Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የችኮላ እንቅስቃሴዎች መዘዝ

    አንዳንዶች በችኮላ በመንቀሳቀስና ባትል ክሪክን ለቀው በመውጣት ተስፋ መቁረጥ ቢደርስባቸው በማይመከር ሁኔታ ለመንቀሳቀሳቸው ምክንያቶቹ ራሳቸው ሆነው ሳሉ ግፊት አድርገውብኛል ብለው ሌሎችን ይወነጅላሉ፡፡ ለደረሰባቸው ብስጭትና ሽንፈት ተጠያቂ መሆን የሌለባቸውን ሰዎች ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡…Amh2SM 363.2

    የመጨረሻ ቀናት አደጋዎች በዙሪያችን እየጨመሩ ያሉበት ጊዜ አሁን ስለሆነ ነገሮችን ማነሳሳትና ሕውከትን መፍጠር ሥራቸው እንደሆነ የሚሰማቸውን ሰዎች ሳይሆን መካር የሆኑ ጠቢባን ሰዎችን እንሻለን፡፡ ነገሮችን ማመሰቃቀልና ውዝግብ መፍጠር ሥራቸው እንደሆነ የሚሰማቸው ሰዎች ጥበብ ያለበትን ምክር መስጠት የማይችሉና እያንዳንዱን እንቅስቃሴ የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ ከውዝግብ ውስጥ ሥርዓትን፣ እረፍትንና ሰላምን ሊያመጣ በሚችል ሁኔታ ማደራጀትና ማስተካከል የማይችሉ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው እንደተሰጠው ልዩ ችሎታ ለጌታው የሆነ ሥራ ለመሥራት በትክክለኛው ቦታ ይገኝ፡፡Amh2SM 363.3

    ይህ ሊደረግ የሚችለው እንዴት ነው? በራሱ ክቡር ደም የገዛችሁና እናንተ ባሪያዎቹና ንብረቱ የሆናችሁለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፣ «ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴ. 11፡ 29፣ 30)፡፡ እያንዳንዱ ሰው ሊስተማር በሚችል መንፈስ፣ በተጸጸተ ልብ ወደ ኢየሱስ ቢመጣ ኖሮ ከኢየሱስ ለመማርና ትዕዛዞቹን ለመታዘዝ በሚችል የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ ይሆን ነበር፡፡…Amh2SM 364.1

    እያንዳንዱን እቅድ በእግዚአብሔር ፊት ዘርግታችሁ አስቀምጡ፡፡ አሁን ደካማ እምነት ሊኖረን አይገባም፤ ግድ የለሽ እና ሰነፍ አመለካከት ይዘን ከአደጋ ነጻ መሆን አንችልም፡፡ እያንዳንዷን ችሎታ መጠቀም እና ኃይለኛ፣ የተረጋጋና ጥልቅ ሀሳብ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጊዜ ለማቀድና ዘዴ ለመቀየስ የማንኛውም ሰብአዊ ወኪል ጥበብ በቂ አይደለም፡፡ እያንዳንዱን ዕቅድ በፆም እና በጌታ ኢየሱስ ፊት ነፍስን ዝቅ በማድረግ ዘርጉና የመንገዳችሁን አደራ ለጌታ ስጡ፡፡ እርሱ የሰጣችሁ እርግጠኛ የሆነ ተስፋ እንደሚያረጋግጥላችሁ ከሆነ በየትኛው መንገድ መሄድ እንደሚገባችሁ ይመራችኋል፡፡ እርሱ ገደብ የለሽ ሀብቶች አሉት፡፡ የሰማይን ሰራዊት በስማቸው የሚጠራ እና የሰማይን ክዋክብት በቦታቸው የሚያቆያቸው የእሥራኤል ቅዱስ እያንዳንዳችሁን በጥበቃው ሥር አድርጎ ይዞአችኋል፡፡…Amh2SM 364.2

    ክርስቶስን ብቃታቸውና መታመኛቸው ላደረጉት ሁሉ ምን ዓይነት አማራጮችና ዕድሎች እንዳሉአቸው ሁሉም እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ፡፡ በክርስቶስ ሆኖ በእግዚአብሔር ውስጥ የተደበቀ ሕይወት ሁልጊዜ መጠጊያ አለው፤ ከዚህ የተነሳ እንዲህ ማለት ይችላል፣ «ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ” (ፊልጽ. 4፡ 13)፡፡Amh2SM 364.3

    ይህን ጉዳይ ለእናንተ እተዋለሁ፤ በባትል ክሪክ ያሉትን ሁሉ ሊያገኛቸው ስላለው አደጋና ጥበብ በጎደለው ሁኔታ በመንቀሳቀስ ለጠላት ዕድል እንዳይሰጡ በማለት እጅግ ተጨንቄና ተረብሼ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ከሄድን ያለ አንዳች ችግር መሄድ ስለምንችል ጥበብ የጎደለው እንቅስቃሴ መሆን የለበትም፡፡ Letter 45, 1893.Amh2SM 364.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents