Go to full page →

ከመለኮታዊው የሹመት ደብዳቤ ጋር መጓዝ ChSAmh 337

እግዚአብሔር መንፈሱን በነፍሳት መቅደስ ውስጥ እያኖረ በተመሳሳይ በእያንዳንዱ ሰው መጠቀም ይችላል፡፡ አምላካዊው አምሳል የሚንጸባረቅበት አገልግሎት በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው፡፡ ተከታዮቹ ዘላቂ ጸባይ የተላበሱትን ዘላለማዊ መርኅዎች የሹመት ደብዳቤዎቻቸው አድርገው ለዓለም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡-- Testimonies, vol. 7, p. 144. ChSAmh 337.2

የክርስቶስ ስም የይለፍ ቃላቸው፣ መለያ አርማቸው፣ የአንድነት ውላቸው፣ መገዣ ሕገ ደንባቸውና የስኬት ምንጫቸው ነው፡፡ የእርሱን ስም ያልያዘና ያልተጻፈበት ማንም በንግሥቱ ዕውቅና የለውም፡፡The Acts of the Apostles, p. 28. ChSAmh 338.1