አንረሳህም፤ በቤተብ መሰዊያ በጸሎታን እናስብሃለን፡፡ ብዙ ሌሊቶችን ስለ አንተ ወደ እግዚአብሔር እየተማጸንኩ እንደነቃሁ በአልጋዬ ላይ እጋደማለሁ፡፡ Amh2SM 256.1

    ስለ አንተ በጣም አዝናለሁ፡፡ የእግዚአብሔር በረከት በላይህ እንዲያርፍ መጸለዬን እቀጥላለሁ፡፡ ያለ መጽናኛ አይተውህም፡፡ ይህ ዓለም ዋጋው ትንሽ ነው፣ ነገር ግን ውድ ወንድሜና እህቴ ሆይ፣ኢየሱስ፣ «ጠይቁ ይሰጣችኋል፤ እሹ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያውን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል” (ማቴ 7፡ 7) ብሏል፡፡ በእናንተ ፋንታ ይህ ተስፋ እንዲፈጸምላችሁ እማጸናለሁ፡፡....Amh2SM 256.2

    ወንድሜ ሆይ፣ አንድ ሌሊት ተደግፌህ እንዲህ የምልህ መሰለኝ፡- «ለጥቂት ጊዜ ነው፣ ጥቂት የሕመም ሰቆቃዎች፣ ጥቂት ተጨማሪ የስቃይ ሰዓታት፣ ከዚያ በኋላ እረፍት፣ የተባረከ እረፍት ነው፡፡ በተለየ ሁኔታ ሰላም ታገኛለህ፡፡ ሰብዓዊ ዘር በሙሉ መፈተን አለበት፡፡ ሁላችንም ጽዋውን መጠጣትና በመከራ መጠመቅ አለብን፡፡ ክርስቶስ ሞትን እጅግ መራር በሆነ መልኩ ለእያንዳንዱ ሰው ቀምሷል፡፡ እንዴት እንደሚያዝልን ያውቃል፡፡ በእሱ ክንዶች ላይ ብቻ እረፍ፤ እሱ ይወድሃል፣ በዘላለማዊ ፍቅሩ አድኖሃል፡፡ እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን፣ የህይወት አክሊል ትቀበላለህና፡፡” Amh2SM 256.3

    “ከአሁን ጀምሮ በዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ የፈተናን ትርጉም ያውቃሉ፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን እንደሚሰጥህና እንደማይተውህ አውቃለሁ፡፡ እንዲህ የሚለውን የእግዚአብሔርን ተስፋ ወደ አእምሮህ አምጣው፣ ‹ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹአን ናቸው፡፡ መንፈስ፡- አዎን፣ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፣ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምጽ ሰማሁ› (ራዕይ 14፡ 13)፡፡ ጥሩ ድፍረት ይኑርህ፡፡ ብችል ኖሮ አብሬህ እሆን ነበር፣ ነገር ግን በትንሣኤ ማግሥት እንገናኛለን፡፡” ...Amh2SM 256.4

    ለእህት ሲ ደግሞ የማጽናኛ ቃላት እየተናገርኩ ነበር፡፡ እያበረታታኋት ሳለ ክፍሉ በእግዚአብሔር መላእክት የተሞላ መሰለ፡፡ ሁለታችሁም ጥሩ ድፍረት ይኑራችሁ፡፡ ጌታ አይተዋችሁም አይጥላችሁምም፡፡ --Letter 312, 1906.Amh2SM 256.5