Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 1

    በኤድን ውድቀት ከገባበት ጊዜ አንስቶ ሰብዓዊ ዘር እየተበላሸ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ አካለ ጎዶሎነት፣ ደደብነት፣ በሽታና ሰብዓዊ ሥቃይ ከውድቀት ጀምሮ ባለው በእያንዳንዱ ትውልድ ላይ እጅግ እየከበዱና እየተጫኑ መጥዋል፣ ነገር ግን እነዚህ ችግሮች በትክክል የሚያስከትሉን ነገሮችን በማወቅ ረገድ አብዛኛው ሕዝብ ተኝቷል፡፡ በአብዛኛው እነዚህ ነገሮች በሚያስጠላ ሁኔታ ውስጥ ስለመሆናቸው እነርሱ በደለኛ እንደሆኑ አድርገው አይቆጥሩም፡፡ በአጠቃላይ እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ እግዚአብሔር እንዳመጣባቸው አድርገው በመመልከት እየደረሰባቸው ላለው ዋይታ ጠንሳሹ እግዚአብሔር እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ነገር ግን፣ ይብዛም ይነስም፣ የሥቃይ ሁሉ መሠረት መሻትን አለመግዛት ነው፡፡ Amh2SM 411.1

    ሔዋን ከተከለከለችው ዛፍ ፍሬ ለመውሰድ እጇን በዘረጋች ጊዜ መሻቷን አልገዛችም ነበር፡፡ ከዚያ ውድቀት ወዲህ የራስን ፍላጎት ማሟላት በወንዶችና በሴቶች ልብ ውስጥ ነግሦአል፡፡ በተለይም ለምግብ ፍላጎት በመገዛታቸው በአእምሮ ከመመራት ይልቅ በምግብ ቁጥጥር ሥር ሆነዋል፡፡ ሔዋን የምግብ ፍላጎቷን ለማሟለት ስትል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላለፈች፡፡ እግዚአብሔር ፍላጎቷ የሚሸውን ነገር ሁሉ ሰጥቷት ነበር፣ ነገር ግን በተሰጣት ነገር አልረካ አለች፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የወደቁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቿ የዓይን አምሮታቸውንና የምግብ ፍላጎታቸውን ተከትለዋል፡፡ ልክ እንደ ሔዋን የእግዚአብሔርን ማዕቀብ አልቀበል በማለት የአለመታዘዝን መንገድ ተከትለዋል፣ አለመታዘዛቸው የሚያስከትለው መዘዝም የተባለውን ያህል አስፈሪ አይሆንም በማለት እንደ ሔዋን ራሳቸውን አታልለዋል፡፡{2SM 411.2}Amh2SM 411.2

    ሰው የአካል ጤንነቱን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ሕጎችን ችላ ከማለቱ የተነሣ በሽታ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ መንስኤው ውጤትን በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡ እጅግ ጤናማ በሆነ ምግብ መርካት እምቢ ብሏል፤ ነገር ግን ጤንነቱን መስዋዕት በማድረግ የምግብ ፍላጎትን አሟልቷል፡፡ {2SM 411.3}Amh2SM 411.3

    እግዚአብሔር የአካላችንን ሕጎች መስርቷል፡፡ እነዚህን ሕጎች ከጣስን ይፍጠንም ይዘግይም መቀጣታችን (ዋጋ መክፈላችን) የማይቀር ነው፡፡ የተዛባ የምግብ ፍላጎታችን የፈለገውን ነገር ለማግኘት እጅግ ከመንሰፍሰፉ የተነሣ ጤናማ ባልሆነ ምግብ ጨጓራችንን ከማጨናነቅ የበለጠ የጤና ሕጎች የሚጣሱበት ሌላ መንገድ የለም፡፡ የምንመገበው ምግብ ቀላል እንኳን ቢሆን ከመጠን በላይ መብላት የምግብ መፈጫ አካላትን ይጎዳል፤ በዚህ ላይ ያልተመጣጠነ ብዙ ምግብን መመገብ ሲታከልበት ክፋቱ እጅግ ይጨምራል፡፡ የሰውነት አቋም የግድ ይጎዳል፡፡ {2SM 411.4}Amh2SM 411.4

    ጤንነት ከፍተኛ በሆነ የምግብ ፍላጎት መሰዊያ ላይ እስኪሰዋ ድረስ ሰብዓዊ ቤተሰብ የምግብ ፍላጎቱን መግዛት ያለመቻል ሁኔታ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በጥንቱ ዓለም ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በመብልና በመጠጥ ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር እንስሳትን እንዲመገቡ ባይፈቅድላቸውም ሥጋን ይበሉ ነበር፡፡ ከመጠን በላይ ይበሉና ይጠጡም ነበር፣ ልቅ የሆነ የምግብ ፍላጎታቸው ገደብ አልነበረውም፡፡ ራሳቸውን አስጸያፊ ለሆነ ዝሙት አሳልፈው ሰጥተው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሊታገሳቸው እስከማይችል ድረስ ጠበኛ፣ ጨካኝ እና ክፉ ሆኑ፡፡ የኃጢአት ጽዋቸው ስለሞላ እግዚአብሔር በጥፋት ውኃ አማካይነት ምድርን ከግብረገብ እርኩሰት አጸዳ፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላ ሰዎች በምድር ላይ በተባዙ ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራትን ረሱና በእርሱ ፊት መንገዳቸውን አበላሹ፡፡ በሁሉም መልክ መሻትን አለመግዛት በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ፡፡ {2SM 412.1}Amh2SM 412.1

    እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ በድል አውጥቷቸው ነበር፡፡ ሊፈትናቸው ስለፈለገ በምድረ በዳ መራቸው፡፡ ከጠላቶቻቸው እጅ ነጻ ሲያወጣቸው ተአምራዊ ኃይሉን በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡ ድምጹን ከታዘዙና ትዕዛዛቱን ከጠበቁ ልዩ እንደሆነ ሐብት የራሱ እንደሚያደርጋቸው ቃል ገባላቸው፡፡ የእንስሳትን ሥጋ እንዳይበሉ ባይከለክላቸውም በብዛት እንዳይመገቡ ከለከላቸው፡፡ እጅግ ጤናማ የሆነ ምግብ ሰጣቸው፡፡ ከሰማይ እንጀራን አዘነበላቸው፣ ከባልጩት አለትም እጅግ ንጹህ የሆነ ውኃ ሰጣቸው፡፡ በሁሉም ነገር እርሱን ከታዘዙት ከበሽታ ሊጠብቃቸው ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ {2SM 412.2}Amh2SM 412.2

    ነገር ግን ዕብራውያን አልረኩም፡፡ ከሰማይ የተሰጣቸውን ምግብ በመጥላት በሥጋ ምንቸት አጠገብ ለመቀመጥ ወደ ግብጽ መመለስን ተመኙ፡፡ ሥጋ ከሚከለከሉ ባርነትን፣ ሞትንም ቢሆን መረጡ፡፡ እግዚአብሔር ተቆጣባቸውና ከፍተኛ የሆነ የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ ሥጋን ሰጣቸው፣ የተመኙትን ሥጋ እየበሉ ሳሉ ከመካከለቻው ብዙዎች ሞቱ፡፡ {2SM 412.3}Amh2SM 412.3

    ናዳብና አብዩ በወይን ጠጅ አጠቃቀማቸው መሻታቸውን መግዛት ካለመቻላቸው የተነሳ በእግዚአብሔር ቁጣ እሳት ተገድለዋል፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንደ መታዘዛቸው ወይም እንደ መተላለፋቸው መጠን እንደሚጎበኙ እንዲረዱ ይፈልጋል፡፡ በየትውልዱ ወንጀልና በሽታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በምግብና በመጠጥ፣ እንዲሁም ተራ የሆኑ ስሜቶችን በመፈጸም መሻትን አለመግዛት የከበሩ የአካል ክፍሎችን አበድኖአቸዋል፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ የምግብ ፍላጎት አስተሳሰብን ተቆጣጥሮታል፡፡ {2SM 412.4}Amh2SM 412.4

    ቅባትና ቅመም በበዛባቸው ምግቦች ሆድን ማጨናነቅ ፋሽን እስኪሆን ድረስ ሰብዓዊ ቤተሰብ ውድ ምግቦችን ለማግኘት እየጨመረ ለመጣው ፍላጎት ተገዥ ሆኗል፡፡ በተለይም ደስታ ፍለጋ በሚደረጉ ግብዣዎች ላይ ያለ ገደብ ለምግብ ፍላጎት መገዛት ይታያል፡፡ በቅባትና ቅመም መረቆች የተቀመሙ የተለያዩ የሥጋ ዓይነቶች፣ ውድ ኬኮች፣ ሳንቡሳዎች፣ አይስክሬም፣ ወዘተ… ያለባቸው ውድና ረፋድ ላይ የሚበሉ እራቶች ይስተናገዳሉ፡፡ {2SM 413.1}Amh2SM 413.1

    በእነዚህ ዘመናዊነትን በተከተሉ አንድነቶች ላይ የመሪነቱን ቦታ የሚወስዱት ክርስቲያን ነን ባዮች ናቸው፡፡ የምግብ ፍላጎትን ለማነሳሳት ሲባል ጤናን የሚጎዱ ቅምጥል ግብዣዎችን በማዘጋጀት እና በዚህ መንገድ ለመንፈሳዊ ዓለማ ሊውል የሚችል ነገር ሊሰበሰብ ይችላል በማለት ጠቀም ያለ ገንዘብ ለፋሽንና ለምግብ ፍላጎት አማልክት ይሰዋል፡፡ በመሆኑም አገልጋዮችና ክርስቲያን ነን ባዮች መሻትን በማይገዛ አመጋገባቸው ጤናን ወደሚጎዳ ሆዳምነት ሰዎችን በመምራት በቃላቸውና በሕይወት ምሳሌነታቸው ድርሻቸውን ተወጥተዋል፣ ተጽዕኖአቸውንም አሳድረዋል፡፡ ለሰው አእምሮ፣ ለልግስናው፣ ለሰብዓዊነቱ፣ ለከበሩ የተፈጥሮ ችሎታዎቹ ጥያቄ ከማቅረብ ይልቅ እጅግ ሊቀርብ የሚችል የተዋጣለት ተማጽኖ የሚቀርበው ለምግብ ፍላጎት ነው፡፡ {2SM 413.2}Amh2SM 413.2

    የምግብ ፍላጎትን የማርካት ፍላጎት ሰዎች ሌላ ጊዜ አንዳች ሳያደርጉ የሚያስቀምጡትን ገንዘብ እንዲሰጡ ያግባባል፡፡ ይህ ለክርስቲያኖች እንዴት ያለ አሳዛኝ ስዕል ነው! በእንደዚህ ዓይነት መስዋዕት እግዚአብሔር ይደሰታልን? ከእነርሱ ሥጦታ ይልቅ የባልቴቷ ሳንቲም የበለጠ ተቀባይነት አለው፡፡ ከልባቸው የእርሷን ምሳሌ የሚከተሉ ምስጉኖች ናቸው፡፡ የተፈጸመውን መስዋዕት የሰማይ በረከት ሲከተለው ቀላሉን ሥጦታ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሊያደርግ ይችላል፡፡ {2SM 413.3}Amh2SM 413.3

    የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ወንዶችና ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ የፋሽን ባርያዎችና በምግብ ፍላጎታቸው ሆዳሞች ናቸው፡፡ ደስታ ፍለጋ ለሚደረጉ ስብሰባዎች በሚደረግ ዝግጅት ከፍ ላሉና ለከበሩ ዓላማዎች ሊውሉ የሚችሉ ጊዜና ጉልበት የተለያዩ ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችን በማዘጋጀት ይባክናሉ፡፡ ፋሽን ስለሆነ ብቻ ደሃ የሆኑና በዕለታዊ የጉልበት ሥራ የሚተዳደሩ ብዙ ሰዎች እንግዶችን ለማስተናገድ ሲባል የተጠቃሚዎቹን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ የተለያዩ ዓይነት ውድ ኬኮችን፣ የታሸጉ ምግቦችን፣ ሳንቡሳዎችንና የተለያዩ ዓይነት ተወዳጅ ምግቦችን ለማዘጋጀት ወጪ ያወጣሉ፤ ይህ የሚሆነው ወጪ ያደረጉትን ገንዘብ ለልጆቻቸውና ለራሳቸው ልብስ ለመግዛት የሚፈልጉት ሆኖ ሳለ ነው፡፡ ጨጓራን እየጎዱ የጣዕም ፍላጎትን ለማሟላት ምግብ በማዘጋጀት ላይ የዋለው ይህ ጊዜ ለልጆቻቸው የግብረ-ገብና መንፈሳዊ ትምህርት ለመስጠት መዋል ነበረበት፡፡ {2SM 413.4}Amh2SM 413.4

    ተወዳጅ ጉብኝት ከርስ የመሙላት በዓል ሆኗል፡፡ በምግብ መፈጫ አካላት ላይ ሥራ ሊያበዙ የሚችሉ ጎጂ ምግቦችና መጠጦች በብዛት ይወሰዳሉ፡፡ ይህንን ሥራ ለማከናወን በጣም ጠቃሚ የሆኑ ኃይሎች አስፈላጊ ያልሆነ ተግባርን እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ፤ ይህ ደግሞ ድካምን ያስከትላል፣ የደም ዝውውርንም በከፍተኛ ደረጃ ይረብሻል፡፡ ከዚህ የተነሣ በመላው የአካል ሥርዓት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ የኃይል እጥረት እንዳለ ይሰማል፡፡ ከማሕበራዊ ጉብኝት ሊገኙ የሚችሉ በረከቶች ብዙ ጊዜ ይጠፋሉ፣ ይህ የሚሆነው እናንተን በእንግድነት የተቀበላችሁ ግለሰብ ከንግግራችሁ ጥቅም ከማግኘት ይልቅ እናንተ የምትበሉአቸውን የተለያዩ ዓይነት ምግቦች በማዘጋጀት በምድጃው ላይ እየለፋ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያን ወንዶችና ሴቶች በዚህ መልክ የተዘጋጁ የቅንጦት ምግቦችን በመመገባቸው የእነርሱ ተጽዕኖ ሌሎች እንዲህ ዓይነት መንገድን እንዲከተሉ በፍጹም መፍቀድ የለበትም፡፡ የእናንተ የጉብኝት ዓለማ የምግብ ፍላጎታችሁን ለማርካት ሳይሆን አብራችሁ ማሳለፋችሁ እና አሳቦቻችሁንና ስሜቶቻችሁን መለዋወጣችሁ የጋራ ጥቅም እንዲያስገኝ እንደሆነ እንዲረዱ አድርጉ፡፡ ንግግራችሁ ኋላ ከፍ ባለ የደስታ ስሜት መታወስ የሚችል ከፍ ያለና የከበረ ይሁን፡፡ {2SM 414.1}Amh2SM 414.1

    እንግዶችን የሚቀበሉ ሰዎች ከጥራጥሬ፣ ከፍራፍሬና ከአትክልት ቀለል ባለና በሚጣፍጥ መልክ የተሰራ የተሟላና ተመጣጣኝ ምግብ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የዚህ ዓይነት የምግብ ዝግጅት አነስተኛ የሆነ ተጨማሪ ጉልበትና ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን፣ በልክ ሲመገቡት የማንንም ጤና አይጎዳም፡፡ ዓለማውያን የምግብ ፍላጎታቸውን ለማርካት ጊዜን፣ ገንዘብን እና ጤናን መስዋዕት ማድረግ ከመረጡ ያድርጉትና የጤና ሕግን የመጣሳቸውን ዋጋ ይክፈሉ፤ ነገር ግን ክርስቲያኖች እነዚህን ነገሮች በተመለከተ የራሳቸውን አቋም መያዝ አለባቸው፣ ተጽዕኖአቸውንም በትክክለኛ አቅጣጫ ማሳረፍ አለባቸው፡፡ እነዚህን ተለዋዋጭ የሆኑና ጤናን እና ነፍስን የሚጎዱ ልምዶችን በመለወጥ ረገድ ብዙ ማድረግ ይችላሉ፡፡ {2SM 414.2}Amh2SM 414.2

    ብዙዎች ከእንቅልፍ ሰዓት በፊት የመብላትን ጠንቀኛ ልምድ ይፈጽማሉ፡፡ ሦስት መደበኛ ምግቦችን ተመግበው ይሆናል፤ ነገር ግን እንደራበው ሰው የድካም ስሜት ስለሚሰማቸው መክሰስ ወይም አራተኛ ምግብ ይመገባሉ፡፡ ይህንን የተሳሳተ ልምምድ በተደጋጋሚ ከመፈጸማቸው የተነሣ ልማድ ይሆንና ሳይበሉ እንቅልፍ መተኛት አይችሉም፡፡ በአብዛኛው ለዚህ የድካም ስሜት መንስኤው ቀኑን ሁሉ በጨጓራ ላይ ያልተመጣጠነና ጊዜውን ያልጠበቀ ምግብ በብዛት በመጫኑ ምክንያት የምግብ መፈጫ አካላት ያለመጠን ሥራ ስለበዛባቸው ነው፡፡ እነዚህ ሥራ የበዛባቸው የምግብ መፈጫ አካላት ስለሚደክማቸው የተንጠፈጠፈውን ኃይላቸውን ለማደስ ከሥራ የሚያርፉበትን ጊዜ ይሻሉ፡፡ ጨጓራ አስቀድሞ የተበላውን ምግብ ከመፍጨት ድካም የሚያርፍበት ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ሁለተኛው ምግብ በፍጹም መበላት የለበትም፡፡ ሦስተኛው ምግብ መበላት ካለበት ቀላልና ወደ መኝታ ከመሄድ በፊት ብዙ ሰዓታት ቀደም ብሎ መሆን አለበት፡፡ {2SM 414.3}Amh2SM 414.3

    የብዙዎች የደከመ ምስኪን ጨጓራ ስለ ድካሙ በከንቱ ያማርራል፡፡ የምግብ መፈጫ አካላት በመኝታ ሰዓታት ውስጥ አስቀድሞ ያደርጉት የነበረውን ሥራ ለመሥራት እንዲጀምሩ የሚያደርግ ተጨማሪ ምግብ በግድ ተጨምሮበታል፡፡ የእነዚህ ሰዎች እንቅልፍ በአጠቃላይ በማያስደስቱ ሕልሞች ይረበሻል፣ ከዚህ የተነሳ በማለዳ ሳይታደሱ ይነቃሉ፡፡ የመዝለፍለፍና የምግብ ፍላጎት ማጣት አለ፡፡ በመላው የአካል ክፍል ውስጥ ኃይል የማጣት ስሜት ይሰማል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምግብ መፍጫ አካሎች የእረፍት ጊዜ ስላልነበራቸው ይደክማሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የምግብ መፈጨት ችግር ስለሚያጋጥማቸውና እንደዚህ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ስለማያውቁ ግራ ይገባቸዋል፡፡ ችግሩን ያስከተለው ነገር እርግጠኛ የሆነ ውጤት አምጥቷል፡፡ ይህ ልምምድ ለረዥም ጊዜ ከተፈጸመ ጤና ክፉኛ ይጎዳል፣ ደም ይቆሽሻል፣ መልክ ይገረጣል፣ ብዙ ጊዜ የሰውነት መቆጣት ይከሰታል፡፡ ብዙ ጊዜ በሆድ አከባቢ ሕመምና የቁስለት ስሜት ይሰማል፣ ሥራን እየሰሩ ሳለ ጨጓራ እጅግ ከመድከሙ የተነሣ ሥራቸውን ለማቋረጥና ለማረፍ ይገደዳሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች እንዲከሰቱ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ ለመንገር ይቸገራሉ፤ ይህን በሚተውበት ጊዜ በግልጽ ጤናማ ናቸው፡፡{2SM 415.1}Amh2SM 415.1

    በቀን ሦስት ጊዜ ምግብ ከመመገብ ወደ ሁለት ጊዜ እየለወጡ ያሉ ሰዎች በመጀመሪያ ይብዛም ይነስም የድካም ስሜት ያስቸግራቸዋል፣ ይህ ስሜት የሚሰማቸው በተለይ ከዚህ በፊት ሦስተኛውን ምግብ የሚመገቡበት ሰዓት ሲደርስ ነው፡፡ ነገር ግን ለአጭር ጊዜ ቢታገሱት ኖሮ ይህ የድካም ስሜት ይጠፋል፡፡ {2SM 415.2}Amh2SM 415.2

    ልናርፍ ስንተኛ ጨጓራችን ሥራውን ሁሉ መጨረስ አለበት፡፡ ይህ መሆን ያለበት እርሱም ሆነ ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን በደንብ እንዲያርፉ ነው፡፡ በማንኛውም የእንቅልፍ ሰዓት የምግብ መፈጨት ሂደት መካሄድ የለበትም፡፡ ሥራ የበዛበት ጨጓራ ሥራውን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ይደክምና ግለሰቡ የድካም ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል፡፡ በዚህ ቦታ ብዙዎች ተታለዋል፣ እነዚህን ስሜቶች የፈጠረው ሰውነት ምግብን ስለፈለገ ነው ብለው ስለሚያስቡ ጨጓራ እንዲያርፍ ጊዜ ሳይሰጡት ተጨማሪ ምግብ ይወስዳሉ፣ ይህ ድርጊታቸው ለጊዜው የድካም ስሜቱን ያስወግድላቸዋል፡፡ አብልጠን በተመገብን ቁጥር የምግብ ፍላጎታችንን የማሟላት ውስጣዊ ጩኸት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ የድካም ስሜት የሚከሰተው ሥጋን ከመመገብ፣ ቶሎ ቶሎ ከመብላትና ያለመጠን ከመብላት ነው፡፡ እጅግ ጤናማ ያልሆነ ምግብን በመፍጨት ያለማቋረጥ እንዲሰራ በመደረጉ ጨጓራ ይደክማል፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ስለሌላቸው የምግብ መፍጫ አካላት ይደክማሉ፣ ከዚህ የተነሣ የ«ባዶነት ስሜት” ይፈጠርና አሁንም አሁንም የመብላት ፍላጎትን ይፈጥራል፡፡ የዚህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መፍትሄ እያሰለሱ መመገብ፣ በመጠን እና ቀለል ያላ ምግብ መመገብ፣ በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ወይም ቢበዛ ሶስት ጊዜ መብላት ነው፡፡ ጨጓራ ሥራውን ለመሥራትና ለእረፍት መደበኛ ጊዜያቶች ያስፈልጉታል፣ ስለዚህ እነዚህን ጊዜያቶች ሳይጠብቁ እና በመደበኛ የምግብ ሰዓቶች መካከል መመገብ እጅግ አደገኛ የሆነ የጤና ሕጎች ጥሰት ነው፡፡ መደበኛ የሆኑ የምግብ ሰዓቶችን በመጠበቅና ተገቢ የሆነ ምግብ በመመገብ ጨጓራ ቀስ በቀስ ይፈወሳል፡፡ {2SM 415.3}Amh2SM 415.3

    ፋሽን ስለሆነ ብቻ ከተዛባ የምግብ ፍላጎት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ውድ የሆነ ኬክ፣ ሳንቡሳዎች፣ ከምግብ በኋላ የሚበሉ ጣፋጭ ምግቦች እና ጎጂ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በጨጓራ ውስጥ ታጭቀዋል፡፡ ጠረጴዛው በተለያዩ ነገሮች መሞላት አለበት፣ ያለበለዚያ የተዛባ የምግብ ፍላጎት ሊረካ አይችልም፡፡ ብዙ ጊዜ እነዚህ የምግብ ፍላጎት ባርያዎች ጧት ንጹህ ያልሆነ ትንፋሽ ይኖራቸውና ምላሳቸው ደግሞ ሱፍ በመሰለ ነገር ይሸፈናል፡፡ ጤንነት አይሰማቸውም፣ በበሽታ፣ በራስ ምታት እና በተለያዩ ዓይነት ሕመሞች ለምን እንደሚሰቃዩ ግራ ይገባቸዋል፡፡ መንስኤው እርግጠኛ የሆነ ውጤትን አምጥቷል፡፡ {2SM 416.1}Amh2SM 416.1

    ጤንነትን ለመጠበቅ በሁሉም ነገር መሻትን መግዛት ያስፈልጋል፡፡ በሥራ፣ በአመጋገብና በምንጠጣው ነገር መሻትን መግዛት አስፈላጊ ነው፡፡ {2SM 416.2}Amh2SM 416.2

    ብዙዎች መሻትን ላለመግዛት ራሳቸውን አሳልፈው ስለሰጡ በምንም መንገድ ቢሆን ከመጠን በላይ የመብላት ልምዳቸውን አይለውጡም፡፡ መሻትን መግዛት የጎደለውን የምግብ ፍላጎታቸውን ከሚገቱ ይልቅ ጤናቸውን ይሰውና ያለ ጊዜ መሞትን ይመርጣሉ፡፡ የሚበሉትና የሚጠጡት ነገር ከጤናቸው ጋር ያለውን ግንኙነት የማያውቁ ብዙዎች አሉ፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የሚመገቡት ነገር ከጤናቸው ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያውቁ ቢደረጉ ኖሮ ለምግብ ፍላጎት ላለመገዛት የሞራል ድፍረት ይኖራቸውና ጤናማ የሆነ ምግብን ብቻ በመጠኑ በመመገብ ራሳቸውን ከትልቅ ስቃይ ያድናሉ፡፡ {2SM 416.3}Amh2SM 416.3

    እያንዳንዱን ሥራ የሚያበዛ ጫና በማስወገድ አሁን የቀረው የአካል ዋና ኃይሎች ብርታት እንዲጠበቅ ጥረቶች መደረግ አለባቸው፡፡ ጨጓራ ሙሉ ለሙሉ ላይድን ይችላል፣ ነገር ግን ትክክለኛ አመጋገብ ችግሩ እየተባባሰ ከመሄድ ያድናል፣ ብዙዎች ራስን ገዳይ በሆነ ከመጠን በላይ በመብላት ልምድ መመለስ እስከማይችሉ ድረስ ርቀው ካልሄዱ በስተቀር ይብዛም ይነስም ይድናሉ፡፡ {2SM 416.4}Amh2SM 416.4

    ሚዛናዊነት ለጎደለው የምግብ ፍላጎት ባሪያ ለመሆን ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች በዚያው አቅጣጫ እየጨመሩ ይሄዱና በምግብና በመጠጥ ራሳቸውን ካለመግዛታቸው የተነሣ የተነሳሳውን የተበላሸ ፍላጎታቸውን በመፈጸም ራሳቸውን ያዋርዳሉ፡፡ ጤና እና የአእምሮ ማስተዋል በከፍተኛ ደረጃ ችግር እስኪደርስባቸው ድረስ አዋራጅ የሆኑ ፍላጎቶቻቸውን ልጓም ይለቃሉ፡፡ የሚያገናዝቡ የአካል ክፍሎች ከክፉ ልምዶች የተነሳ በከፍተኛ መጠን ይበላሻሉ፡፡ {2SM 416.5}Amh2SM 416.5

    የምድር ኗሪዎች እንደ ሶዶምና ጎሞራ ሰዎች አለመጥፋታቸው አስገርሞኛል፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ ላለው ማሽቆልቆልና ሞት በቂ ምክንያት እንዳለ ተመልክቻለሁ፡፡ ጭፍን ፍላጎት አእምሮን ከመቆጣጠሩ የተነሳ በብዙዎች ዘንድ እያንዳንዱ የከበረ ነገር ለፍትወት ተሰውቷል፡፡{2SM 417.1}Amh2SM 417.1

    የመጀመሪያው ትልቁ ክፋት በምግብና በመጠጥ መሻትን አለመግዛት ነበር፡፡ ወንዶችና ሴቶች ለምግብ ፍላጎት ራሳቸውን ባሪያ አድርገዋል፡፡ {2SM 417.2}Amh2SM 417.2

    የአሳማ ሥጋ በብዛት ለምግብነት ከሚቀርቡ ነገሮች አንዱ ቢሆንም ለጤና እጅግ ጎጂ ነው፡፡ ዕብራውያን የአሳማን ሥጋ እንዳይበሉ እግዚአብሔር የከለከላቸው ዝም ብሎ ሥልጣኑን ለማሳየት ሳይሆን ለሰው ተገቢ የሆነ ምግብ ስላልሆነ ነበር፡፡ አካል ወደ ነቀርሳነት ሊለወጡ በሚችሉ የዕጢዎች እብጠት ይሞላል፣ በተለይ በሞቃት የአየር ንብረት አከባቢ የስጋ ደዌንና የተለያዩ ዓይነት በሽታዎችን ያስከትላል፡፡ በአካል ውስጥ የሚያስከትለው ጉዳት ከቀዝቃዛ የአየር ንብረት ይልቅ በሞቃታማ የአየር ንብረት አከባቢዎች እጅግ የከፋ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ አሳማ እንዲበላ አላዘጋጀም፡፡ አህዛቦች አሳማን በምግብነት ተጠቅመውበታል፣ የአሜሪካ ሕዝብም የአሳማ ሥጋን ጠቃሚ ምግብ እንደሆነ አድርገው እንደፈለጉ ተጠቅመውበታል፡፡ የአሳማ ሥጋ በተፈጥሮአዊ ሁኔታው ጥሩ ጣዕም ያለው አይደለም፡፡ ከምግብ ፍላጎት ጋር እንዲስማማ ለማድረግ ከፍተኛ ቅመም ይደረግበታል፣ ይህ ድርጊት ደግሞ መጥፎውን ነገር የከፋ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ የአሳማ ሥጋ ከሌሎች የሥጋ ዓይነቶች የበለጠ የደም ሁኔታን የከፋ ያደርጋል፡፡ አሳማን እንደልብ የሚመገቡ ሰዎች በበሽታ መጠቃታቸው የማይቀር ነገር ነው፡፡ ከቤት ውጭ ብዙ የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ሕይወታቸውን በቤት ውስጥ እንደሚያሳልፉ ወይም ተቀምጠው የመሥራት ልምድ እንዳላቸው ወይም የአእምሮ ሥራን እንደሚሠሩ ሰዎች ያህል የአሳማ ሥጋ የመብላትን መጥፎ ውጤት አይገነዘቡም፡፡ {2SM 417.3}Amh2SM 417.3

    ነገር ግን የአሳማ ሥጋን መመገብ የሚጎዳው የአካል ጤናን ብቻ አይደለም፡፡ ይህን ምግብ ከመጠቀም የተነሳ አእምሮ ይጎዳል፣ ረቂቅ የሆኑ የግንዛቤ ችሎታዎች ይደነዝዛሉ፡፡ ቆሻሻ የአካል ክፍሉ የሆነና ማንኛውንም የሚያስጠላ ነገር የሚመገብ የትኛውም ፍጡር ቢሆን ሥጋው ጤናማ ሊሆን አይችልም፡፡ የአሳማ ሥጋ የተሰራው ከሚመገቡት ነገር ነው፡፡ ሰዎች የእነሱን ሥጋ ከተመገቡ ደማቸውና ሥጋቸው በአሳማው ሥጋ አማካይነት ወደ እነርሱ በሚተላለፉ ቆሻሻዎች ይበከላሉ፡፡ {2SM 417.4}Amh2SM 417.4

    የአሳማን ሥጋ መመገብ ወደ ነቀርሳነት ሊለወጡ የሚችሉ የዕጢዎች እብጠትን፣ የሥጋ ደዌን እና ካንሰር ያለባቸውን እባጮች ያስከትላል፡፡ የአሳማን ሥጋ መመገብ በሰብዓዊ ዘር ላይ አሁንም ጥልቅ የሆነ ሥቃይ እያስከተለ ነው፡፡ የወረዱ የምግብ ፍላጎቶች ለጤና እጅግ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት ይስገበገባሉ፡፡ በምድር ላይ በከፍተኛ ደረጃ ያረፈው እና መላው ሰብዓዊ ዘር እየተሰማው ያለው እርግማን በእንስሳትም ላይ አርፏል፡፡ የእንስሳት መጠናቸውም ሆነ እድሜአቸው እጅግ ቀንሷል፡፡ ከሰዎች መጥፎ ልምዶች የተነሳ እጅግ ለከፋ ሥቃይ ተዳርገዋል፡፡ {2SM 417.5}Amh2SM 417.5

    ከበሽታ ነፃ የሆኑ ጥቂት እንስሳት ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ከብርሃን፣ ከንጹህ አየርና የተሟላ ምግብ እጥረት የተነሳ በከፍተኛ ደረጃ ለሥቃይ ተዳርገዋል፡፡ እንዲሰቡ በሚቀለቡበት ጊዜ በተዘጉ በረቶች ውስጥ እንዲወሰኑ ስለሚደረጉ እንዲንቀሳቀሱና በቂ አየር እንዲያገኙ አይደረጉም፡፡ብዙዎቹ ምስኪን እንስሳት በበረቶች ውስጥ የቀረውን ቆሻሻ መርዝ እንዲተነፍሱ ተትተዋል፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ ቆሻሻዎችን እየተነፈሱ ሳለ ሳንባዎቻቸው ጤናማ መሆን አይችሉም፡፡ በሽታው ወደ ጉበት ይተላለፍና የእንስሳው መላው የአካል ክፍሎች በበሽታው ይመረዛሉ፡፡እነዚህ እንስሳት ታርደው ለሽያጭ ይዘጋጁና የእነዚህን እንስሳት የተመረዘ ምግብ ሰዎች እንደልብ ይበላሉ፡፡ ብዙ በሽታዎች የሚመጡት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ነገር ግን ሰውነታቸውን የመረዘውና ብዙ ስቃይ ያመጣባቸው የበሉት ሥጋ እንደሆነ ቢነገራቸው ሰዎች ለማመን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ብዙዎች የሚሞቱት ሙሉ በሙሉ ሥጋ ከመብላታቸው የተነሳ ከመጡ በሽታዎች ነው፣ ነገር ግን ዓለም ጠቢብ መሆን የሚፈልግ አይመስልም፡፡ {2SM 418.1}Amh2SM 418.1

    ከእንስሳት የሚገኘውን ምግብ በሚመገቡ ሰዎች ላይ ምግቡ የሚያስከትለው ጉዳት ወዲያው አለመሰማቱ ጎጂ ላለመሆኑ ማረጋገጫ አይደለም፡፡ ሰዎች ለጊዜው ምንም ባይገነዘቡም ሥራውን በእርግጠኝነት በአካል ክፍሎች ውስጥ እየሰራ ነው፡፡ {2SM 418.2}Amh2SM 418.2

    እንስሳት በተዘጉ መኪናዎች ውስጥ ታጉረው ሙሉ በሙሉ አየርንና የፀሐይ ብርሃንን፣ ምግብንና ውኃን ተነፍገው ከተጠራቀመ ቆሻሻ የሚነሳውን የቆሸሸ አየር በመተንፈስ በሺሆች የሚቆጠሩ ማይሎችን እንዲጓጓዙ ስለሚደረጉ ከመዳረሻቸው ሲደርሱ አብዛኞቹ በከፊል ረሃብ ያጠቃቸው፣ የታፈኑ እና ሞት የሸተታቸው ስለሆኑ ሳይታረዱ ቢተው ኖሮ በራሳቸው ይሞቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራውን አራጅ ይጨርስና ሥጋቸውን ለገበያ ያዘጋጃል፡፡ {2SM 418.3}Amh2SM 418.3

    አብዛኛውን ጊዜ እንስሳት የሚታረዱት ወደ እርድ ቦታ ለመድረስ ረዘም ያለ ርቀት ከተነዱ በኋላ ነው፡፡ ደማቸው ፈልቷል፡፡ የደለቡ እና እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የተከለከሉ ስለሆኑ ረዥም መንገድ በሚጓዙበት ጊዜ ይደክማሉ፣ ይዝላሉም፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ታርደው ለገበያ ይቀርባሉ፡፡ ደማቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣ ስለሆነ የእነዚህን እንስሳት ሥጋ የሚመገቡ መርዝ እየተመገቡ ናቸው፡፡ የእነዚህን እንስሳት ሥጋ ከሚመገቡ ሰዎች መካከል በአንዳንዶቹ ላይ ወዲያውኑ ጉዳት ባይደርስባቸውም በሌሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም ስለሚያስከትልባቸው በትኩሳት፣ በኮሌራ፣ ወይም ምንነቱ በማይታወቅ በሽታ ይሞታሉ፡፡ ከገዦቹም ቢሆን ጉዳዩ ሁል ጊዜ የተሰወረ ባይሆንም ሻጮቹ ግን በሽተኛ መሆናቸውን የሚያውቋቸው ብዙ እንስሳት በከተማ ገበያዎች ላይ ይሸጣሉ፡፡ በተለይም በታላላቅ ከተማዎች ውስጥ ይህ በከፍተኛ ደረጃ የሚፈጸም ሲሆን ሥጋ ተመጋቢዎች ግን በሽተኛ እንስሳትን እየተመገቡ መሆናቸውን አያውቁም፡፡ {2SM 418.4}Amh2SM 418.4

    አንዳንድ ወደ እርድ ቦታ የሚያመጡአቸው እንስሳቶች ሊሆን ያለውን የሚገነዘቡ ይመስል እጅግ ይቆጡና ያብዳሉ፡፡ በዚያ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ይገደሉና ሥጋቸው ለገበያ ይዘጋጃል፡፡ ሥጋቸው መርዝ ስለሆነ በበሉት ሰዎች ላይ የጡንቻ መሸማቀቅን፣ መንቀጥቀጥን፣ የሚጥል በሽታንና ድንገተኛ ሞትን ያስከትላል፡፡ ሆኖም የዚህ ሁሉ ሥቃይ መንስኤው ሥጋ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ አንዳንድ እንስሳት ወደ እርድ ቦታ ሲመጡ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተይዘው ነው የሚመጡት፡፡ ከፍተኛ ሥቃይ ይደርስባቸዋል፣ ይህን የመሰለ እጅግ ከባድ ሥቃይ ለብዙ ሰዓታት ከደረሰባቸው በኋላ ይታረዳሉ፡፡ አሳማዎች ወረርሽኙ በላያቸው እያለ ለገበያ ተዘጋጅተው በመቅረባቸው እና መርዘኛ ሥጋቸው ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን በማዛመቱ ምክንያት በብዙ ሰዎች ላይ ሞትን አስከትሏል፡፡Amh2SM 419.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents