Go to full page →

የእግዚአብሔርን ማህተም መቀበል አይችሉም Amh2SM 140

በልዑል አማኑኤል በደም በተቀለመ ባንዲራ ስር የሚቆሙ ከፍሪ ማሰኖች ወይም ከማንኛውም የምስጢር ድርጅት ጋር ሕብረት አይፈጥሩም፡፡ የእውነት ብርሃን በመንገዱ ላይ ከበራለት በኋላ የዚህን ዓይነት ግንኙነት ይዞ በሚቀጥል በማንም ላይ የሕያው እግዚአብሔር ማህተም አያርፍበትም፡፡ ክርስቶስ አልተከፋፈለም፣ ክርስቲያኖችም እግዚአብሔርንና ገንዘብን ማገልገል አይችሉም፡፡ ጌታ እንዲህ ይላል፣ «ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ» (2ቆሮ. 6፡17፣ 18)፡፡ --Letter 21, 1893. {2SM 140.1} Amh2SM 140.1