Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እየሞተ ካለ ሰው ጋር የተደረገ ውይይት

    በዚህ መስመር ከገጠሙኝ ሥራዎች እጅግ ከባድ የነበረው ከአንድ ከማውቀው ጌታን መከተል ከፈለገ ሰው ጋር የነበረኝ ግንኙነት ነበር፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አዲስ ብርሃን እያገኘ እንደሆነ አስቦ ነበር፡፡ በጣም ታሞ ስለነበር በቅርቡ መሞቱ የማይቀር ነበር፡፡ እያደረገ የነበረውን ነገር እኔ እንድነግረው እንዳያደርገኝ በማለት ልቤ ተስፋ ያደርግ ነበር፡፡ አመለካከቱን የነገራቸው ሌሎች ሰዎች በታላቅ ጉጉት አዳምጠውታል፣ አንዳንዶቹም መገለጥ ተሰጥቶታል ብለው አስበዋል፡፡ ሰንጠረዥ ሰርቶ ነበር፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመውሰድ ጌታ በ1894 ዓ.ም ላይ የሚመጣ ይመስለኛል የሚል ሀሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ ለብዙዎች እሱ ያቀረበው ምክንያት እንከን የለሽ መሰላቸው፡፡ ታሞ በተኛበት ክፍል ውስጥ ሆኖ ስለሰጣቸው ኃይለኛ የሆኑ ልባዊ ምክሮቹ ተናገሩ፡፡ እጅግ አስደናቂ የሆኑ እይታዎች በፊቱ አለፉ፡፡ ነገር ግን እሱ ለተቀበለው መገለጥ ምንጩ ምንድን ነበር? ምንጩ ህመሙን ለማስታገስ የተሰጠው ሞርፊን የሚባል መድሃኒት (ዕፅ) ነበር፡፡ {2SM 113.1}Amh2SM 113.1

    ወደ አውስትራሊያ ከመምጣቴ በፊት በሚሺጋን ግዛት ላንሲንግ በተባለ ቦታ በነበረው መንፈሳዊ ስብሰባ ይህን አዲስ ብርሃን በተመለከተ በግልጽ መናገር ነበረብኝ፡፡ ለሰዎቹ የሰሟቸው ቃላቶች የእውነት መገለጥ አለመሆናቸውን ነገርኳቸው፡፡ የታይታ እውነትን ያቀረበው አስደናቂ ብርሃን መጽሐፍ ቅዱስን በስህተት ከመጠቀም የመጣ ነበር፡፡ በ1894 ዓ.ም የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፍፃሜ አይደርስም፡፡ ለእኔ የተሰጠኝ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ የሚል ነበር፡- «ይህ እውነት አይደለም፣ ነገር ግን ወደ ስህተት መንገድ ይመራል፤ አንዳንዶች በዚህ አቀራረብ ላይ ግራ ይጋቡና እምነትን ይተዋሉ፡፡» . . . {2SM 113.2}Amh2SM 113.2