Go to full page →

ምዕራፍ 8—የሀሰተኛ ነቢያትን ሀሳቦች መጋፈጥ Amh2SM 72

ልንጠብቅ የምንችለው ነገር Amh2SM 72

በተለየ ሁኔታ እግዚአብሔር እንዳስተማራቸው የሚናገሩና ሌሎችን ለመምራት የሚሞክሩ ብዙ ሰዎችን እንዳይ ተደርጌ ነበር፤ እነዚህ ሰዎች ለተግባር ካሉአቸው የተሳሳቱ ሀሳቦች በመነሳት እግዚአብሔር በፍጹም ያልሰጣቸውን ሥራ ይሰራሉ፡፡ የዚህ ውጤት ግራ መጋባት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በግል ደረጃ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስተዋል እንዲችል እሱን ከልቡ ይፈልግ፡፡ --Letter 54, 1893. {2SM 72.1} Amh2SM 72.1

ራዕዮች እንዳሉአቸው የሚናገሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ በውጭ አገርና በአሜሪካ ብዙዎች ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሊመሩ ስለሆነ ራዕዩ ከእሱ እንደሆነ እግዚአብሔር ግልጽ ማስረጃ ሲሰጥህ ልትቀበል ትችላለህ፣ ነገር ግን በሌላ በማንኛውም ማስረጃ አትቀበል፡፡ --The Review and Herald, May 25, 1905. {2SM 72.2} Amh2SM 72.2