Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «እገስጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ»

    የቤተ ክርስቲያን አባላት በግል ደረጃ በራቸውን ለኢየሱስ የሚከፍቱለት ከሆነ የበለጸጉ በረከቶቹን ሊሰጣቸው እየመጣ ነው፡፡ ባቢሎን ብሎ አይጠራቸውም፣ እንዲወጡም አይጠይቃቸውም፡፡ ነገር ግን እንዲህ ይላል፣ «የምወዳቸውን ሁሉ እገስጻቸዋለሁ እቀጣቸዋለሁም» (በማስጠንቀቂያና በወቀሳ መልእክቶች) (ራዕይ 3፡ 19)፡፡ ተግሳጾቹን አውቃቸዋለሁ፡፡ ማስጠንቀቂያዎቹን የሰጠሁት የጌታ መንፈስ እንድሰጥ ስላስገደደኝ ነው፣ ተግሳጾቹንም የተናገርኩት የተግሳጽ ቃላትን ጌታ ስለሰጠኝ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን እንዳስተላልፍ የተሰጠኝን ጠቅላላውን የእግዚአብሔር ምክር ከማወጅ አልሸሸሁም፡፡ {2SM 67.1}Amh2SM 67.1

    በእግዚአብሔር ፍርሃትና ፍቅር እላለሁ፣ ጌታ ከማፈግፈጋቸው ሁሉ ሊመልሳቸውና ሊፈውሳቸው የፍቅርና የምህረት ሀሳብ እንዳለው አውቃለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ እንድትሰራ የሚፈልገው ሥራ አለው፡፡ ባቢሎን ተብለው መጠራት የለባቸውም፣ ነገር ግን የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን ተብለው መጠራት አለባቸው፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ሕያው መልእክትን የሚያውጁ ሕያዋን መልእክተኞች ሊሆኑ ነው፡፡ {2SM 67.2}Amh2SM 67.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents