Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እያደገ በመምጣት ላይ ያለ ልልነት (ግድ የለሽነት)

    «ወንድም ኤች ትምህርቱን ያገኘው ከየት ነው?” ከሚለው ጥያቄ ጋር እነዚህን የማረጋገጫ ጥቅሶችን አቀርባለሁ፡፡ ትምህርቱን ያገኘው ከባትል ክሪክ ነው፡፡ አክብሮት መስጠትን በተመለከተ እግዚአብሔር የሰጠው ብርሃን ሁሉ እያለ አገልጋዮች፣ በትምህርት ቤቶቻችን ያሉ ርዕሳነ-መምህራንና አስተማሪዎች በቃላቸውና በሕይወት ምሳሌነታቸው ልክ ፈሪሳውያን ያደርጉ እንደነበረ ሁሉ በአምልኮ ሰዓት ወጣቶቻችን ቀጥ ብለው እንዲቆሙ ሊያስተምሩ ይችላሉን? ይህ የእነርሱን የራስ ብቃትና ለራሳቸው የሚሰጡትን ዋጋ እንደሚያሳይ አድርገን ማየት እንችላለንን? እነዚህ ባሕርያት ጎልተው ሊወጡ ነውን?Amh2SM 313.3

    «ጻድቃን እንደሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ እንዲህ ሲል፡- ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፣ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ ነበር፡፡ ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፡- እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፣ ቀማኞችና አመጸኞች አመንዝሮችም፣ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እፆማለሁ፣ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ» (ሉቃስ 18፡ 9-12)፡፡ ልብ በሉ፣ ፈሪሳዊው ራሱን ዝቅ ያላደረገና ለእግዚአብሔር አክብሮት ያልነበረው፣ በራሱ ጽድቅ የሚተማመን ነበር፤ ነገር ግን ኩራት በተሞላበት በራስ ብቃት ስሜት ተሞልቶ በመቆም የሚያደርጋቸውን መልካም ተግባራት ሁሉ ለጌታ ነገረ፡፡ «ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ ይህን ጸለየ” (ሉቃስ 18፡ 11)፤ ጸሎቱ ከራሱ አልፎ ወደ ላይ አልሄደም፡፡ Amh2SM 313.4

    «ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ እንኳን ሊያነሳ አልወደደም፣ ነገር ግን፡- አምላክ ሆይ፣ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር፡፡ እላችኋለሁ፣ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፣ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል” (ሉቃስ 18፡ 13፣ 14)፡፡Amh2SM 313.5

    ወንድሞቻችን ብቸኛና ሕያው ወደሆነ አምላክ ሲቀርቡ አህዛብ ለጣዖት አምላኮቻቸው ከሚያሳዩት አክብሮት ያነሰ አክብሮትና ፍርሃት እንደማያሳዩ ተስፋ እናደርጋለን፤ እንዲህ ካልሆነ ግን የመጨረሻው ውሳኔ በሚሰጥበት ቀን እነዚህ ሰዎች ይፈርዱብናል፡፡ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የመምህርነት ቦታን ለያዙት ሰዎች እናገራለሁ፡፡ ወንዶችና ሴቶች ሆይ፣ አክብሮት የጎደላችሁ በመሆንና በጉረኝነታችሁ እግዚአብሔርን አታዋርዱ፡፡ በፈሪሳዊነታችሁ ቆማችሁ ጸሎታችሁን ወደ እግዚአብሔር አታቅርቡ፡፡ በራሳችሁ ብርታት አትተማመኑ፡፡ በራሳችሁ ብርታት አትደገፉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት በጉልበታችሁ በመንበርከክ ስገዱለት፡፡Amh2SM 314.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents