Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ታማኝ ረዳት ለነበረችው የተሰጡ የርኅራኄና የተስፋ መልእክቶች

    {በ1879 ዓ.ም የሚስስ ኋይትን ሰራተኞች የተቀላቀለችው እና ሚስስ ኋይት በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ እና በአውስትራሊያ ትሰራ በነበረችበት ጊዜ ከእሷ ጋር ለሃያ አንድ አመታት አብራ የሰራች ሚስ ማሪያን ዴቪስ በ1903 ዓ.ም የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ያዛትና ከአንድ አመት በኋላ የሕይወት ሥራዋን ወደ ድምዳሜ አመጣች፡፡ ሚስ ዴቪስ ሚስስ ኋይት እጅግ የምትወዳት በጣም ታማኝና እምነት የሚጣልባት የስነ-ጽሁፍ ረዳት ነበረች፡፡ እዚህ ላይ የቀረበው ሀሳብ ሚስስ ኋይት ለሚስ ዴቪስ በመጨረሻዎቹ የህመሟ ሁለት ወራት ውስጥ ከጻፈቻቸው የርህራሄ፣ የተስፋና የምክር መልእክቶች የተወሰደ ነው፡፡ --አሰባሳቢዎች}፡፡Amh2SM 251.1

    ሜልሮስ፣ ማሳሹሴትስ

    ነሐሴ 17 ቀን 1904 ዓ.ም

    ውድ እህት ማሪያን ዴቪስ፡-

    እቤት መሆን ያስደስተኛል፣ ነገር ግን ምን ዓይነት ስብሰባዎችን ለመካፈል እንደምስማማ እርግጠኛ አይደለሁም፤ ስለዚህ ለማድረግ የምንችለውን በጣም የተሻለ ነገር እናደርጋለን፡፡….Amh2SM 251.2

    ጌታ እንዲያበረታሽ እየጠየቅኩ ነኝ፡፡ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሆንሽ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እጅሽን በክርስቶስ እጅ ውስጥ በማድረግ ጌታን አጥብቀሽ ያዢ፡፡. . . .Amh2SM 251.3

    ማሪያን ሆይ፣ ተስፋ መቁረጥ የለብሽም፡፡ የአንቺ ጉዳይ በጌታ እጅ ስለሆነ ሕክምናን በተመለከተ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች እንዲያደርጉልሽ ጉዳይሽን ለዶ/ር ኤ እና ዶ/ር ቢ አሳልፈሽ ስጪ፡፡ አሁን ያለብሽን ሕመም ስትቋቋሚ በሰዎች እጆች ውስጥ ማስቀመጥ የምንፈልጋቸው ሌሎች መጻሕፍት አሉን፡፡ የሚያሳምምሽ እንኳን ቢሆን ምግብ መብላትሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ ከምግብ በራቅሽ ቁጥር እየደከምሽ ትሄጂያለሽ፡፡ …እግዚአብሔር እኛን የሚፈልገው እንዴት ነው? አምላካችን ብርቱ አይደለምን? የእርሱን ብርታት አጥብቀሽ አትይዥምን? ብለን እንጠይቃለን፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንደሚረዳሽ ማንኛውም ሕያው ፍጡር ሊረዳሽ አይችልም፡፡ በእርሱ ታመኚ፡፡ እርሱ ይጠነቀቅልሻል፡፡ -- Letter 378, 1904.Amh2SM 251.4

    ሜልሮስ፣ ማሳሹሴትስ

    ነሐሴ 24 ቀን 1904 ዓ.ም

    ውድ እህት ማሪያን ዴቪስ፡-

    አንድም የመሸበር ሀሳብ ወደ አእምሮሽ አይምጣ፡፡ በጣም በመታመምሽ አዝናለሁ፣ ነገር ግን ጤንነትሽን ለመመለስ በአንቺ በኩል ማድረግ የምትችዪውን ሁሉ አድርጊ፡፡ ወጪዎች በሙሉ እንዲሸፈኑ አደርጋለሁ፡፡ እኔም ጤንነት አይሰማኝም፤ በሰረገላ ካልሆነ በስተቀር ትንሽ ርቀት እንኳን መሄድ አልችልም፡፡ በመኪና ረጅም ጉዞ የማድረግ ድፍረት የለኝም፡፡ አንቺና እኔ በሕይወት እስካለን ድረስ ቤቴ ቤትሽ ነው፡፡ . . .Amh2SM 251.5

    ማሪያን ሆይ፣ ከቤት ርቄ በነበርኩበት ሰዓት ሁሉ ምግብ ደስ አይለኝም ነበር፣ ነገር ግን ካልበላሁ ምንም ማድረግ ስለማልችል ምግብ መብላት አልተውኩም ነበር፡፡ በሕይወት መኖር ስላለብኝ ደስ ሳይለኝ እንኳን በልቻለሁ፡፡ ወደዚህ ከመጣሁ ወዲህ ምግብ ደስ ብሎኝ እበላለሁ፡፡ በእግዚአብሔር በመታመን ለአንቺና ለራሴ እማጸነዋለሁ፡፡ ስጋትና ጭንቀት ሊይዘን አይገባም፡፡ ብቻ በእግዚአብሔር ታመኚ፡፡ ከአንቺና ከእኔ የሚጠበቀው ወደ እርሱ የሚመጡትንና የሚታመኑበትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው በሚችለው ማመንና መታመን ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ አንቺንና እኔን «እጄን አጥብቃችሁ ያዙ» ይለናል፡፡ የአንቺም የእኔም አዳኝ ስለሆነው ኢየሱስ ትክከለኛ የሆኑ ሀሳቦችን እንድታስቢ ተደፋፍረሻል፡፡ የእሱን ክብር የሚጨምረውን ነገር ለማድረግ በሚያስችልሽ በእያንዳንዱ አጋጣሚ ሐሴት አድርገሻል፣ የመጨረሻው የጌታ መለከት ሲነፋ ወደ እግዚአብሔር ከተማ ትመሪያለሽ፣ እውነተኛ በሆነ ደስታ አቀባበል ይደረግልናል፡፡ Amh2SM 252.1

    ማሪያን ሆይ፣ ሰዎች መገለጥን እንዲረዱና ትክክለኛ የሆነ ልምምድ እንዲኖራቸው ለማድረግ ትክክለኛ የሆነ አስተምህሮን ከሰብአዊ ነፍሶች ጋር ለማገናኘት ከእኔ ጋር አንድነት ፈጥረሻል፡፡ «ትክክለኛ የሆኑ ቃላት” ከወርቅ፣ ከብርና ከማንኛውም ምድራዊ ብልጭልጭ ይልቅ የበለጠ ዋጋ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እውነትን ወደሻል፡፡ ጌታችንና አዳኛችን እየደረሰበት ያለው ትልቅ የሆነ ንቀት በጣም አሳዝኖሻል፡፡ ከእግዚአብሔር አእምሮ ጋር መመሳሰል እንዴት ያለ ድንቅ ነገር ነው! ስትናፍቂው የኖርሽው ይህንን ነበር፡፡ ለሰው ከእግዚአብሔር እውነት የሚበልጥ የሚያድን ሌላ ከፍታ የለም፡፡ Amh2SM 252.2

    “ነፍሴ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ባርኪ፣ አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን” ( መዝ. 103፡ 1)፡፡ አሁን አንቺና እኔ በየቀኑ የምሥጋና አገልግሎት እንዲኖረን እማጸንሻለሁ፡፡ ለእምነት ጸሎት ምላሽ ሕይወትሽን ለእነዚህ ብዙ አመታት ስላቆየ ምሥጋና አይገበውምን? በድካምሽ ጊዜ ራስሽን በእሱ እጆች አሳልፈሽ ስጪና ሙሉ በሙሉ በእርሱ ታመኚ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የሕይወታችን ታላቅ ደንብ፣ በእጃችን ውስጥ ያለ ሰማያዊ የችግር መፍትሄ አድርገን እንወስዳለን፡፡ አንቺና እኔ አንድ ላይ ሆነን ወደ ሰዎች አእምሮ እውነተኛ የአስተምህሮ ዓይነትን፣ የሚዋሃድ ቅድስናን፣ ምህረትን፣ እውነትንና ፍቅርን ለማምጣት ጥረት አድርገናል፡፡ ነፍሳት የተዋሃደ ፍቅርንና ቅድስናን፣ በቀላሉ ሲገለጽ የልብ ክርስትናን እንዲያስተውሉ ለማድረግ እነዚህን ነገሮች በትህትና ለማቅረብ ጥረት አድርገናል፡፡ ክርስትናን በዚህች ዓለም ላይ የሰው ሕይወት ዘውድና ክብር፣ የእግዚአብሔር ውድና ክቡራን የዳኑ ሰዎች እሱ ሊያዘጋጅልን ወደ ሄደው ቤታችን፣ ወደ እርሱ ከተማ ለመግባት መዘጋጃ አድርገን ለማቅረብ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ አድርገናል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ እርሱን እናወድስ፡፡ Amh2SM 252.3

    ማሪያን ሆይ፣ ምድራዊው ሐኪምሽ እና ታላቁ የሕክምና ሚስዮናዊው ምግብ እንድትበዪ ስለሚፈልጉ እባክሽን ብዪ፤ እህት ኤም ጄ ኔልሰን የምትጠይቂውን ማንኛውንም ነገር ታገኝልሻለች፡፡ ሥራውን መስራትሽን እንድትቀጥዪ ሕይወትሽ ቢተርፍ ከእኔ የበለጠ የሚደሰት ሰው አይኖርም፤ ነገር ግን ለአንቺም ሆነ ለእኔ በጌታ የማንቀላፋት ጊዜ ደርሶ ከሆነ አካላችን የሚፈልገውን ምግብ በመንፈግ ሕይወታችንን ማሳጠር የለብንም፡፡ ውዴ ሆይ፣ አሁን ብትፈልጊም ባትፈልጊም ምግብን በመመገብ ለመፈወስ የራስሽን ድርሻ ፈጽሚ፡፡ ለመፈወስ ማድረግ የምትችዪውን ሁሉ አድርጊ፣ ከዚያ በኋላ ማረፍሽ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ከሆነ አንቺ የምትችዪውን አድርገሻል፡፡ ልፋቶችሽን አደንቃለሁ፡፡ ማሪያን ሆይ፣ ታላቁ ሐኪም ኢየሱስ ሊፈውስሽ ስለሚችል ጌታን አመስግኚ፡፡ እወድሻለሁ፡፡ --Letter 379, 1904.Amh2SM 253.1

    ኮሌጅ ቪው፣ ነብራስካ

    መስከረም 16 ቀን 1904 ዓ.ም

    ውድ እህት ማሪያን፡-

    የአንቺን ጉዳይ በፊቴ አስቀምጣለሁ፣ አእምሮሽ ስለተጨነቀም አዝናለሁ፡፡ በእኔ ችሎታ ሥር ያለ ነገር ቢሆን ኖሮ አጽናናሽ ነበር፡፡ ክቡር አዳኝ የሆነው ኢየሱስ በችግርሽ ጊዜያቶች ብዙ ጊዜ በአጠገብሽ ረዳትሽ አልነበረምን? መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኚ፣ ነገር ግን መጨነቅሽን አቁሚ፡፡ ይህ ነገር አንቺ ራስሽ ለብዙዎች የተናገርሽው ነገር ነው፡፡ ልክ የአንቺ እንደነበረው ሁሉ ያልታመሙ ሰዎች ቃላት ያጽናኑሽ፣ ጌታ ይርዳሽ የሚለው ጸሎቴ ነው፡፡ Amh2SM 253.2

    መሞትሽ የጌታ ፈቃድ ከሆነ ሁለመናሽን ማለትም አካልሽን፣ ነፍስሽን እና መንፈስሽን ቅንና መሃሪ በሆነው በእግዚአብሔር እጅ አሳልፈሽ መስጠት መልካም ዕድል እንደሆነ ሊሰማሽ ይገባል፡፡ አንቺ እንደምትገምችው እሱ የኩነኔ ስሜቶች የሉትም፡፡ ጌታ እንደማይወድሽ አድርገሽ ማሰብሽን እንድታቆሚ እፈልጋለሁ፡፡ ራስሽን ባለመቆጠብ እሱ ባዘጋጀው የምህረት መሰናዶ ላይ ጣዪ፡፡ ግብዣውን እስክትሰሚ ድረስ እየጠበቀሽ ነው፡፡ …እግዚአብሔር በጭካኔ እንዲቀጣሽ የሚያደርግ ምንም ነገር እንዳደረግሽ ሊሰማሽ አይገባም፡፡ ከአንቺ የተሻለ አውቃለሁ፡፡ ፍቅሩን እመኚና በቃሉ ያዥው፡፡ …አእምሮአችንን ጥርጣሬና አለማመን ሊቆጣጠር አይገባም፡፡ የእግዚአብሔርን ታላቅነት መፍራት እምነታችንን ግራ ሊያጋባው አይገባም፡፡ ራሳችንን በትህትናና በየዋህነት ዝቅ ማድረግ እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ክርስቶስ ከሰብአዊነት ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና ሰብአዊ ፍጡራን ፍጹም መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት የንጉሥነት ልብሱንና ዘውዱን ተወ፡፡ የፍቅሩን ማረጋገጫ ሊሰጠን የምህረትን ልብስ ለብሶ በዓለማችን ውስጥ ፍጹም ሕይወትን ኖረ፡፡ አለማመንን ሊያጠፋ የሚችል ነገር አድርጓል፡፡ በሰማይ ጉባኤ የነበረውን ከፍተኛ ሥልጣን በመተው ሰብአዊ ተፈጥሮን ለመቀበል ዝቅ አለ፡፡ የእርሱ ሕይወት የእኛ ሕይወት ምን መሆን እንዳለበት ምሳሌ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ታላቅነት መፍራት በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያለንን እምነት እንዳያጠፋ ክርስቶስ የሀዘን ሰውና መከራን የሚያውቅ ሆነ፡፡ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ልብ ቅዱስ ሙዚቃን የሚያፈልቅ የተቀደሰ በገና ይሆናል፡፡--Letter 365, 1904.Amh2SM 253.3

    ኮሌጅ ቪው፣ ነብራስካ

    መስከረም 26 ቀን 1904 ዓ.ም

    ውድ እህት ማሪያን፡-

    እንደገና አንድ ጊዜ እስክንገናኝ ድረስ በሕይወት እንድትጠበቂ እንጸልያለን፣ ነገር ግን በሕይወት ትኖሪያለች እንጂ አትሞችም፡፡. . . .Amh2SM 254.1

    ወደ ኢየሱስ ተመልከቺ፡፡ በሕይወት ብትኖሪም ብትሞቺም በኢየሱስ ታመኚ፡፡ እሱ አዳኝሽ ነው፡፡ እሱ ሕይወት ሰጭያችን ነው፡፡ በኢየሱስ ካንቀላፋሽ ከመቃብር አስነስቶ ግርማ ወዳለው ዘላለማዊነት ያመጣሻል፡፡ ከአሁን ጀምሮ እሱ ሰላምን፣ መጽናናትን፣ ተስፋንና ደስታን ይስጥሽ፡፡ Amh2SM 254.2

    መታመንሽን ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ አድርጊ፡፡ አይተውሽም አይጥልሽምም፡፡ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ ይልሻል፡፡ ማሪያን ሆይ፣ ከእኔ ቀድመሽ ከሄድሽ እዚያ አንዳችን ሌላችንን እናውቃለን፡፡ እንደታየን እናያለን እንደታወቅን ደግሞ እናውቃለን፡፡ ብቻ የክርስቶስ ሰላም ወደ ነፍስሽ እንዲመጣ ፍቀጂ፡፡ እሱ ለገባው ቃል ታማኝ ስለሆነ አንቺም በእርሱ ላይ ባለሽ መታመን እውነተኛ ሁኚ፡፡ ደካማ የሆነ ድንጉጥ እጅሽን በእሱ ጽኑ እጅ ውስጥ አድርጊና እሱ እንዲይዝሽና እንዲያበራታሽ፣ እንዲያስደስትሽና እንዲያጽናናሽ ፍቀጅለት፡፡ ይህን ስፍራ ለመልቀቅ አሁን እዘጋጃለሁ፡፡ ምነው በዚህች ቅጽበት አብሬሽ በሆንኩ! አብዝቼ እወድሻለሁ፡፡--Letter 382, 1904.Amh2SM 254.3