Go to full page →

የነጻነት ተዋጊ ወታደሮች ChSAmh 338

ታማኝ የነጻነት ተዋጊ ወታደሮች በመሆን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃን ለጠራችሁ አምላክ ምስጋናችሁን አሳዩ፡፡Review and Herald, Jan. 24, 1893. ChSAmh 338.2

የእግዚአብሔር አገልጋዮችመለኮት ጣልቃ እየıባ የሚከፍተውን መንገድ እየተጠቀሙ ከነጻነት አርበኞች ጎን የሚሰለፉ ተዋጊ ወታደሮች ሊሆኑ ይገባል፡፡ ማንም የድርሻውን ከመወጣት ቢዘገይ ሰይጣን ማሸነፍ የሚያስችለውን ጊዜ የሚያገኝበትን ዕድል ይሰጠዋል፡፡- Patriarchs and Prophets, p. 423. ChSAmh 338.3

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ ሕዝቦቹ ዘወትር ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነው ሊገኙ ይገባል፡፡--Testimonies, vol, 8, p. 247. ChSAmh 338.4

በእውነት የክርስቶስ ተወካዮች የሆኑ ሁሉ ስለ ሌሎች መልካም ሲሉ ይሠራሉ፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ፊት ማራመድ በመቻላቸው ደስ ይሰኛሉ፡፡ በጸሎት ስብሰባ ወቅት አርአያነታቸው የሚታይ፣ የሚደመጥና የሚሰማ ይሆናል፡፡ የአገልጋዩ አገልግሎት መድረስ ያልቻለበትን ስፍራ ለመመሸፈን ይሞክራሉ፡፡ ራሳቸውን ግዙፍ አድርገው ለማቅረብ ወይም ለሠሩት ታላቅ ሥራ ዕውቅና ለማግኘት ሳይመኙ፤ ክርስቶስ እንደሠራላቸው እነርሱም በትህትናና በታማኝነት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ጥቃቅኖቹን የየዕለት ተግባራት ያከናውናሉ፡፡--Review and Herald, Sept. 6, 1881. ChSAmh 338.5