Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተጽናኑ

    ለተሰቃዩ ሰዎች በትንሣኤ ማግስት ተስፋ ተጽናኑ እላለሁ፡፡ ስትጠጡ የነበራችሁት ውኃ የእሥራኤል ልጆች በምድረ በዳ እንደጠጡት እንደ ማራ ውኃ መራራ ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ በፍቅሩ ጣፋጭ ያደርገዋል፡፡ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት የገጠማቸውን አሳዛኝ ችግር ባቀረበ ጊዜ የሰጣቸው አዲስ መፍትሄ ሳይሆን መጀመሪያውኑ በእጃቸው ወደነበረው ነበር ትኩረታቸውን የሳበው፤ ያውም ውኃውን ጣፋጭና ንጹህ ማድረግ እንዲችል እሱ የፈጠረውን ቁጥቋጦ ቆርጦ ውኃው ውስጥ እንዲጨምር ነበር፡፡ ይህ በተደረገ ጊዜ ሥቃይ ላይ የነበረው ሕዝብ ውኃውን ያለ አንዳች ችግር በደስታ መጠጣት ቻለ፡፡ Amh2SM 273.2

    እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ቁስል መፈወሻ ቅባት አዘጋጅቷል፡፡ በግልኣድ ዘይት እና ሀኪም አለ፡፡ ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት የበለጠ ቅዱሳት መጻሕፍትን አታነቡምን? በእያንዳንዱ አንገብጋቢ ሁኔታ ውስጥ ጌታ ጥበብ እንዲሰጣችሁ ፈልጉት፡፡ በእያንዳንዱ ፈተና ውስጥ ከችግራችሁ መውጫ እንዲያዘጋጅላችሁ ኢየሱስን ለምኑት፡፡ ያኔ ፈውሱን እንድታዩና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተመዘገቡ ተስፋዎችን ለገጠሙአችሁ ችግሮች እንድትጠቀሙ ዓይኖቻችሁ ይከፈታሉ፡፡ በዚህ መንገድ ጠላት ወደ ሀዘንና አለማመን ሊመራችሁ ቦታ አያገኝም፣ ነገር ግን በተቃራኒው በጌታ እምነት፣ ተስፋና ድፍረት ይኖራችኋል፡፡ ለሀዘን እንደ ማርከሻ የሚያገለግለውን እያንዳንዱን በረከት ማየትና የራሳችሁ ማድረግ እንድትችሉ፣ በከናፍሮቻችሁ ላይ ለተደረገው ለእያንዳንዱ የመራርነት መጠጥ እንደ ፈዋሽ ቅርንጫፍ እንዲሆንላችሁ መንፈስ ቅዱስ የጠራ መረዳትን ይሰጣችኋል፡፡ እያንዳንዱ የመራርነት መጠጥ ከኢየሱስ ፍቅር ጋር ይቀላቀልና በማጉረምረም ፋንታ የኢየሱስ ፍቅርና ፀጋ ከሀዘን ጋር ከመደባለቃቸው የተነሳ ወደ መገዛትና ወደ ተቀደሰ ደስታ መለወጡን ትገነዘባላችሁ፡፡Amh2SM 273.3

    ታላቁ ልጃችን ሄንሪ ኋይት ሊሞት ሲል “የስቃይ አልጋ ኢየሱስ በዚያ ቦታ ከተገኘ የከበረ ቦታ ነው” ብሏል፡፡ መራራ ውኃችንን መጠጣት ግድ በሚሆንብን ጊዜ ፊታችንን ከመራራው ወደ ከበረውና ወደ ብርሐን እንመልስ፡፡ በፈተና ጊዜ ለሰብአዊ ነፍስ ፀጋ ማረጋገጫ መስጠት ይችላል፡፡ በሞት አልጋ ላይ ቆመን ክርስቲያን እንዴት መከራን እንደሚሸከምና በሞት ሸለቆ ውስጥ እንዴት እንደሚያልፍ ስንመለከት ለመስራት ብርታትንና ድፍረትን እናገኛለን፣ አንደክምም፣ ነፍሳትን ወደ ኢየሱስ ለመምራትም ተስፋ አንቆርጥም፡፡--Letter 65a, 1894.Amh2SM 274.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents