Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “ውድ ቤተሰብ”

    የቤተሰባቸውን ውድነት እንደ ሰበብ በመጥቀስ ከፍተኛ ደሞዝ ማግኘት አለብን ብለው የጻፉልኝ ወንዶች አሉ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያለው ተቋም የማንቀሳቀሻ ወጪን እንዴት መሸፈን እንዳለበት ለማግኘት ተገዷል፡፡ ማንም ቢሆን ከፍተኛ ደሞዝን ለመጠየቅ የቤተሰቡን ውድነት ለምን እንደ ምክንያት ያቀርባል? ክርስቶስ የሰጠው ትምህርት በቂ አይደለምን? እንዲህ ብሏል፣ «ማንም ከኋላዬ መምጣት ቢወድ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” (ማቴ. 16፡ 24)፡፡ Amh2SM 183.1

    ተቋሞቻችን የተመሰረቱት ነፍስን የማዳን ስራን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም እንዲያገለግሉ ነው፡፡ ከእነዚህ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ከተቋማቱ ግምጃ ቤት ውስጥ እንዴት ባለ ሁኔታ የተሻለ ጥቅም እንደሚያገኙ ሳይሆን ተቋማቱን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ማጥናት አለባቸው፡፡ ከሚገባቸው በላይ ከጨበጡ የእግዚአብሔር ሥራ እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ ከእነዚህ ተቋማት ጋር ግንኙነት ያለው እያንዳንዱ ሰው እንዲህ ይበል፡- «ከፍተኛ ደሞዝ መጠየቅ ግምጃ ቤቱን ስለሚያራቁትና የምህረት መልእክት እወጃን ስለሚደናቀፍ ከፍተኛ ደሞዝ አልጠይቅም፡፡ ቁጠባን መለማመድ አለብኝ፡፡ በውጭ በሥራ መስክ ውስጥ ያሉት እኔ እንደምሰራው ሥራ አስፈላጊ የሆነ ሥራ እየሰሩ ናቸው፡፡ እነርሱን ለመርዳት በእኔ አቅም የሚቻለኝን ሁሉ ማድረግ አለብኝ፡፡ እየያዝኩ ያለሁት የእግዚአብሔርን ገንዘብ ስለሆነ ክርስቶስ በእኔ ቦታ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገውን አደርጋለሁ፡፡ ገንዘብን በቅንጦት ላይ አላጠፋም፡፡ በሚስዮን መስክ ያሉትን የጌታን ሰራተኞች አስባለሁ፡፡ ከእኔ ይልቅ የበለጠ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሥራቸው ውስጥ እጅግ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ከገጠማቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡ ድሆችን መመገብና የተራቆቱትን ማልበስ አለባቸው፡፡ በእነርሱ የፍቅር አገልግሎት ድርሻ እንዲኖረኝ ወጪዎቼን መቀነስ አለብኝ፡፡» --Special Testimonies, Series B, No. 19, pp. 19, 20.Amh2SM 183.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents