Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ትችትና ፍሬዎቹ

    ጌታ ሕዝብ አለው፣ እሱም እየመራቸው ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች በእርግጠኝነት ቢኖሩም ቤተ ክርስቲያንን እንድትመራ ኢየሱስ በመሪነት ቦታ ላይ አላስቀመጠህም፡፡ አመለካከትህን ካልለወጥክ በስተቀር መዳን አትችልም፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ወደማግኘት ሊመልስህ የሚችልበት ብቸኛው ቅድመ ሁኔታ «ንስሃ ግባ የቀደመውንም ሥራ ሥራ» (ራዕይ 2፡5) የሚለው ነው፡፡ ጌታ ይቅር የሚላቸውን ሰዎች መጀመሪያ ለኃጢአታቸው ተጸጻች ያደርጋቸዋል፡፡ በአንተ ሁኔታ ከጠላት ወጥመድ ድነህ ከሆነ በልብ ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ትክክለኛ የሆነ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ መርሆዎችህ የተበከሉ ስለሆኑ በአንተ ላይ ያለኝ ተስፋ የመነመነ ነው፡፡ የማታለል ባሕርይ ያለህ ሰው ነህ፤ እንዲህም ሆኖ ለራስህ ትልልቅ ነገሮችን ታስባለህ፡፡ {2SM 83.3}Amh2SM 83.3

    የሶስተኛው መልአክ መልእክት በኃይል ወደ ፊት እየገሰገሰ ሳለ እንደ ተወካይ ሰው ሆነህ የተለየ ሚና እንድትጫወት በእግዚአብሔር እንደተመረጥክ አድርገህ እንድታስብ በማድረግ ሰይጣን ተሳክቶለታል፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነት ትክክል አይደለም፣ እግዚአብሔር ወደ ስህተት አይመራም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኃላፊነት ባላቸው ሰዎች ላይ የምታያቸውን ስህተቶች እጅግ በመጠቀም ለእነርሱ የተሰጠውን ተግሳጽ ታጎላለህ፡፡ ይህን የምታደርገው እነዚህ ሰዎች ከአንተ ጋር ስለማይስማሙ ወይም እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ካበራው ብርሃን በላይ አድርገህ የያዝከውን ኃይማኖታዊ ልምምድ ትክክል ነው ብለው ስለማይቀበሉ ነው፡፡ ሌሎችን እንድትኮንን በፍርድ ወንበር ላይ ማን አስቀመጠህ? እግዚአብሔር ሳይሆን ራስህ ነህ፡፡. . .{2SM 84.1}Amh2SM 84.1

    ወንድሞችህን በመኮነን የተናገርካቸው ቃላት ጥቂት አልነበሩም፡፡ መኮነን ምግብህና መጠጥህ ይመስላል፡፡ መንፈሳዊ ልምምድህ እንዲመገብ ከሰጠኸው ነገር የተሰራ ነው፡፡ ደግሞ የውሸት ሀሳቦችህን በቤተሰብህና በሚሰማህ ሁሉ ፊት ማቅረብ ትወዳለህ፡፡ ታዲያ ቅዱስ ያልሆነ እርሾ ሥራውን በመሥራቱ መደነቅ ትችላለህን? ከፈለግክ ይህን ስድብ ልትለው ትችላለህ፣ ነገር ግን ጌታ ያሳየኝ ነገር ነው፡፡ የአና ራዕዮች የሚገቡት የአንተን የስህተት ሀሳቦች ለማጽናት ነው፡፡ እያሳሳትክና እየሳትክ ነህ፡፡ ሰይጣን ነገሮችን በደንብ ስላቀናጀ ነፍስህን በውሸት አጥረሃል፡፡ --Letter 12, 1890. {2SM 84.2}Amh2SM 84.2