Go to full page →

ምዕራፍ 14—የሰራተኛ ግጭቶችን ማስወገድ Amh2SM 141

[ካንትሪ ሊቪንግ በሚል መጽሔት ገጽ 7፣ 9፣ 10-12 የወጣ]

የሰራተኛ ማህበራት የመቆጣጠር ኃይል በጣም ጨቋኝ የሚሆንበት ጊዜ በፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ወደ ፊት የመግዛትና የመሸጥ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ስለሚሆን ሕዝባችን ቤተሰቦቻቸውን ከከተማ አውጥተው ለራሳቸው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማምረት ወደሚችሉበት ወደ ገጠር እንዲወስዱ ጌታ በተደጋጋሚ አዞኛል፡፡ ከከተማ ወጥታችሁ ቤቶች እጅግ ተቀራርበው ወዳልተሰሩባቸውና ከጠላቶች ጣልቃ ገብነት ነጻ መሆን ወደምትችሉባቸው ገጠራማ መንደሮች ሂዱ ተብሎ በተደጋጋሚ የተሰጠንን መመሪያ አሁን መስማት መጀመር አለብን፡፡--Letter 5, 1904. {2SM 141.1} Amh2SM 141.1