Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የክርስቶስ ምሳሌ

    በእያንዳንዱ እርምጃ ነፍሱን ዝቅ በማድረግ ቃሉን በቅርበት የሚያጠና ተማሪ የሆነ ማንም ቢሆን ወደ ጽንፍ እሄዳለሁ ብሎ አይፍራ፡፡ ክርስቶስ በእምነት በውስጡ ማደር አለበት፡፡ ምሳሌያቸው የሆነው እሱ ራሱን የገዛ ነው፡፡ በትህትና ተመላልሷል፡፡ እውነተኛ የሆነ ክብር ነበረው፡፡ ትዕግሥት ነበረው፡፡ ጽድቅ በእምነትን የሚቀበሉ እነዚህ ባሕርያት ካሉን ጽንፈኞች አይኖሩም፡፡. . . {2SM 22.2}Amh2SM 22.2

    ሁልጊዜ ሕግና ወንጌል ያላቸውን የቅርብ ግንኙነት ለመጠበቅ የክርስቶስ ምሳሌ በፊታችን ነው፡፡ ሁለቱም ሊለያዩ አይችሉም፡፡ ይህ የክርስቶስ ባሕርይ ስለነበረ የመንፈስ እርጋታና ራስን መቆጣጠር ማደግና ያለመሰልቸት መጠበቅ አለባቸው፡፡ ለእምነታቸው እጅግ አነስተኛ የሆነ መሠረት እንኳን ሳይኖራቸው «እኔ ቅዱስ ነኝ፣ እኔ ኃጢአት የለብኝም” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገውና አስረዝመው የድፍረት ማስመሰልን የሚያሳዩ ኃይለኛ ቃላቶችን የሚናገሩ ሀሰተኛ ኃይማኖተኞችን እንሰማቸዋለን፡፡ የእውነት ሁሉ ደራሲ ከሆነው ውስጥ ጩኸት ያለበትን የእምነት አቤቱታዎች አንሰማም፣ ወይም ከፍተኛ የሆኑ አካላዊ መወራጨትንና እንቅስቃሴዎችን አናይም፡፡ {2SM 22.3}Amh2SM 22.3

    በእርሱ ውስጥ የመለኮት ሙላት በአካል እንዳደረበት አስታውሱ፡፡ ክርስቶስ በእምነት በልባችን ካደረ፣ የእርሱን አኗኗር በመመልከት እንደ ኢየሱስ ንጹህ፣ ሰላማዊ፣ እና ያልረከስን ለመሆን እንሻለን፡፡ በባሕርያችን ክርስቶስን እናሳያለን፡፡ ብርሃንን የምንቀበልና እዚያው የምናስቀር ሳንሆን ወደ ሌሎች እናስተላልፋለን፡፡ ኢየሱስ ለእኛ ምን እንደሆነ የበለጠውን ግልጽና ጉልህ አመለካከቶች ይኖሩናል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ውስጥ የነበሩ ሚዛናዊነት፣ ደስተኛነት እና ቅንነት በእኛ ሕይወት ውስጥ በርተው ይታያሉ፡፡ --Manuscript 24, 1890. {2SM 22.4}Amh2SM 22.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents