Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 35—በዕድል ዘዴዎች መመራት

    (ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ለመወሰን የተከተላቸውን ዘዴዎች በተመለከተ ለንግድ ሰው የተሰጠ ምክር)

    ኃይማኖታዊ ተግባራትን በተመለከተ ትክክለኛ ወደሆኑ ውሳኔዎች ለመድረስ እና የንግድ ድርጅቶችን በተመለከተ መከተል ያለብህን አቅጣጫ ለመወሰን ሳንቲምን ወደ ላይ ወርውረህ ሳንቲሙ የወደቀበት ጎን እንዲወስን ትጥራለህ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ዘዴዎችን ማደፋፈር እንደሌለብን መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች እጅግ ተራ የሆኑ፣ የእጅ አጠቃቀም ቅልጥፍናን የሚጠይቁ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ከእግዚአብሐር ስላልሆኑ መመሪያ ለማግኘት በእነርሱ ላይ የሚደገፉ ሰዎች ውድቀትና ተስፋ መቁረጥ ያጋጥማቸዋል፡፡ እነዚህ መፈተኛዎች የእድል ጉዳይ ስለሆኑ ተግባርን በተመለከተ እነርሱን እንደ መፈተኛ መቀበል ሥራዎቻችንና ለሥራዎቻችን ያሉን ዕቅዶች ሁሉ አስተማማኝ በሆነው የእግዚአብሔር ቃል ላይ መመስረት ሲገባቸው አእምሮ በዕድልና በግምት ሥራ ላይ እንዲደገፍ ለመምራት የተሰሉ ናቸው፡፡Amh2SM 325.1

    የእግዚአብሔር ሕዝብ ተግባራቸውን በትክክል ወደ ማስተዋል መምጣት የሚችሉት ልባዊ በሆነ ጸሎትና በመንፈስ ቅዱስ ለመቀደስ ተግተው ሲሹ ብቻ ነው፡፡ መከተል ያለባቸውን አቅጣጫ በተመለከተ መመሪያ ለማግኘት በትክክል ሲሹ እነዚህ እንግዳና ተአማኒነት የሌላቸው ዘዴዎች ተቀባይነት አያገኙም፡፡ ያኔ በዘፈቀደ ከሚሰራ ሥራ እና ሰው በቀየሳቸው ዘዴዎች ከመደገፍ የተነሳ ከሚመጣ ግራ መጋባት ይድናሉ፡፡Amh2SM 325.2

    ለሕዝባችን ይህን እላለሁ፣ ማንም ቢሆን እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመምራት ያስቀመጣቸውን ግልጽና ትርጉም የሚሰጡ መርሆዎች በመተው መመሪያ ለማግኘት ሳንቲምን ወደ ላይ የመወርወር ዘዴዎችን አይከተል፡፡ ይህ መንገድ የነፍሳት ጠላት የሆነውን በደንብ የሚያስደስት መንገድ ነው፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ጠላት ሳንቲሙን ለመቆጣጠር በመስራት በወኪሎቹ አማካይነት እቅዱን ስለሚፈጽም ነው፡፡ እነዚህን በመሳሰሉ መፈተኛዎች በመደገፍ ማንኛውም ሰው በቀላሉ መታለል የለበትም፡፡ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት ባላቸው ነገሮች ላይ መመሪያ ለማግኘት እነዚህን ርካሽ ዘዴዎች በመጠቀም ማናቸውም ቢሆኑ ልምምዳቸውን ማቅለል የለባቸውም፡፡Amh2SM 326.1

    እግዚአብሔር በዘፈቀደ መንገድ አይሰራም፡፡ እጅግ ቅንነት በተሞላበት ሁኔታ በጸሎት ፈልጉት፡፡ አእምሮን በመንካት ቋንቋና ቃል ይሰጣል፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እርሱ ስለ እነርሱ ያለውን ፈቃድ ለማወቅ በሰብአዊ ፈጠራዎች እና እርግጠኛ ባልሆኑ መፈተኛዎች እንዳይታመኑ መማር አለባቸው፡፡ ሰይጣንና ወኪሎቹ ነፍሳትን ከእግዚአብሔር ቃል ንጹህ መርሆዎች ለማራቅ በሚያገለግሉ ክፍተቶች ሁሉ ውስጥ ለመግባት ዝግጁ ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር የሚመራ እና ከእግዚአብሔር የተማረ ሕዝብ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚል ማረጋገጫ ለሌላቸው ፈጠራዎች ቦታ አይሰጡም፡፡Amh2SM 326.2

    ለጌታ መምጫ እየተዘጋጀን ነን የሚሉ ሁሉ የእርሱን ፈቃድ እውቀት ለማግኘት እና እርሱ በሚልከው ብርሃን ሁሉ ለመጓዝ ፈቃደኛ የሆነ መንፈስ እንዲሰጣቸው በትህትና ይሹ፡፡ ተግባራችንን በተመለከተ እንደ ሕዝብ ጥበብና ምክር ለማግኘት በእግዚአብሔር እንድንደገፍ ብዙ መመሪያ ተሰጥቶናል፡፡ ፈጣሪ «መጻሕፍትን እሹ» ብሏል፡፡ …ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ልጅ እምነት ለመራመድ በመማር በየቀኑ ልባችንን ትሁት ማድረግና ነፍሳችንን ማንጻት ያስፈልጋል፡፡Amh2SM 326.3

    ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ፣ ለመጠቀም እየተፈተናችሁ ያላችኋቸውን ጥቃቂን መፈተኛዎች ሁሉ በመተው መንፈሳችሁን በእግዚአብሔር ቃል ፈትኑ፡፡ የእግዚአብሔርን ባሕርይና ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ ቃሉን አጥኑ፡፡ እያንዳንዱ አማኝ አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን መመሪያው እና መጠበቂያው ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ወጣት ወንድና ሴት፣ እንዲሁም በዕድሜ ለገፉት፣ እስከመጨረሻው ጸንቶ ለመቆም ለሚፈልግ ነፍስ ከአደጋ መጠበቂያ ብቸኛው መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ Special Testimonies, Series B, No. 17, pp. 25-29.Amh2SM 326.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents