Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የከበረውን ነገር ከማይታመን ነገር (ከሞኝነት) ጋር መቀላቀል

    አሁን የምልክልህን ማስጠንቀቂያ ከእግዚአብሔር ተቀብያለሁ፡፡ አና ፊሊፕስ የተሰጣት ማደፋፈሪያ ሊሰጣት የማይገባ ማደፋፈሪያ ነበር፤ ለእሷ ከፍተኛ ጉዳት ነበር፣ በማታለያ ውስጥ አስሯታል፡፡ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ማናቸውም ቢሆኑ በእነዚህ ራዕዮች በሚባሉ ነገሮች ለመደፋፈር ዝግጁ በመሆናቸውና በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ መለኮታዊ መረጃዎችን እንደሚያዩ በማሰባቸው አዝናለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች ለወቅቱ አስፈላጊ የሆነውን ስራ ለመስራት ትክክለኛ ባሕርይ ያላቸው አይደሉም፡፡ ቅዱስና ሰማያዊ የሆኑ ነገሮችን ለመግለጽ ሕጻን የሚጠቀማቸው ምሳሌዎችና መግለጫዎች ጥቅም ላይ ውለዋል፣ የከበረውን ከማይታመን ነገር ጋር መቀላቀል አለ፡፡ ሥራው ታላቅ ቅድስና ያለው ቢመስልም ነፍሳትን ለማጥመድና ወደ ስህተት ለመምራት የተሰላ ነው፡፡ ... {2SM 89.2}Amh2SM 89.2

    የተለያዩ ነገሮች ከእግዚአብሔር የመጡ ራዕዮች እንደሆኑ በመነገር ይመጣሉ፣ ነገር ግን ከትዕቢተኛና ከተታለለ አእምሮ የሚፈልቁ ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች በቀደምት ልምምዶቻችን መጋፈጥ ነበረብን፡፡ በእግዚአብሔር እንደተመሩና ከእርሱ እንደተማሩ በመናገር የሚያውጁት የተለየ መልእክት እንዳላቸው ይናገሩ የነበሩ ወጣቶችና ሕጻናት እንዲሁም በእድሜ የበሰሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ በአንዳንድ ነጥቦች እውነትን ይዘው በሌሎች ነጥቦች ላይ ደግሞ ስህተትን ይዘው በየአቅጣጫው ብቅ ይሉ ነበር፡፡ ለአመታት ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል መልእክት ይመጣልኝ ነበር፣ «ወደ ስህተት መንገዶች ስለሚመሩ አትመኑአቸው፡፡ እግዚአብሔር አልላካቸውም፡፡” --Letter 4, 1893. {2SM 90.1}Amh2SM 90.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents