Go to full page →

ፋይዳ ቢሶቹ የሥነ ምግባር መምህራን ChSAmh 60

ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ከሚጠሩ መካከል አብዛኞቹ ከሰብዓዊ የሥነ ምግባር መምህርነት የዘለለ ፋይዳ የላቸውም፡፡ ክርስቶስን በዚህ ዓለም በመወክል ለእርሱ ክብር ለመስጠት የሚያስችላቸውን ብቸኛውን ስጦታ ተቃውመዋል፡፡ ቃሉን አድራጊዎች ላልሆኑት ለእነርሱ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እንግዳና ያልተለመደ ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር በአንድነት የሆኑትን እና በዓለም ያሉትን ለይተው የሚያሳዩት ሰማያዊ መርኅዎች ይህን ማድረግ በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ከሌሎች የተለዩና ልዩ ጠባይ ያላቸው ሕዝቦች የመሆናቸው ጉዳይ ያበቃለት ይመስላል፡፡እነዚህን ሁለቱን የሚለየው መስመር ደብዛዛና የማይታይ ሆኖአል፡፡ ሕዝቡ ራሱን ለዓለማዊ ልማዶች፣ ወጎችና ራስ ወዳድነት እያስገዛ ይገኛል፡፡ ዓለም ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ሕጉን መታዘዝ ሲገባው ቤተ hርስቲያን ሕጉን ተላልፋ ዓለም ውስጥ ገብታለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ ዓለምን እየመሰለች በመለወጥ ላይ ትገኛለች፡፡-Christ’s Object Lessons, pp. 315, 316. ChSAmh 60.2